የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለፀ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለፀ
#Ethiopia

= በዛሬው ዕለት ስራ የለም፡፡ ስራ አቁመናል፡፡ የገቡ ሰራተኞች ቢኖሩም ቁጭ ከማለት ውጭ ስራ እየሰሩ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሰራተኛ ዝም ብሎ ቁጭ ብሏል = የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በየዓመቱ ሰኔ 20 በጀት ከተሰራ በኋላ ከትርፉ ድጎማ እንዲያገኙ ከፋብሪካው ጋር ስምምነት እንዳላቸው የገለፁት የፋብሪካው ሰራተኞች ፋብሪካው ትርፋማ ቢሆንም ድጎማቸው ስላልተሰጣቸው በዛሬው (ነሃሴ 25/2007 ዓ.ም) ዕለት የስራ
ማቆም አድማ እንዳደረጉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አንድ የፋብሪካው ሰራተኛ ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በዘንድሮው ዓመት ፋብሪካው ከፍተኛ
ትርፍ ቢያገኝም ድጎማውን ላለመስጠት ከስረናል ማለታቸው
ን ገልጸዋል፡፡‹‹በዚህ ዓመት ከፍተኛ ሽያጭ ነው ያለው፡፡ ወደ ውጭ የተላከውንእናውቀዋለን፡፡ ምርቱንም እናውቀዋለን፡፡ ይህን እያወቅን ነው ከስረናልየሚሉን›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ፋብሪካው መክሰሩን በመግለፅ ድጎማውን አልከፍልም እንዳለ የገለፁት ሰራተኞቹ፣ ፋብሪካው ከስሬያለሁ ካለም ኦዲት እንዲደረግ ቢጠይቁም ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹ተዘርፈናል!›› እስከማለት የደረሱ ሰራተኞች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ማኔጅመንት ለሳምንት ያህል ሰራተኛውን ለማሳመን ቢጥሩም ሰራተኛው ‹‹ካልተከፈለን፣ ወይንም ኦዲት ተደርጎ ካላወቅን›› በማለታቸው ስኬታማ
መሆን እንዳልቻሉ ተገልጾአል፡፡
ችግሩም ተባብሶም በዛሬው ዕለት ሰራተኛው የስራ ማቆም አድማ እንዳደረገ የፋብሪካው ሰራተኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በዛሬው ዕለት ስራ የለም፡፡ ስራ አቁመናል፡፡ የገቡ ሰራተኞች ቢኖሩም ቁጭ ከማለት ውጭ ስራ እየሰሩ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሰራተኛ ዝም
ብሎ ቁጭ ብሏል›› ሲሉ የፋብሪካው ሰራተኛ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡