የህወሓት መንግስት የዓረና ኣባላትን ማሰሩን ቀጥሎበታል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የእስር ዜና..! Amdom Gebreslasie

======

Amdom Gebreslasie's photo.

የህወሓት መንግስት ከምርጫ በሗላም የዓረና ኣባላት ማሰሩ ቀትሎበታል። ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ በ2007 ዓ/ም ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ በኣፅቢ ወንበርታ የዓረና-መድረ

ክ የፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ነበረ።

ኣቶ ወልደገብርኤል የዓረና-መድረክ እጩ ተወዳዳሪ ሁኖ ሳለ ህወሓት የውሸት ክስ ፈጥረው የውሸት ምስከር ኣቅርበው፣ ክሱ በዉሉ ሳይከላከልና ሳይከራከር የኣስር ወር የእስር ፍርድ ሰጥተዉት ነበር።
በወቅቱ ይግባይ ጠይቆና ዋስ መብት ጠይቆ ከእስር ወጥቶ የነበረ ቢሆንም የሰበር ፍርድ ቤት ፍርዱ በዛሬ ቀን ኣፅንቶታል።

“እጩ ተወዳዳሪ እጅ ከፈንጅ ወንጀል እየሰራ ካልተያዘ በስተቀር ያለመከሰስ መብት ኣለው” የሚለው ሕግ በመጣስ ለሁለት ወራት ኣስረው የኣስር ወር እስራት ፈርደውበት ነበር።

በወቅቱ የዋስ መብቱ ይከበርለት ተብሎ ከእስር የወጣ ሲሆን ግዜው የምርጫ ወቅት ነው ቅስቀሳ ሊዘጋ ቀናት ሲቀረው ከእስር የለቀውትነበር።
ምርጫ ካለፈ በሗላ ከዓረና እንዲወጣ ያደረጉት ጥረት እንዲከሽፍ በማድረጉ ዳግም የተፈረደው መተግበር ኣለበት ብለው ዛሬ ሰኞ 10 / 01 / 2008 ዓ/ም ጉዳዩ በሰበር ችሎት ኣንስተው እንዲፀድቅ ኣድርገዋል።

ወልደገብርኤል ሀይሉ በዓረና ካሉት ጀግኖችና የለውጥ ሃይሎች ኣንዱ ሲሆን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ኣገራቸው ከወራሪ ነፃ ለማውጣት ከታገሉና መስዋእትነት ከከፈሉ ጀግኖች ኣንዱ ነው።

በወቅቱ በዛላምበሳ ዓይጋ ግንባር ተሰልፎ የሃይል መሪ ሁኖ የሻዕብያ ሰራዊት ደምስሰው ዓይጋ ነፃ ኣውጥተው በድል የተራራው ኣናት ከረገጡት ጀግኖች ኢትዮዽያውያን ኣንዱ ነበር።

ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ በህወሓት መንህስት ሁለት ግዜ ድብደባና ግርፋት ደርሶበት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትና ሆስፒታል ገብቶ ኣናክምም እስከማለት የደረሰ ግፍ ቢደርስበትም በህወሓት ግፍ ያልተንበረከከ ጀግና ነው።

የህወሓት መንግስት የዓረና ኣባላትና ደጋፊዎች ናቹ እያለ ህዝቡ በየቀበሌው እያሰረ፣ እያንገላታና እያዋከበ ይገኛል።

በኣሁኑ ሰዓት ህወሓት የትጥቅ ትግል የመረጡ ወገኖች ተመልሰው ኣገር ቤት ሲገቡ “ጀግኖች” የሚል የክብር ሹመት ሲሰጣቸው በኣገራቸው በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ዜጎች ደግሞ ኣገር ለቀው ጥይት እንዲያነግቡ የሚገፋፋ ግፍ እየፈፀመባቸው ይገኛል።

ለህወሓት መሪዎች ይሄ ጦረኛ ባህሪያቹ ትታቹ ባገሪቱ በሰለማዊ መንገድ ለሚታገሉ ዜጎች የሚሆን ምህዳር እንድትፈጥሩ ኣሳስባለው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!

IT IS SO…! Amdom Gebreslasie