ኩሌ ትል ነበር ( ሄኖክ የሺጥላ )


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኩሌ ትል ነበር ( ሄኖክ የሺጥላ )
አንድ እብድ ነበረች
ኩሌ የተባለች
ሱፍ የለበሰ ስታይ

Henoke Yeshetlla's photo.

የምትጮህ በአደባባይ ።

ኩሌ ሱፍ የለበሰ
በሷ አይን የበሰበሰ
በጨርቅ ውስጥ ተሸፍኖ

የሐቅ የሐቅ የረከሰ

እንደሆነ ታወራለች
ማን ሊሰማት ኩሌ አብዳለች !

ትላለች
እናንተ ናችሁ
ቤታችሁን አፍርሳችሁ
ክብራችሁን አዋርዳችሁ
ምሁር ተብዬዎቹ
መሪ ተብዬዎች
ባገር ስም ላገር ተጠሪ

ጨዋ መሳይ አጭበርባሪ
ያልሆነው ሆነ ባይ ፣ ጨርቃም የሹም ቀባጣሪ
ባገር በሕዝብ ሀብት ላይ ፣ የተሾመ አቃጣሪ !
ሱፍ የለበሰ ባንዳ
ህሊና ቢስ ፣ ውስጠ ገንዳ !
ጭቃ አእምሮ ፣ ቆሮቆንዳ

እንኳን ለሰው ለራስ ባዳ !
ቆሻሻ
ያገር ጥቀርሻ
የማንነት ፣ የስም ልምሻ !

እርካሽ ፣ ዘኬ ለቃሚ
ስንዴ ለማኝ ለቃቃሚ !
የብሶት ፍል ፣ ልቅቃሚ !

እናንተ ባለ ሱፎቹ
እናንተ !

ብላ እየጮኸች
በቆሻሻ የጠቆረ
መጥረጊያዋን እያሸች
ሶስት ውሾቿን አስቀድማ
ታለቅስ ነበር ለማማ !

ኩሌ ትጮህ ነበረ
ሱፍ የለበሰ ስታይ
የተሾመ መሪ ስታይ
በተራበ ሕዝብ መሃል

ቦርጩን መሸከም ያቃተው
የሰው አጋሰስ ስታይ
ሆዱ ጣኦት የሆነው
የቦርጭ ሙክራብ ስታይ
ትናገር ነበር ኩሌ !

ትላለች

እናንተ ሆድ አምላክ የሆነላችሁ
እናንተ የሰው እርጉሞች
በትውልድ ሕልም ቁማር
በሕዝብ ተስፋ ላይ ተስካር
በሀገር ትንሣዔ ላይ ሞት
ያወጃችሁ ከንቱዎች

ህዝብን በማበላላት
ባንዱ ላይ አንዱን ማስነሳት
ባንዱ ላይ ማስጠራት
አንዱን ባንዱ ማስመንጠር
በነገር ፣ ብበጎሰኝነት ፣ የፍቅር ውል መቆጣጠር
በየገደሉ መወርወር
ማፈናቀል እና መንቀል
መግደል ማስገደል ፣ ማስበላት
መብላት!
እርስ በእርስ መበላላት
መካድ መካካድ
የተሰራውን መናድ
ባህል የሆነላችሁ
እናንተ ሱፍ ለባሽ ሹሞች
የሀገር የታሪክ ነቀርሶች

ትል ነበር
ኩሌ እብዷ
ባለ ቆሻሻ መጥረጊያ
ባለ ድሪቶ ጉዷ !

እናንተ እርጉም ሱፈኞች
እናንተ ባለ ድንጋይ ቤቶች
ባለ አሸር ገርዶቹ
እናንተ መሪ ነን ባዮቹ
እናንተ
ልበ- ግ-ቾች
እናንተ
ሀገር አቀናን ባዮች
ያገር እኩዮች
እናንተ ፣ ላገር ቆምን ባዮች
የሃገርነት ምሰሶን ነቃዮች
ደመ ጥፋቶቹ

ቲግሪ-ዎቹ
ሸረኛ አውሬዎቹ !
የሰው ጉዶቹ !
እናንተ
መሰሪ ፣ መርዘኛ እባብ
ጠባብ ! ጠባብ ! ጠባብ

ብላ እየጮኸች
በቆሻሻ የጠቆረ
መጥረጊያዋን እያሸች
ሶስት ውሾቿን አስቀድማ
ታለቅስ ነበር ለማማ !

Henoke Yeshetlla's photo.
Henoke Yeshetlla's photo.
Henoke Yeshetlla's photo.
Henoke Yeshetlla's photo.