ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል:ኢትዮጵያዊነት በህዝብ ልብ ውስጥ ላይወርድ የነገሰ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ባለፉት 20 አመታት ሁላችን አንድ የታዘብነው ጉዳይ አለ::ስለኢትዮጵያዊነት ጠንካራ አቋም ያላቸው ስለሃገር የፖለቲካ ይሁን የኢኮኖሚ አንድነት የማህበረሰብ ትሥሥር ታላቅ አመኔታ ያላቸው ሰዎች ሲሰደዱ ሲወገዱ ሲሸበቡ አይተናል በአጠቃላይ አይፈለጉም:: የመንግስታዊ ፖለቲካ ጡዘት ውስጥ ሳይገቡ ስልጣን ሳይፈልጉ አሊያም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይደግፉ በነጻ አእምሮ ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ስላቀነቀኑ ስለዘመሩ ካለምንም ድርድር ለካልቾ አሊያም ለእስር ሲልም ለስደት ከፍ ሲልም ለጥይት ተዳርገዋል:: ሕወሓት እንደዚህ አይነት ሰዎችን ሲያይ ያቅለሸልሸዋል:: ከብአዴን እና ኦሕዴዽ ውስጥ ደግሞ የሕወሓት አለቅላቂ ቅጥረኞች በፍጹም ድድብና ውስጥ ሆነው የታዘዙበትን ብቻ ሲያኩ አስተውለናል ይብልጡኑ ግን ከአንድ ፓርቲ ሕወሓት ብቻ የሆኑ ሰዎች በጸረ ኢትዮጵያዊነት ሲንጫጩ በስፋት እያስተዋልን ነው::
በኢሕአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ዘለቅ ብሎ ተገብቶ ሲታይ ሙሉ በሙሉ ሕወሓት እና በከፊል የግንባሩ አባል ድርጅት ቅጥረኞች የሚያራምዱት የዘረኝነት (ጸረ-ኢትይኦጵያዊነት)አላማ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም አንድም በባንዳዎች መጠመቅ ከቤተሰብ የተወረሰ ሌላም በፖለቲካ ጥላቻ እና ቅናት ላይ የተመረኮዘ ሲከተልም የበታችነት ስሜትና የግል ጥቅም(ሆዳምነት) ነው::በብዛት ይህ ነገር የሚታይባቸው በበታችነት ስሜት ተጠፍንገው በራስ መተማመን ስለሚያጡ ነገን የሚፈሩ ሰዎች የወለዱት የዘረኝነት አባዜ ነው:: የሕወሓት አባላት ቤተሰቦች አብዛኛዎቹ በባንዳነት ለቅኝ ገዢዎች አድረው የነበረ በበታችነት ሕይወት ተጠፍንገው ያደጉ በቅናት እና መርዘኛ ጥላቻ የተመረዙ መሆናቸው እሙን ነው::በኢትዮጵያዊነት አሊያም በሃይማኖታዊ ትውፊት ትኮትኩቶ ያደገ ሰው ሕወሓት ውስጥ የለም ::ቢኖርም ተበልቷል አሊያም ተባሯል ሲልም ስለሰብኣዊነት እና ማንነት በመናገሩ የተለየ ሃሳብ በማምጣቱ ተወግዷል::ምንጫቸውን የረሱ የጥቅም ተገዢ የሆኑ ጥቂቶች ደግሞ ለጊዜው ስለሚጠቀሙ ብቻ ትፋታቸው እየላሱ ጸረ ኢትዮጵያዊ አቋም ይዘው ተደባልቀዋል::
ሕወሓት ከተለያዩ ሕዳጣን ሰብስቦ ያሰለጠናቸው እና በአውሮፓ እና አሜሪካ ተቀምጥው ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የሚያራምዱ ጥቂቶች የትም ላይደርሱ ቢፈራገጡ ምንም እንደማያመጡ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ::የኢትዮጵያን መበጣጠስ የሚያልሙ ጥቂቶች የድህረገጽ ሹምባሾች ዲስኩራሞች ኢትዮጵያዊነትን በወሬ ሊንዱት አይችሉም::ኢትዮጵያዊነት እንኳን በየድህረገጹ ከሕወሓት እየተከፈላቸው ቡራ ከረዩ የሚሉ አይደለም ምእራባውያን እንኳን መናድ እንደማይችሉ የታወቀ ሲሆን ሞክረምው አልተሳካላቸውም:: ሕወሓት እንደአመጣጡ ቢሆን እስካሁን ያለማትን አገር ለመመስረት ቢያልምም እንደማይሳካ ስላወቀው ነው ስልጣኑን የሙጥኝ ብሎ የሚውተረተረው::አሁንም ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል::ስለ ኢትዮጵያ የሚያዜሙ ስለኢትዮጵያ የሚናገሩ ሁሉ ታላቅ ናቸው:: በሕዝብ ልብ ውስጥ ይነግሳሉ::ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል::… እንዳቅለሸለሻቸው ወደ መቃብር ይወርዳሉ:: #ምንሊክሳልሳዊ