በባህርዳር የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ታሰሩ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በባህርዳር ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

• ‹‹ሲገረፉ ተባባሪያቸውን ይናገራሉ፡፡›› ፖሊስ

በባህርዳር የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቁ ጥላሁንና የፓርቲው አባል የሆኑት አቶ ሲሳይ ታፈረ መታሰራቸውን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ፀኃፊ አቶ መልካሙ ታደለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሁለቱን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የትግስቱ አወሉ አንድነት አባል ነኝ የሚል መልካሙ ሙጨዬ የሚባል ግለሰብ ደብድበውኛል ብሎ እንደከሰሳቸው የገለፁት ፀኃፊው፤ ድርጊቱ ተፈፀመበት በተባለው ቀን አንዱ ተከሳሽ አዲስ አበባ እንደነበሩና ሌላኛውም በቦታው እንዳልነበሩ ገልጸው ክሱ ሆን ተብሎ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ለማጥቃት የተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከሳሹ ሌሎች የሚያዙ ‹‹ግብረ አበሮች አሉ›› እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ፖሊስም ‹‹ችግር የለም፡፡ ሲገረፉ ተባባሪያቸውን ይናገራሉ፡፡ ያወጡዋታል፡፡›› ሲል እንደሰሙ አቶ መልካሙ ታደለ ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የታሰሩት ዛሬ ነሃሴ 28/2007 ዓ.ም ሲሆን ባህርዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡