በፕሮፓጋንዳ ቀውስ የሚዋዥቀው የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi – አምባገነን መንግስታት ወንጀላቸው እየበዛ መውጪያ ቀዳዳ እያጡ ሲሄዱ በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው የሕዝብ ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው በከፍተኛ ደረጃ ዘረፋ ውስጥ ሲዘፈቁ ሕዝብን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለመሸንገል የሚያደርጉት መፍጨርጨር ሕዝቡ ከነሱ ቀድሞ እንደሚያውቅ ይዘነጋሉ አሊያም እንደለመዱት በሃይል ለመቀጠል ደፋ ቀና ይላሉ::ይመስላቸውል እንጂ የሕዝብ ዝምታ በራሱ እየገዘገዛቸው መሆኑን ሕሊናቸው ስለተደፈነ አያውቁትም::የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝም የዚህ ድድብና ተጠቂ ስለሆነ ሕሊናውን ዘግቶ ሕዝብን በመናቅ በፕሮፓጋንዳ ቀውስ እየዋዠቀ ይገኛል::

የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ በረሃብ በጦርነት በነጻነት እጦት በመብት ገፈፋ በኑሮ ውድነት በማህበራዊ ዝቅጠት እየተጠበሰች ያለችውን ሃገራችንን እና እኛ ሕዝቦቿን በመደበቅ ኢትዮጵያ በልማት እና ዲሞክራሲ ጎዳና እንዳለች አድርጎ በራሱ ሕሊና እና ድሎት የሳላትን ኢትዮጵያ በማቅረብ በሃሰት መረጃ በማባዛት በወሬ እና በቁጥር ቁልል በመካብ በፕሮፓጋንዳ ሃሰትነት ሳያፍር ሰበካውን እንደቀጠለ ቢሆንም ፕሮፓጋንዳው በሕዝብ ንቃተ ሕሊና መቅደም የመጣ አገዛዙን ቀውስ ውስጥ ከቶት በራሱ አንደበት የሚናገረውን በመርሳት ራሱን አኮላሽቶ ሲገኝ ይህ የሚያመለክተው አገዛዙ ለውድቀት መቃረቡን መሆኑ በቂ ማሳያ ነው::

በኢትዮጵያችን የፖለቲካ ምሕዳሩ መዘጋቱ የኑሮ ውድነቱ ከመኖር ሕልውና በላይ መሆኑ ወጣቱ ትውልድ ከአልሚነት ይልቅ በማህበራዊ ቀውስ ተመቶ ለዝቅጠት መጋለጡ ያለው ሁኔታ ምስክር ነው::ያልተደረጉ እንደተደረጉ ያልተሰሩ እንደተሰሩ ተደርገው መቅረባቸው ያሌለ እድገት እንዳለ ተደርጎ መወራቱ አገዛዙ ምን ያህል በባዶ ፕሮፓጋንዳ እንደሚኖር ምስክር ነው::ድህነትን እቀርፋለው በሚል ለብልጭልጭ ዘላዊነት ላሌላቸው ልማት ተብዬ መነገጃዎች ከፍተኛ ገንዘቦችን በመበደር መጪውን ትውልድ ለከፍተኛ እዳ በመዳረግ ወደር ያልተገኘለት ኢ ፍትሃዊ ወንጀል በትውልድ ላይ እየፈጸም በሚገኝበት ውቅት በፕሮፓጋንዳ ብቻ እንዴት ድህነት እንደሚቀረፍ የሕዝብን ጥያቄ ሳይመልስ እንዴት ስደት ጦርነት እንደሚቆም ሰላም እንደሚገኝ መልስ ብሎ ሊያስበው ፍቃደኛ አይደለም:;አገዛዙ ሊወገድ የሚችለው በሕዝቦች የጋራ ትግል ስለሆን መላው ኢትዮጵያውያን ይህን በባዶ ሜዳ በፕሮፓጋንዳ ቀውስ የሚዋዥቀውን አገዛዝ ለመጣል በመረባረብ የዜግነት ግዴታችንን በመወጣት ለመጪው ተተኪ ትውልድ ነጻ ኢትዮጵያን እንድናወርስ በአንድነት እንታገለው::ድል የሕዝብ እንጂ የሃሰት ፕሮፓጋንዲስቶች አይደለም::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬