የባሕር ኀይላችን(Our Navy)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ኄኖክ ኄኖክ –
የባሕር ኀይላችን(Our Navy)
.
ከገናናው አክሱምና የካሌብ ቀይ ባህራዊ ሞገድ ደማቅ ታሪክ መነሳቱን ለጊዜው ቸል እንበለውና ወደ ትናንቱ እውነት እንመለስ።
.
ለእኔና በእኔ ትውልድ አዙሪት ውጥስ የተፈጠርን በሙሉ አልፎ አልፎም ቢሆን በጆሮዎቻችን “አየር ሃይል” እና “ጦር ሃይል” የሚሉ ቃላት ሲንቃጨሉ እንሰማ እንደሆን እንጅ ተረት ሆኖ የቀረውን “ባህር ሃይል” ለማወቅ አልታደልንም። እስቲ በቀይ ባህር ላይ የነበረንን የቅርብ ጊዜ ገናናነት ቆንጥረን እንመልከት፦
.
ከኤርትራ ውህደት ማግስት ጥልቅ የነበረው የአፄ ሃይለስላሴ የባህር ሃይል መኖር ተሳክቶ እውን መሆን የቻለው በ1955 ምፅዋ ላይ በከፍተኛ ወጪ በተገነባበት ጊዜ ነበር። ንጉሱ በእጭር ጊዜ ውስጥ ባህር ሃይላችንን ከየትኛውም የአለም ሀገር በላይ ቀዳሚ ማድረግም ችለዋል። በ1956 አስመራ ላይ በ1957 ራሱ ምፅዋ ላይ ጠንካራ የባህር ሃይል ኮሌጆችን በመክፈት ብቁ ኢትዮጵያዊያን የባህር ሃይል መኮንኖችን ማፍራት ችለዋል። ጥራቱን ይበልጥ የተሻለ ለማድረግም ከእንግሊዝ የባህር ሃይል አሰልጣኞችን በማስመጣት፣ እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያዊያንን “ሊቮርኖ” ወደተባለ የኢጣልያ ባህር ማሰልጠኛ እና በአሜሪካ ሜሪላንድ የባህር አካዳሚ በመላክ አሰልጥነው አሰማርተዋል። ይህንን የንጉሱን ብርታትና የባህር ሃይላችንን ጥንካሬ በማየትም የተለያዩ ሀገራት መርከቦችን፣ጀልባና ሂሊኮፍተሮችን በስጦታ ለግሰውልናል። በታሪካችንም በቀይ ባህር ላይ ሰንደቅ አላማችንን እያውለበለበች ለ31 አመታት መልህቋን የጣለችው አንጋፋዋ መርከብም በ1962 ከአሜሪካ መንግስት የተበረከተች ነበረች። ንጉሱ በመጨረሻ ዘመናቸውም የባህር ሃይሉን ክልል በማስፋት መቀመጫዎቹን ከምፅዋና አስመራ በተጨማሪ አሰብና ዳህላክ ደሴቶች ላይም ተክለዋል። ከ3500 በላይ ሰራተኞችም በውስጡ ነበሩት።

ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በተፈጥሯዊው ቀይ ባህራችን ላይ የገነቡትን ገናና የባህር ሃይል ታሪካችንን በስሱ ቃኝተናል። የንጉሱና የዘውዳዊው ስርኣት ባበቃለት ማግስት ስልጣኑን የተቆናጠጠው የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር (ደርግ) ከንጉሰ ነገስቱ ያላነሰ ጠንካራ የባህር ሃይል ለመገንባት ችሏል። ደርግ የስልጣኑ መጀመርያና መጨረሻ በጦርነት ቀጠና የተፈተነ መሆኑ ደግሞ ለዚህ ትልቅ ምክንያት ነው። ወታደራዊው መንግስት የባህር ሃይሉ አባላትን በመላ ከቀድሞ ሶቪየት ህብረት ጋር ትብብር በመፍጠር በአዲስ መልክ ማሰልጠኑን ተያያዘው። ደርግ ገና ከመነሻው በ1969 ሶማሊያ በኦጋዴን የከፈተችውን ወረራ ለመቀልበስ የባህር ሃይሉ ትልቅ ሚና ተጫውቶለታል። ለዚህም ሲባል ደርግ የምፅዋን ማእከልነት በመሻር ወደ አሰብ ፊቱን አዙሯል። በጊዜው ውጥረት ውስጥ የነበረው ደርግ ሻቢያ በድንገት የባህር በሩን መውጫና መግቢያ ቢቆጣጠር እንኩዋ ሀገራችን ባህር በር አልባ እንዳትሆን አሰብን በከፍተኛ ብርጌድ የባህር ጦር ያስጠብቅ ነበር። በተጨማሪም ደርግ ቀይ ባህር ላይ 2 ግዙፍ የጦር መርከቦች፣8 ተወንጫፊ ጦር መሳርያ ማመላለሻ ጀልባዎች፣ 6 በባህር ውስጥ የሚጉዋዙ የቦንብ መርከቦች፣ 6 ቀጠናውን በባህሩ ላይ እየተንሳፈፉ የሚቆጣጠሩ መርከቦች፣2 በባህር ውስጥ የተተከሉ መከላከያ መርከቦች፣እንዲሁም 2 ረዳትና የስልጠና መርከቦችን በመገንባት አስፈሪና ሀገርን የሚያኮራ ታላቅ የባህር ሃይል ፈጥሮ ነበር። አሜሪካ ትጥቅ ትግልን ከመረጡ የውስጥ ተቃዋሚዎች ጋር ጋብቻ የፈፀመችበት አንዱ ምክንያትም ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ገናና የባህር ሃይል መፃኢ ስጋት ስለሆነባት ጭምር ነው።
.
ሆኖም ነገሮች ባልታሰቡበት አቅጣጫ ደርግ በመውደቁ ባህር ሃይላችን ዛሬ ላይ ተረት ሆኖ ቀርቷል።
