የፀፀት ደወል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


regret
አሜሪካ ከመጣች 20 አመት አለፋት። ታዋቂ ድምፃዊ ናት። ከአመታት በፊት ተወልዳ ካደገችበት ጐንደር ይኖሩ የነበሩ ወላጅ እናቷን ወደዚህ ታስመጣለች። ምስኪን እናት አገሩ አልተመቻቸውም። ድምፃዊቷ በከፈተችው (ዝጉብኝ) መሸታ ቤት ዋልጌ ሃበሾች የሚያሳዩዋቸው ድርጊቶች እንባ ያስፈስሣቸው ያዘ። ሙዚቃው ሲረብሻቸው ይነጋል። ድምፃዊቷ ልጃቸው በየቀኑ ስድብ፣ ማንጓጠጥና ዘለፋ ለእናት «ቁርስና እራት» ሆናቸው። «እባክሽ ልጄ አገሬ ስደጅኝ» እያሉ በማልቀስ እግሯ ላይ ወድቀው ለመኗት። አሻፈረኝ በማለት እናትዋን ማዋረድ ቀጠለች። በሃዘን፣ በብስጭትና እንባ የታጠሩትና በዚህ ሁሉ ተደራራቢ ሃዘን የወደቁት እናት ህይወታቸው አለፈ። አስክሬን ይዛ አገር ቤት ብትሄድም ወንድሟ አይንሽን ላፈር ብሎ አሰናበታት። ድምፃዊቷ በሌሎች ሃበሾች ያደረሰችው አሳዛኝ በደል ቢታለፍ ይሻላል።…እየዋለ እያደረ በእናቷ ያደረሰችው በደል ክፉኛ በፀፀት አለንጋ ይሸነቁጣት ገባ። ሃዘን ባጋጠመበት ቦታ ስታለቅስ ትታያለች። የምታለቅሰው ደግሞ ያ በደሏ ድቅን እያለባት ይመስላል። «ፊቱን ነበር እንጂ አልሞ መደቆስ አሁን…..» ነበር የተባለው!?

ይህን ታሪክ ማውሳት ያስፈገው ወላጆችን አሜሪካ በማምጣት የምታሰቃዩ ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ለማሳሰብ ነው። ዘጠኝ ወር ተሸክማና በችግር ያሳደገች እናት (ያውም ምትክ የሌላት) ውለታዋ ስቃይ መሆን አለበት!?..በተለይ ወላጆች እዚህ ከመጡ በኋላ የሚጐዳቸው ቋንቋ አለማወቃቸው እንጂ ለፖሊስ ቢያሳውቁ ልጆች ምን እንደሚጠብቃቸው ግልፅ ነበር። ..የወዲ ደባልቄ ልጅ የፀፀት ደወል ትምህርት ይሁናችሁ!