ጐዳና የተገፉ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አርአያ ተስፋማሪያም
[ፎቶ: ሰሎሞንና ልመንህ]
የዛሬ አመት አንድ አርቲስት እዚህ ዲሲ መጥቶ ሲያወራ « ከሌሊቱ 10 ሰዓት ቀረፃ አብረውኝ ያመሹትን ለማድረስ በሾላ መንገድ እያሽከረከርኩ ስጓዝ አካባቢው ጭር ብሎ ነበር። ሃይለኛ ዝናብ ይጥላል። በርቀት ዶፍ እየወረደበት በእግሩ የሚጓዝ ሰው ተመለከትኩ። ስንቀርብ ለካስ ልመንህ ታደሰ ነው» ሲል ከመሃከላችን አንዱ «እና ዝም ብለኸው ሄድክ?» አለ። «አዎ መንገዴን ቀጠልኩ» ርህራሄ የነጠፈበት የወዲ ጉግሳ ምላሽ ነበር። ሌላ የተናገረውን ባልደግመው ይሻላል። ኮሜዲያን ልመንህ ይህቺ ወረተኛ አለምና ህይወት ፊቷን ያዞረችበት አሳዛኝ ወገን የሚታደግ፣ ቢያንስ ፀበል እንኳ የሚወስድ ይጥፋ?.. ልመንህ በጤናው ሆኖ አገር ቤት ቢመጣ አጃቢው ይበዛ ነበር። በተመሳሳይ ለነፃው ፕሬስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከተው፣ በርካታ ድራማዎችን የፃፈው ጋዜጠኛና ደራሲ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰ ጊዮርጊስ ቤ/ር ጀርባ ጐዳና ማደርና መዋል ከጀመረ አመታት ተቆጠሩ። በዛ ላይ በኪንታሮት በሽታ ይሰቃያል። ረሃብ፣ በሽታና ስቃይ እንዲሁም ዝናብና ቁር ይፈራረቁበታል። በእሱ ጀርባ ተረማምደው ሚሊየነር የሆኑትና ለዚህ ያበቃቸው እነሰራዊት ፍቅሬና ሌሎች አይተው እንዳላዩት ያልፋሉ። ሰው ሲሞት አበባ ጉንጉን ለማስቀመጥና ታሪክ ለማነብነብ የሚቀድማቸው የለም። የጋሽ ተስፋዬ ለማ ውሳኔ መነሻው ይኸው መገፋት ነበር።