ሚሊየነሩ ኒቆ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ኒቆዲሞስ ዜናዊ ሁለት ካተርፒለር አገር ውስጥ በማስገባት ቢዝነሱን እያጧጧፈ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ከ200 ሺህ ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ ከደ/አፍሪካ የተገዙት የኮንስትራክሽን መገንቢያ ማሽኖች በመከላከያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው በኬኒያ በኩል መግባታቸው ሲታወቅ ምንም ቀረጥ እንዳልተከፈለባቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በደርግ ዘመን በክብሪት ፋብሪካ ተራ ወዛደር የነበረው ኒቆዲሞስ ዜናዊ ታላቅ ወንድሙ የሚመሩት ፓርቲ ስልጣን በያዘ ማግስት 25ሺህ ዶላር የምታወጣ አውቶማቲክ ማርሽ ዘመናዊ አውቶሞቢል ከአሜሪካ ተሸምቶለት ያለቀረጥ መግባቱ ይታወቃል።
«ወጋህታ» የተባለች የትግርኛ ጋዜጣ ያለቀረጥ የገባችውን አውቶሞቢል ሻንሲ ቁጥርና ከቀረጥ ነፃ የተባለበትን ማስረጃ (ደብዳቤ) ይፋ በማድረግ ማጋለጧ ይታወሳል። ከአንድ ኤርትራዊ ጋር በመሆን «ጃክሮስ ኢትዮጵያ» የሚል በማቋቋም «ቤት እንገነባላችኋለን» በማለት 70ሚሊዮን ብር ሰብስበው የዘረፉት እነኒቆዲሞስ ይህ የዝርፊያ ወንጀል በቲቪ የአይናችን ፕሮግራም ቢጋለጥም ሳይጠየቅ እንደቀረና ኤርትራዊው ሶስት ቀን ከታሰረ በኋላ ከአገር እንዲወጣ መደረጉ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ1993ዓ.ም ጋዜጠኛ ሴኩቱሬ ለአቶ መለስ ዜናዊ « ከወንድሞ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ነገር አለ፤ ይህን እንዴት ያዩታል?» ብሎ ሲጠይቃቸው « ወንድሜን ያገኘሁት አዲስ አበባ እንደገባን ሲሆን ከዛ በኋላ ሳላገኘው ቆይቼ የእናታችን ቀብር ላይ ነው ያገኘሁት። ነገር ግን ስላልከው ጉዳይ ስሰማ ከዚህ ተግባር ተቆጠብ ብዬ መክሬዋለሁ» ብለው ነበር። «አግኝቼው አላውቅም» ባሉበት አንደበት «መክሬዋለሁ» ማለታቸው እርስ በእርሱ የሚጋጭ ምላሽ ነበር።