የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ እና የከንቲባው ምላሽ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


The town of Sodo, Ethiopia
በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አካባቢ አርሶአደሮች ያለ አግባብ ከይዞታችን ተፈናቅለናል ሲሉ ማማረራቸውን አንድ የዓይን ምስክር ተናገሩ ። ከተማይቱን ለማስፋፋት በተያዘው እቅድ በሺህዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ እና አርሶአደሮቹም ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ እንደሆነ ለዶቼቬለ አስረድተዋል። እርምጃው የማረራቸው አርሶ አደሮች ከከተማው መስተዳድር ለችግራቸው መፍትሄ እንዳላገኙ ም የዓይን ምስክሩ ተናግረዋል። የአይን ምስክሩ ለስራ ጉዳይ ወደ ወላይታ ሶዶ በሄዱበት አጋጣሚ አየሁ እንዳሉት በወላይታ ሶዶ ከተማ መስፋፋት ሰበብ ቤቶች የፈረሱትና አርሶ አደሮችም ከይዞታቸው የተፈናቀሉት በ8 የገበሪ ቀበሌማህበራት ነው። በነዚህ የገበሬ ቀበሌ ማህበራት ከሁለት ሳምንት በፊት በተጀመረው በዚሁ ዘመቻ የፈረ ሱት ከዓመታት በፊት እንዲሁም በቅርቡ ሃላፊዎች በፈቀዱት መሠረት ጭምር ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶች ናቸው። የዓይን ምስክሩ እንዳሉት ከነሐሴ አጋማሽ አንስቶ በቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ከ2500 በላይ ሰዎች መኖሪያ የነበሩ ቤቶች እንዲነሱ ተደርጓል ።በዚህ የተነሳም ብዙዎች መግቢያ አጥተው እየተሰቃዩ ነው እንደ ዓይን ምስክሩ። ለከተማው መስተዳደር ሮሮአቸውን ያሰሙት ከይዞታቸው የተነሱት የወላይታ ሶዶ አካባቢ አርሶ አደሮች ለችግራቸውም ሆነ ለስጋታቸው መፍትሄ የሚሆን መልስ አላገኙም ። በዚህ የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ ላይ ከንቲባው ምላሽ ሰጥተውናል። LISTEN