የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያንና የቀዳማዊ ኃ/ስላሴን አስተዋጽኦ ዘከረ ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በመጪው ጥቅምት የ70ኛ አመት የምስረታ በዓሉን የሚያከብረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ ኢትዮጵያና የቀድሞው የአገሪቱ መሪ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በድርጅቱ መስራች አባልነት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ የሚዘክርና የበዓሉ አካል የሆነ ልዩ ፕሮግራም ማካሄዱን ታዲያስ መጽሄት ዘገበ፡፡

ኒውዮርክ ሲቲ ውስጥ በሚገኘው የተመድ ዋና ጽህፈት ቤት ከትናንት በስቲያ በተከናወነው በዚህ ልዩ ፕሮግራም ላይ አለማቀፍ እውቅና ያላቸው የታሪክ ተመራማሪዎች፣ ጸሃፊያንና በተመድ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልኡክ ዶክተር ግርማ አበበ፤ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በተመድ የነበራቸውን ሚና በተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልምና ንጉሱ እ.ኤ.አ በ1963 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በዋይት ሃውስና በሌሎች መድረኮች ላይ ያደረጓቸውን ንግግሮች የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎች ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡

በተመድ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልኡክና የተመድ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ጉዳዮች ክፍል ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር ግርማ አበበ ባደረጉት ንግግር፤ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባዎች ላይ ያደረጓቸውን በሰላም፣ በጸጥታና በሰብዓዊመብቶች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ንግግሮችን ዳስሰዋል፡፡

PHOTO – H.I.M. Haile Selassie I Emperor of Ethiopia address to the General Assembly – 1963.  (Minilik Salsawi)