ሰራዊቱ የተቃዋሚ ሃይሎችን ጫን ያለ ጉልህ እንቅስቃሴ አድብቶ እየጠበቀ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሰራዊቱ የተቃዋሚ ሃይሎችን ጫን ያለ ጉልህ እንቅስቃሴ አድብቶ እየጠበቀ ነው:: ..
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- ወያኔ በፓርቲው መርሃግብር ጠርቦ የገነባው እና የመከላከያ ሰራዊት የሚለው ሃይል ውስጡ በስፋት በለውጥ ጥያቄዎች እየተንተከተከ ሲሆን የተቃዋሚ ሃይሎችን ጫን ያል ጉልህ እንቅስቃሴ አድብቶ እየጠበቀ መሆኑን በሰራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::በሚዲያ ከሚሰማው ውጪ ተቃዋሚዎች ሰርገው ገብተው ተጨባጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሰራዊቱ መሃል አለማድረጋቸው ሰራዊቱ ዝምታን እንዲመርጥ እና አድብቶ እንዲቀመጥ አድርጎታል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል::
ከቅንጅት በኋላ አንድነት ፓርቲ ላይ ትልቅ አትኩሮት አድርጎ ነበር ሰራዊቱ ያሉት መረጃዎች ለአንድነት ፓርቲ መፍረስ የፓርቲው በሰራዊቱ ውስጥ ድንገት ዘልቆ መግባት እና በሰራዊቱ ደረጃ መወያያ ነጥብ እንደነበር ታውቋል::ወያኔን በመጣል አንድነት ፓርቲ ጥሩ አስተዳደር ሊያመጣ ይችላል የሚል እምነቶች ፓርቲው ከመፍረሱ በፊት ይሰራጩ እንደነበርና ለፓርቲውም መፍረስ አስታውጾ እንዳደረገ ምንጮቹ ያለፉትን የወታደራዊ ደህንነት መረጃዎች ጠቅሰው አሁንም በፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የፖለቲካ መንገዶች እና ስትራቴጂዎች ወደ ሰራዊቱ ዘልቆ በመግባት እንቅስቃሴዎች ማድረግ አለባቸው ሲሉ አስምረውበታል::
የወታደራዊ ደህንነት ምንጮቹ እንደሚሉት ሰራዊቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ አንዴ ሲነሳ አንዴ ሲልፈሰፈስ አንዴ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሲሆንበት እንዲሁም ለመስዋትነት ዝግጁ ያልሆነ ጥገኛ ተቃዋሚ መብዛት ለውጥ እንዳይመታ እና ሰራዊቱ በፖለቲካው ማእበል ውስጥ እንዳይሳተፍ ከፍተኛ ተጽእኖ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል::ሰራዊቱ በዘረኝነት በኑሮ ውድነት እና በእድገት ማጣት እየተሰቃየ ሲሆን እንኳን ቤተሰቡን ሊረዳ ይቅርና ራሱን መቻል አቅቶት እየዋተተ ስለሚገኝ አጥብቆ ለውጥ የሚፈልግ ሲሆን በሌላ መልኩ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው መከፋፈል የተቃዋሚዎች እጅ ቢጠልቅበት በራሱ ሰራዊቱን እንዲያምጽ ያደርገዋል ሲሉ አስገንዝበዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ