የአርባምንጭ ሕዝብ ባደርገው 2ኛ ድንገተኛ ተቃውሞ የጎፋና የጋሞ የወያኔ ሹሞች ስልጣን እንዲለቁ ጠየቀ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የአርባምንጭ ሕዝብ ባደርገው ድንገተኛ ተቃውሞ የወያኔ ሹሞች ስልጣን እንዲለቁ ጠየቀ::
የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ ይባላሉ፡ የጎፋ ብሔር ተወላጅ ናቸው፡፡ ሰሞኑን የሆነ መጽሀፍ ሲታተም ድጋፍ ያደርጋሉ(ለጊዜው የመጽሀፉን ርዕስ አልያዝኩትም) እናም መጽሀፉ የጋሞ ብሔርን ይነቅፋል፡፡ እናም ይህንን መጽሀፍ የዞኑ ዋና ከተማ የሆነችሁ አርባምንጭ እየኖሩ፡ ይህ መጽሀፍ እንዲታተም ይረዳሉ፡፡ ይህ መረጃ የደረሳቸው የጋሞ ተወላጅ የአከባቢው ባለስልጣናት በ አቶ ሽመልስና ሌሎች የጎፋ ብሔር ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞ እና ከስልጣን ይልቀቁልን ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡
ጥያቄያቸውን የዛሬ ሳምንት በተቃውሞ ሰልፍ ይገልጻሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ለአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተብሎ የመጣን አጎበር በነጋዴዎች እጅ ይገኛል፡፡ ነገሩ ሲጣራ ከጉዳዩ ጀርባ የአንድ የጎፋ ብሔር ተወላጅ ነገር ግን የአርባምንጭ ባለስልጣን እጅ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ከዚያም በዛሬው እለት ድንገተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ሕዝቡ ከአጎራባች አከባቢዎች ጭምር በመምጣት ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍና ባለስልጣናቱ ከስልጣን እንዲለቁ ጠይቋል፡፡ በመሐል የመኪኖችና የሕዝብ መጨናነቅ ሳቢያ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ሰልፉ በጋሞ አደባባይ አድርጎ ስቴድየም ነው የተፈጸመው፡፡ ይህ ጉዳይ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ከፍተኛ ወደሆነ የእርስ በእርስ ግጭት ሊከሰት ይችላል፡፡