አስተማማኝ ሰላም የሚመጣው – ግርማ ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አስተማማኝ ሰላም የሚመጣው – ግርማ ካሳ

አቶ ሞላን በተመለከተ፣ የአገዛዙ ሜዲያዎችም ወሬዉን በሚያስገርም ሁኔታ እያዳመቁት ነው። የአራቱ ድርጅቶች ጥምረት እንደፈረሰም ይናገራሉ”Ginbot-7, Arbegnoch, and DMHIT Merger collapsed leaders and rebel soldiers fleeing from Eritrea” ሲል ትግራይ ኦንላይን አይጋ ደግሞ “Dmhit and Molla said “Chaw to Comishtato life in Asmara” ሲል ጽፏል። ቢኒያም ከበደ፣ የተሰኘው የኢትዮጵያ ፈርስት (የህወሃት ፈርት ብዬዋለሁ) ድህረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ደግሞ የሚከተከውን አስፍሯል

“ሰሞኑን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ኤርትር ዉስጥ ግንባር ፈጠረ የተባለው ኃይል ፈርሶ ወደ ሱዳን መግባቱን ለማወቅ ተችሏል” ሞላ አስግዶም ከዉህደቱ ፊርማ በኋላ ከአስመራ ጀምሮ በየቦታው የነበረው ኅያሉን የተለያየ መክንያት እየሰጠ በድንበር አካባቢ ወደ ምትገኘው ጉልጅ የተባለች የገጠር ከተማ እንዲሰባሰብ ካደረገ በኋላ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የመረጃና የደህንነት አካላት ጋር ተደራድሮ በሰላም ወደ ሀገራቸው ለመግባት ስለጨረሰ፣ ሰራዊቱን ይዞ እንዲንቀሳቀስ ትእዛዝ በመስጠት አሥራ አንድ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በመያዝ ወደ ኡምሃጀር ጎዞ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል” (በነገራችን ላይ ቤን የተባለው እጅግ በጣም ዉሸታም ጋዜጠኛ እንደሆነ ይታወቅልኝ። ስለዚህ ምን እንዳለ ለማሳየት እንጂ የጻፈውን ከቁም ነገር ቆጥሬ አይደለም የጠቀስኩት)

መጀመሪያ ደረጃ፣ የአገር አድን ንቅናቄው የአራት ድርጅቶች ስብስብ ነው። ደሚትን ቢወጣም ሌሎች ሶስት ደርጅቶች አሉ። ስለዚህ አንድ ደሚት ወጣ ተብሎ የአራት ድርጅቶች ስብስብ ፈረሰ ብሎ ማውራት አያስኬድም።
ሁለተኛ ደሚት ወደ ሰላሳ ሺህ ሺህ የሚሆን ሰራዊት አለው። ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተወጣጡ ያሉበት ድርጅት እንደሆነ ይነገራል። ከአቶ ሞላ ጋር ወደ ሱዳን ገቡ የተባሉት ቢበዛ ወደ ሰባት መቶ ቢጠጉ ነው፡። ስለዚህ በአሥር ሺሆን የሚቆጠ ርሰራዊት ባለበት በመቶ የሚቆጠር አቅጣጫ ቢቀይሩ፣ የአገር አድን ንቅናቄው ፈርሷል በሚል ወያኔዎች ብዙ ጮቤ ባይረግጡ ጥሩ ነው።

በሶስተኛ ደረጃ ወያኔዎች የሚሉትን እዉነት ነው ብለን ተቀብለን፣ የአገር አንድ ንቅናቄው ፈርሷል፣ በኤርትራ በኩል ሊደረግ የታሰበው ትግል ዜሮ ገብቷል ብለን ብንቀበል እንኳን፣ የከፋው፣ የመረረው ሕዝብ በሌላ መልኩ ማመጹ የማይቀር መሆኑ ሊታሰብበት ይገባል። እንደዉም በኤርትራ በኩል መሆኑ ትንሽ ቢሆን ተቃዉሞዉን በአንድ አካባቢ ታምቆ እንዲቆይ አድርጎት ነበር። በዚያ ምንም ነገር ከሌለ ግን፣ ዜጎች ወደ አስመራ ከማምራት በአካባቢያቸው አመጽ የሚጀመሩበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ያ ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። አገሪቷን ወደ አናርኪ ይወስዳታል።

ስለዚህ ወያኔዎች በጉልበታቸው ተመክተው ማቅራራታቸዉንና እና ድንፋታችሁ አቁመው፣ ከሕዝብ ጋር ቢታረቁ ይበጃቸዋል። ዜጎች እንዲያምጹና በረሃ እንዲገቡ የሚገፋፋቸውን መሰረታዊ የመብትና የነጻነት ጥያቄ መመለስ መቻል አለባቸው። መንግስታዊ ዉንብድናቸውን ማቆም አለባቸው። ወደ 200 ጥቂት ወንጀለኞችን ፈተው፣ ምህረት አደረግን ብሎ መመጻደቅ ሳይሆን ወንጀል ያልፈጸሙትን በዉሽት የተከሰሱና የተፈረደባቸው የሕሊና እስረኞችን በሙሉ መፈታት አለባቸው። አገር ቤት እና በዉጭ አገር ካሉ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ብሄራዊ እርቅ እንዲመጣ በሩን መክፈት ይኖርባቸዋል። ያ ብቻ ነው አስተማምኝ ሰላም ሊያመጣ የሚችለው። አንጂ አቶ ሞላና ጥቂት የደሚት ሰዎች ከጨዋታ ዉጭ ሆኖኑ ነገሩ አበቃለት ማለት አይደለም።

ያሉ ቡድኖች፣ የተረጋገጠ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያደረጉት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ይታወቃል። ይሄንን ደግሞ ወያኔዎች በሚገባ ያውቅታል። በወልቃት ጠገዴ ሕዝቡ ራሱ ተደራጅቶ ጠመንጃ አንስቶ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። በቴፒ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያን ወረው በመያዝ ከመቶ በላይ እስረኞችን ማስፈታታቸው ይታወቃል። ይሄ ሁሉ ኤርትራ ያሉ ደርጅቶች ያደረጉት አይደለም። ስለዚህ ኤርትራ ያሉ ድርጅቶች ኖሩም አልኖሩም፣ ጠነከሩም አልጠነከሩም፣ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ካልተመለሰ፣ ወያኔዎች ባላሰቡትና ባልጠበቁት መልኩ፣ ሊቆጣጠሩት በማይችሉት ሁኔታ ተቃዉሞና አመጽ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ያጋጥማቸዋልም።

የጦርነት ወሬ መስማት፣ ጦርነት እንዳይኖር በርግጥ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ለአገርና ለልማት የቆሙ ከሆነ፣ እንግዲህ ተግባር ይታከልበት። አቶ ኃይለማሪያም በአዲስ አመት አዲስ ነገር ፣ መልካም ነገር መኖር አለበት እንዳሉ፣ መልካም ነገር፣ አዲስ ነገር ያሳዩን። ልማት ፣ ልማት ማለታቸውን አንጠላዉም። ግን ያለ መረጋጋት ልማት የለም። ያለ ሰላም መረጋጋት የለም። ያለ ፍትህና ያለ ሰብአዊ መብት መከበር ደግሞ ሰላም የለም።

በአገራችን ተከባብረን፣ በዘር በሃይማኖት ሳንለያይ፣ በፍቅር አገራችንን እንድገነባ፣ ሌሎች አገሮች የደረሱበት ደረጃ እንድንደርስ እንቅፋት እየሆኑ ያሉት ሕወሃት/ኢሕአዴጎች ናቸው ። ፖለቲካውን የሚያበላሹት፣ ጥላቻና መካራር እንዲያድግ፣ ህዝቡ በአገሩ አንገቱን ደፍቶ በፍርሃት ተሸምቆ እንዲኖር እያደረጉ ያሉት፣ የሚገዙትን ሕዝብ የሚያዋርዱ፣ የሚንቁ፣ የሚያፈናቅሉ እነርሱ ራሳቸው ናቸው።

አሁንም በአዲስ አመት እንመክራቸዋለን። እናስጠነቅቃቸዋለን። “የጦርነትን በር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት፣ ብቸኛው

ከጥላቻ ፍቅር፣ ከዘረኝነት፣ ኢትዮጵያዉነት፣ ከመከፋፈል አንድነት፣ ከጭካኔ ርህራሄ፣ ከቂም በል ይቅርታ፣ ከመረጋገጥ መሸካከም፣ ከማሰር መፍታት፣ ከመወንጀል ምህረት ማድረግ፣ ከመሰዳደብ በልዩነቶች መቻቻል፣ በጉልበትና በጠመንጃ ከመመካት በእግዚአብሄር መመካት፣ ከ እብሪትና ከጥጋብ ትህትና ይሻላል።

ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልብ ያለው ያስተዉል !