በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ የ 7 አመት እስራት ተበይኖባቸው በቃሊቲ ቀርተው የነበሩት 3ቱ ወደ ዝዋይ ተወሰዱ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ በሃሰት ተወንጅለው የ 7 አመት እስራት የተበየነባቸው ኡስታዝ ባህሩ ኡመር፣ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ እና ወንድም ሙራድ ሽኩር ወደ ዝዋይ እስር ቤት ዛሬ ተዋት መወሰዳቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከ 7 አመት በላይ የተፈረደባቸውን ኮሚቴዎቻችንን እና ወንድሞቻችንን ከቂሊንጦ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲዘዋወሩ የተደረገ ሲሆን 7 አመት የተፈረደባቸውን ግን በቃሊቲ እስር ቤት እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር፡፡ ጁምዓ ሐምሌ 1 ቀን የጁምዓ ሰላት ከሰገዱ ቡሃላ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ሁሉም የተዘዋወሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ሶስቱ ኡስታዞችን ግን በዛሬው ዕለት ወደ ዝዋይ እስር ቤት እንደሚዘዋወሩ እና እቃቸውን እንዲያስተካክሉ ተነግሯቸው ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ዛሬ ነሃሴ 2 ጠዋት ላይ ኡስታዝ ባህሩ ኡመር፣ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ እና ወንድም ሙራድ ሽኩር ወደ ዝዋይ እስር ቤትእንዲዘዋወሩ መደረጉ ታውቋል፡፡ ዝዋይ እስር ቤት ከአዲስ አበባ ክልል ውጪ ሲሆን ከኢትዬጲያ ካሉ እስር ቤቶች ውስጥ እጅግ አስፈሪ እና አደገኛው መሆኑ ይታወቃል፡፡