በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ለድርድር አዲስ አበባ የሄዱት የጁባ መንግስት የካቢኔ ሚኒስቴር ከነልኡካቸው ተባረሩ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በደቡብ ሱዳን የካቢኔ ሚኒስቴር በማርቲን ኢሊያ ሎሙሮ የሚመሩት እና የጁባ መንግስት አጋር ፓርቲዎችን ያቀፈው ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ የተባረሩ መሆኑ ታውቋል::ራዲኦ ታማዙ በዛሬው እለት በድህረገጹ እንዳሰፈረው የካቢኔ ሚኒስትሩ ከሚመሩት ቡድን ጋር የተባለሩበት ምክንያቱ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳት በጁባ የሚገኙ ተቃዋሚ ሃይሎች መሪ ላም አኮል በድርድሩ ላይ እንዳይሳተፉ ከደቡብ ሱዳን እንዳይወጡ ማገዳቸውን ተከትሎ መሆኑ ታውቋል::
የተባረሩት የካቢኔ ሚኒስትር ማርቲን አሊያ የመንግስት ደጋፊ ፓርቲዎችን እየመሩ ከደቡብ ሱዳን መንግስት ልኡካን ጋር በመሆን ባለፈው ሳምንት በሰላም ድርድሩ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ሲደርሱ ዋና የተባለው የደቡብ ሱዳን መንግስት ከመንግስት እጅ ነጻ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት እና በስላማዊ መንግድ ጁባ ላይ የሚንቅሳቀሱት ላም አኮል ወደ አዲስ አበባ መተው የሰላም ድርድሩን እንዳይሳተፉ ለበረራ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሯቸው በፕሬዝዳንት ኬር መታገዳቸው ታውቋል::
South Sudan’s Cabinet Minister Martin Elia Lomuro and his Group have been deported from Ethiopia – #MinilikSalsawi
