የትግላችን መለያ አርማ በአካል እና በጽሑፍ በሁለት መልኩ የሚገለጽ ይሆናል! ድምጻችን ይሰማ!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የትግላችን መለያ አርማ በአካል እና በጽሑፍ በሁለት መልኩ የሚገለጽ ይሆናል! ድምጻችን ይሰማ!
አርማዎቹ ጠቋሚ ጣት እና አንድ ቁጥር ናቸው!
ማክሰኞ ጳጉሜ 3/2007
ለዛሬ የትግላችንን መለያ ምልክት ይፋ እንደምናደርግ መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት የሰላማዊ ትግላችን አርማ በአካል እንቅስቃሴ ሲገለጽ የጠቋሚ ጣት ሲሆን በጽሑፍ፣ በግራፊክስ እና በግራፊቲ ሲሆን ደግሞ በክብ ቀለበት ውስጥ የሚቀመጥ 1 ቁጥር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
እንደሚታወቀው መለያ ምልክት (አርማ – ሎጎ) ታጋዮች አንድን ትግል ለመወከል እና በሩቁ ለመግባባት፣ የትግላቸውን ዓላማም ለሌሎች ግልጽ ለማድረግ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡ በየትኛውም የሕዝብ ትግል ውስጥ የጋራ አርማ መኖሩ ልቦችን ከሩቁ ያግባባል፡፡ ለጋራ የተሰለፉለት ዓላማ በብዙሃን መካከል የተንሰራፋ የጋራ ቋንቋ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ያውጃል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎችም ትግሉን ወክሎ ለመግለጽ አመቺ መንገድን ይፈጥራል፡፡
ላለፉት አራት ዓመታት ላደረግነው ሰላማዊ ትግል ገላጭ ናቸው ተብለው የታመነባቸው ሁለቱ መለያ ምልክቶች ከታች በተያያዙት ፎቶ ምሳሌነት እንደሚታየው መገለጫቸው ቢለያይም የሚወክሉት ሐሳብ ግን አንድ ነው፡፡ የተመረጡበት ምክንያትም፡-
1. የአንድ ጣት ምልክት ቢላል በሃይማኖቱ ሲጨቆን ጽናቱን የገለጸባት የ‹‹አሃዱን አሃድ›› መፈክር ተምሳሌት እንደመሆኗ መጠን እኛም በዚችው የ‹‹አሃዱን አሃድ›› ምልክት እንደህዝብ የሚደርስብንን ጫና ለመቋቋም ቁርጠኛ መሆናችንን ለማሳየት፤
2. ሃይማኖታችን ላይ የሚሰነዘርን ህገወጥ ጥቃት ለመከላከል በገባንበት ትግል ያሳየነው አንድነታችን ከምንም በላይ የጥንካሬያችን ምንጭ ሆኖ መቆየቱን ለመመስከር፤
3. እስካሁን በነበረው ትግላችን ጠቋሚ ጣትን ማሳየት ተቃውሟችንን ስንገልጽባቸው ከነበሩ መንገዶች አንዱ መሆኑን ለማረጋገጥ፤
ይህንን የአንድ ጣት ምልክት መጠቀም የምንችለው በአካል እንቅስቃሴ ብቻ እንደመሆኑ መጠን በጽሁፍና በግራፊክስ፣ እንዲሁም በግራፊቲ ስራዎች ወቅት የበለጠ ቀላል ለማድረግ የቁጥሩን ምልክት እንጠቀማለን፡፡ ለዚህም ሲባል ነው ለጽሁፍ እና ግራፊክስ ስራዎች ተመሳሳይ መልእክት የሚያስተላልፈው በቀለበት ውስጥ ያለ የአንድ ቁጥር ምልክት የተመረጠው፡፡ ሁለቱም ምልክቶች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሲሆኑ የሚወክሉትም ተመሳሳይ ሃሳቦችን ነው፡፡
ብሄራዊ የሃይማኖት ጭቆናን አንሸከምም!
በጋራ ተሳትፎ እና በአንድነት ዲናችንን እንጠብቃለን!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
