የተነከሰ ፍቅር (አርአያ ተስፋማሪያም)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አሜሪካ ከመጣ ረጅም አመት አስቆጥሯል። የጊዮርጊስ ክለብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ታዋቂ ኳስ ተጨዋች ነበር። አገር ቤት የነበረችውን ፍቅረኛውንና አንድ ልጅ ያፈራችለትን ሴት እጅግ ይወዳታል። ሌላ ሴት ጋር በጭራሽ ሄዶ አያውቅም። ለሚቀርቡት ሁሉ ስለፍቅረኛው አውርቶ አይጠግብም። ለጠበቃ በአስር ሺህ የሚቀጠር ዶላር ከስክሶ ፍቅረኛውን ከአገር ቤት ያመጣታል። ከብዙ አመት በኋላ ሲያገኛት ደስታው ከልክ በላይ ነበር። ከትላንት በስቲያ ስራ ውሎ ወደቤት ሲያመራ ከደጅ በርካታ ፖሊሶች ጠበቁት። እጁ ላይ ካቴና ገባ። ግራ ተጋባ። «ሊገድለኝ ነበር፣ አንቆ..አስፈራራኝ..ይገድለኛል..» እያለች ፍቅረኛው ትናገራለች። በጣም ከመደንገጡ የተነሳ «ምንድነው የምታወሪው? ..ማነው እንዲህ ያደረገሽ?» ቢልም ሰሚ አልነበረም። በፖሊስ ከተወሰደ በኋላ ታሰሮ ትላንት ተለቀቀ። እሷ ባለችበት ስፍራ (በቤቱ) ድርሽ ማለት እንደማይችል በፖሊስ ተነገረው። ጉዳዩ በህግ ተይዞዋል። ጐረቤቱ የሆነ ሃበሻ ሲናገር « ምን አይነት ዘመን ነው?…እንዴት ያለ ታላቅ የፍቅር ሰው መሰለህ!?…ገና ከመጣች 6 ወር ሳይሞላት እንዲህ ያለ ግፍ ትፈፅማለች?…እሱ ልቡ ብቻ ሳይሆን አንገቱ ተሰብሯል! ያሳዝናል! ምንም አያወራም፤ ፍዝዝ ብሏል። ምንም እንዳላደረጋት እመሰክራለሁ!» ይላል። የስንቱ ፍቅር ተነከሰ!?…ስንቶች በፍቅር ነገዱ!?..ስንቶች በፍቅር ቀርበው – ለጥቅም አደሩ!?….