አገሬ ስንት እዳ አለብሽ!?… ያገለገልኳት አገሬና ህዝቤ የሰጡኝ ምላሽ ይህ ከሆነ …ከነፈር እንዲመጥልኝ… አልሻም.. ሬሳዬ ይቃጠል»
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አገሬ ስንት እዳ አለብሽ!?… ያገለገልኳት አገሬና ህዝቤ የሰጡኝ ምላሽ ይህ ከሆነ …ከነፈር እንዲመጥልኝ… አልሻም.. ሬሳዬ ይቃጠል»= ” ጋሽ ተስፋዬ ለማ።”
አንጋፋና እውቅ የኪነጥበብ ሰው ነው። “ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ”ን ያቋቋመና የመጀመሪያውን የኪነትና ትያትር ቡድን አሜሪካ ይዞ የሄደ፣ “ህዝብ ለህዝብ” ታሪካዊ ስራ ያዘጋጀና የመራ፣ በርካታ ግጥምና ዜማዎችን የደረሰ፣ ከነዚህም በደርግ ጥርስ ውስጥ ያስገባውን «አልማዝን አይቼ- አልማዝን ባያት..» እንዲሁም «አርቆ ማሰቢያ..እንደምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ» የገጠመ ድንቅ አርቲስት ነበር።
አሜሪካ አገር የኢትዮጵያ ባህላዊ መሳሪያዎችንና ታሪኮችን ያካተተ ሙዚየም ከፍቶ ነበር። «መጠጥ ቤት ከምታመሹ ልጆቻችሁን እዚህ አምጥታችሁ የአገራቸውን ታሪክ እንዲያውቁ ብታደርጉ ይሻላል» ይል ነበር። ቻርልስ የተባለ አሜሪካዊ ማሲንቆ በአስደናቂ ሁኔታ እንዲጫወት ያደረገው ይህ ሰው ነው። ጋሽ ተስፋዬ ለማ። ሁለቱ ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጭ ሆነው፣ አስታዋሽና ጠያቂ አጥቶ ተሰቃየ። ከጐኑ ያልተለዩት ቻርልስና ሻምበል በላይነህ ነበሩ።
ጋሽ ተስፋዬ አንድ ኑዛዜ ፅፎ ለሻ/ል በላይነህ ሰጠው። «ያገለገልኳት አገሬና ህዝቤ የሰጡኝ ምላሽ ይህ ከሆነ አመሰግናለሁ። ማንም ሬሳዬ ላይ ቆሞ ከነፈር እንዲመጥልኝና ታሪኬን እንዲያነበንብ አልሻም። ስለዚህ ሬሳዬ ይቃጠል» በኑዛዜው መሰረት የጋሽ ተስፋዬ ሬሳ በአሜሪካ ተቃጠለ። አገሬ ስንት እዳ አለብሽ!?…