አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ 24 ሰአት ብርሃን እንዳያገኙ ተደርገዋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አልጀዚራ ያወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው የአውሮፓ ሕብረት አሜሪካ እና እንግሊዝ ለወያኔው ጁንታ መንግስት በአሜሪካ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል እና የካሊፎርኒያ የሪፕብሊካን ምክር ቤት አባል በሆኑት ዳና ሮህራባቸር ስም የተፈረመ ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 24 ሰአት በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስረው የተፈጥሮ ብርሃን እንዳያገኙ ተደርጎ በስቃይ ውስጥ መሆናቸውን ጽፈው መላካቸው ሲታወቅ አቶ አንዳርጋችው ጽጌ በአስቸኳይ እንዲፈጡ በደብዳቤያችው ጠይቀዋል::እንዲሁም ደብዳቤውን የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት ኤሚሊ ቶርቤሪና ጀርሚ ኮርቢን እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ሪቻርድ ሆዊት፥ አና ጎሜዝና ሌሎች ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎች ደብዳቤውን በጋራ መጻፋቸውን ተጠቁሟል::

በቅርቡ በአሜሪካ ድምጽ የቀረበ ራሱን ቴዎድሮስ የሚል አንድ የወያኔ ሚኒስቴር እንዳለው አቶ አንዳርጋቸው ላፕቶፕ ተሰቶት መጽሃፍ እየጻፈ ነው ቢልም እውነታው ግን የአለም አቀፍ ታላላቅ አገራት የፖለቲካ ሰዎች እና ታላላቅ ሚዲያዎች እንዳሉት ያሉበት ሁኔታና ቦታ የማይታወቀው አቶ አንዳርጋቸው በቤተሰቦቻቸው እንዳይጎበኙ ተደርጎ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አምባሳደሩ እና በደህንነት አታቼው ሶስት ጊዜ ብቻ እንደተጎበኙ ታውቋል።

እንግሊዝና የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች አቶ አንዳርጋቸው በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙና የህግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች ጥያቄ ቢያቀርቡም በወያኔ መንግስት በኩል የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩን አስታውቀው አቶ እንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥያቄያቸው ለወያኔ ጁንታ በደብዳቤ ያቀረቡት የአውሮፓ ሕብረት እንግሊዝ እና አሜሪካ የፖለቲካ ሰዎች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበት ሁኔታ አሳሳቢ እና በሀገሪቱን ከአለም ማህበረሰብ የሚያገል እንደሆነ አስቀምጠዋል። ደብዳቤው የወያኔ መንግስት በሰብአዊ መብት ላይ የሚከተለውን አካሄድ አጥብቆ መተቸቱም ታውቋል። ሲል አልጀዚራ ያገኘውን መረጃ በማጣቀስ ዘግቧል::