የማለዳ ወግ … የቅጥፈት ዲፕሎማሲ ! ነቢዩ ሲራክ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የማለዳ ወግ … የቅጥፈት ዲፕሎማሲ !
========================
* ” ሰራተኞች የሳውዲ ባህል እና አኗኗርን በተገቢ መንገድ እንዲያውቁ ተደርገው የሰላጠኑ ናቸው !” ባለስልጣኑ እአአ በ2012 ዓም
* ” …ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች ነፍስ በማጥፋት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል ፣ ጉዳዩ እስኪጣራ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማስመጣት ቆሟል ! ” የሳውዲ መንግስት
* አዲስ ይፈረማኝ የተባለው ስምምነት 2008 ዓም ቅድመ ዝግጅት ፣ ውይይት አልተደረገበትምና ያሳስበናል
* ከዚህ ቀደም ለመጡት መቶ ሽዎች መብት ሳናስከብር ሌላ ሰራተኛ ፣ ለምን ?
በሀገረ አሜሪካ አትላንታ ከሚሰራጨው ታዋቂ የአድማ ስ ራዲዮ አዘጋጅ ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጋር በብላቴናው መሀመድ አንድልአዚና በአዲሱ ዓመት ይጀምራል በተባለ ው የሳውዲና የኢትዮጵያ የሰራተኛ ሰምምነት ዙሪያ ለውይ ይት ተቀጣጥረናል ። በተለይም በሰራተኛ ውሉ ዙሪያ ለው ይይታችን ግብአት የሚሆኑኝን ያለፉት መረጃዎችን እያገለ ባበጥኩ መመልከት ጀመርኩ ። ” አሳ ጎርጓሪ … ” እንዲሉ ወደ ውስጥ ተመስጨ ገባሁና ለአንድ ማለዳ ወግ የምትሆነኝን መረጃ እነሆ አደረስኩ
ያኔ እአአ በ2012 ዓም ህጋዊ ውል ሳይፈጸም ግማሽ ሚሊዮን ሰራተኛ ለጠጉ 45 ሽህ ያህ የቤት ሰራተኞች ወደ ሳውዲ በወር ማስገባት ሲጀመር በሳውዲና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት የተሰጠው ስምምነቱን ህጋዊ የማስመሰል የተደሰኮረው የቅጥፈት ገለጻ ሁሉ ታወሰኝ ። ” አይመጋም መስሎሽ… ” እንዲሉ ያ ጊዜ አልፎ አሁን ሌላ ጊዜ ሊመጣና የተለመደው ማደንቆር አሁንም መልኩን ቀይሮና ዘምኖ ቀጥሏል !
ለግንዛቤ መረጃ ሳገላብጥም በመንግስት ከፍተኛ ኋላፊነት ያሉ ወገኖች የሰነዘሩትን የያኔ የቅጥፈት ዲፕሎማሲያዊ መረጃ አገኘሁትና ጥቂት ቆዘምኩ … እአአ 15 March 2012 በወጣው የሳውዲ ጋዜጥ ላይ መረጃውን ይዞ በተሰራጨው ጋዜጣ ቅጥፈቱ እንዲህ ይላል ” Ethiopian housemaids are trained well on Saudi customs and traditions …” በአጭሩ ሲተረጎም ” ከኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች የሳውዲ ባህል እና አኗኗርን በተገቢ መንገድ እንዲያውቁ ተደርገው የሰላጠኑ ናቸው !” ይላል ፣ ወደ ሳውዲ ስለሚገቡት ባለስልጣኑ የሰጡት መግለጫ ሲያትት …
ባለስልጣኖች ያልሆነውን ሆነ ብለው ሲደሰኳኩሩ ፣ እኛ “ተው አይሆንም ፣ አልሆነም! “እያልን ፣ ይህን ተከትሎ ግማሽ ሚሊዮን ዜጎቻችን ሳውዲ ከገቡ በኋላ የሆነው ግን ሌላ ነው ። ጭራሽ የተበደልነው ተቆርቋሪ አጥተን የበደሉን ቀንበር መሸከሙ ሳያንሰን እአአ ሀምሌ 18, 2012 በወጣ ጋዜጣ ላይ ” ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች ነፍስ በማጥፋት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል ፣ ጉዳዩ እስኪጣራ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማስመጣት ቆሟል ” ሲል የሳውዲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሳወቀ ! ኢትዮጵያም ይህ በሆነ በሳምንቱ ሳወዲን ተከትላ እገዳዋን አጸናች !
ሁለቱም ሀገራት በጠረጰዛ ዙሪያ የሚስማሙበት ፣ በምድር የሚታሽ ፣ የሚሰቃየውን ወገን ፍላጎት ፣ ጥቅምና ይዞታ ያማከለ አለመሆኑን ሳስበው ሁሌም ያሳዝነኛል ። በቂ ጥናት ሳይደረግ ” ተደረገ ” ተብለን ፣ በቂ ስልጠና ሳይሰጥ ” ተሰጠ ” እያሉ ያለ ምንም አይነት መብት ከለላና አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት የዜጋን ጉልበት መሸጥ ተገቢ አይደለምና ሊታሰብበት ይገባል ብንልም ሰሚ አልተገኘምና የሆነው ሆነ!
ወጣቱ በሀገር ቤት ስራ አጥነት ፣ ድህነትና የናረው የኑሮ ውድነት አማሮት ወደ ሳውዲ መሰደድ ፣ መምጣት ይፈልጋል ። በህጋዊነት ተመዝግቦ መጥቶ ቢሰራም እንደ እድሉ ከሀገር የተሻለ ነገ
ር ሊያገኝ ይችላል ! ላያገኝም ይችላል ! ዳሩ ግን ሌላው ቀርቶ ሰራተኞችን በማሰልጠኑ ረገድ ቅድመ ዝግጅት ፣ ስልጠናና ከዚህ ቀደም ለመጡት በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ዜጋ የመብት ከለላ በሌለበት ሁኔታ ዜጎችን ዳግም ወደ ሳውዲ አምጥቶ መበተኑ አሳዛኝም አሳፋሪም ነው የሚሆነው! ይህን የምለው በተለያዩ የሳውዲ ግዛቶች ፣ ከተማሞችና ፣ ጭልጥ እስካለው በርሃ ባሉ መንደሮች ሳይቀር ያሉትን የኮንትራት ሰራተኞች ይዞታ አሳምሬ አውቀዋለሁና ነው !
እንግዲህ ከላይ ያነሳኋቸውን ነጥቦች ከመረጃ ጋር ማገናኘት ከፈለጋችሁ ከዚህ ሃር የለጣጠፍኳቸውን የጋዜጣ ስብስቦች ተመልከቷቸውና የየግላችሁን ፍርድ ስጡ ! መንግስት የሚያወጣው ህግ ፣ መመሪያ ሆነ ሰምምነት ከከባቢው ነባሬ ሁኔታ የተለየ መሆን የለበትም ! በመጭው የ2008 ዓም አዲስ ይፈረማል የተባለው ስምምነት ቅድመ ዝግጅት ፣ ውይይት አልተደረገበትምና ያሳስበናል ! የሰራተኞች ውል ሰምምነት ዛሬም እንደ ቀደመው የቅጥፈት ዲፕሎማሲ አደገኛ አካሔድ ሆኖ እንዳይጎዳን ከፍ ያለ ስጋት አለኝ … !
ይህም ያገባኛልና እናገራለሁ !
ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 24 ቀን 2007 ዓም