አዳማ ከተማ በግራፊቲ ጹሁፍ ተጠለቅልቃ ማደሯን ምንጮች ከስፍራው ገለጹ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዳማ ከተማ በግራፊቲ ጹሁፍ ተጠለቅልቃ ማደሯን ምንጮች ከስፍራው ገለጹ::#Ethiopia #MinilikSalsawi

አዳማ ከተማ በኮሚቴዎቹ ላይ የፈረደውን ኢህአዴግን በሚያሳስቡ በሚያስጠነቅቁ የግሬቪቲ ፅሁፎች ተፅፈው ማደራቸውን የቢቢኤን ምንጮች ገለፁ::በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ተፅፈው ካደሩት መካከል የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ ፍትህ ለኮሚቴው፣ ትግላችን ይቀጥልል ፣ ዋ ! ዋ ! ፣ ድምፃችን ይሰማ፣ አምባገነንት ስርአት ከትከሻችን ይውረድ ፣ we need freedom ፣ ትግላችን እስከ ድላችን የሚሉ ፅሁፎች በቀይ ቀለማት እንዲሁም በወረቀት ላይ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋ ተፅፎ ማደሩን የቢቢኤን ምንጮች በፎቶ ጭምር አስደግፈው ከላኩት መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

በሁኔታው የተደናገጡ ፖሊሶች ለማጥፋት በጠዋት ሲራወጡ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። መንግስት በሙስሊሙ ኮሚቴዎች ያስተላለፈው ውሳኔ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ቁጣ ከመፍጠሩም ባሻገር ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍለው ነው ተብሏል።