የመለስ ዜናዊ ግፍ – የገብረመድህን አርዓያ ምስክርነት!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የመለስ ዜናዊ ግፍ = የገብረመድህን አርዓያ ምስክርነት!
ስለ ሀውዜን ጭፍጨፋና ስለ ሌሎች የህወሓት ሚስጥሮች በቀዳሚነት እየተናገሩ ከሚገኙት መካከል ገብረመድህን አርዓያ የተባሉ የቀድሞ የህወሓት አመራር ይገኙበታል፡፡ አቶ ገብረ መድህን እንደሚሉት የሀውዜን ጭፍጨፋ ሚስጥር የሚጀምረው የህወሓት ሰራዊት ከትግራይ ውጭ መዋጋት እንደማይፈልግ አቋን በገለፀበት ወቅት ነው፡፡ በወቅቱ የህወሓት አቋም ያልተስማማው 10 ሺህ ያህል ሰራዊት ከጦር ሜዳ አፈግፍጎ ወደ ትውልድ ሰፈሩ ተመልሷል፡፡
ይህ የሰራዊቱ አቋምም የህወሓትን የመጨረሻ አጣብቂኝ ውስጥ ያስገባ ነበር፡፡ በመሆኑም ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ወደ ሰራዊቱ ድረስ በመሄድ ለማግባባት ጥረዋል፡፡ አልሆን ሲል ከጦር ሜዳ ያፈገፈጉት የሰራዊቱ አባላትም ታድነው እንዲያዙ በማስደረግ፡፡ቤተሰቦቻቸውም የተመለሱትን የሰራዊቱን አባላት ይዘው እንዲሰጡ ጫና ተደርጎባቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹም
ታስረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በርካታ የሰራዊት አባለት ጠፍተው መቅረታቸውን የሚገልጹት አቶ ገብረ መድህን በድሮው የእነ መለስ አስተሳሰብ አምነው ‹‹እኛ ትግራይን ነፃ አውጥተናል›› ብለው በተመለሱ የሰራዊቱ አባላት ላይ ግድያ መፈፀሙንም መስክረዋል፡፡
ይህ የህወሓት እርምጃ ግን ሰራዊቱ ወደ ቀሪው ኢትዮጵያ ክፍል እንዲዘምት ለማሳመን በቂ አልነበረም፡፡በመሆኑም ሌላ ስልት መነደፍ ነበረበት፡፡ ሀውዜንን ማስጨፍጨፍ፡፡ አቶ ገብረ መድህን አርዓያ እንደሚሉት ህወሓት የትግራይን ከተሞች በማስደብደብ ህዝብን ማንቀሳቀስ የጀመረው በሀውዜን አይደለም፡፡ ከሀውዜን ቀደም ብሎም በተንቤን፣ አብአዲና ጭብሃ የተባሉ አከባቢዎች ላይም የህወሓት አመራሮችና ሰራዊቱ ከተሞቹ ውስጥ እንዳለ በማስመሰል ከተሞቹን በደርግ አስደብድቦ ህዝብን ለማንቀሳቀስ ጥሯል፡፡ይሄን ሀውዜንን ጨምሮ የማስደብደብ ስልትን የቀየሱት አቶ መለስና ስብሃት ነጋ መሆናቸውን ገብረ መድህን አርዓያ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል::