ሠማያዊ ፓርቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው:: አዲስ አመራር እንደሚመረጥ ይጠበቃል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ ነሐሴ 16 እና 17 የሚያካሂድ ሲሆን በዚህ ጉባኤ አዲስ መራር ይመረጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ የሚደረገው በየ3 ዓመቱ መሆኑን የጠቀሱት የፓርቲው ብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰይድ ኢብራሂም፤ ጉባኤው በሐምሌ መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች ምክር ቤቱ ለ3 ወር የማራዘም ስልጣኑን ተጠቅሞ እስከ ነሐሴ ማራዘሙን ገልፀዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ አባላት ቁጥርና የጉባኤውን አካሄድ ለመወሰን ብሄራዊ ምክር ቤቱ ስብሰባ እንደሚያደርግም ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያሳልጥ የተቋቋመው ኮሚቴም በእለቱ ሪፖርቱን ያቀርባል ብለዋል፡፡ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት አንድ ፕሬዚዳንት ለሁለት የስልጣን ዘመን ብቻ መመረጥ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ሰይድ፤ በአሁኑ ወቅት ፓርቲውን የሚመሩት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለሁለተኛ ጊዜ ይወዳደሩ አይወዳደሩ እስካሁን እንዳላሳወቁ ተናግረዋል፡፡