መምህር ዘበነ ለማ መጽሐፍ ለመጻፍ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛሉ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በቅርቡ በዶክተር ኦፍ ሚንስትሪ (Doctor of Ministry) ከHoward University የተመርቁት መምህር ዘበነ ለማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥልቅ ጥናት በማድረግ መጻፍ ሊጽፉ በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመዘዋወር መሰረታዊ መረጃዎችን ሲያሰባስቡ ቆይተው ተመልሰዋል። መምህር ዘበነ መጽሐፍ ለመጻፍ ፍላጎት ካሳደሩ ሰንበት ብሏል። ከሰባት (7) ዓመታት በፊት አውደምህረት ላይ ሆነው “በ5 ዓመታት ዉስጥ ዓለምን የሚያንቀጠቅጥ መጽሐፍ እጽፋለሁ” ብለው መናገራቸውን ያስታወሱ ምዕመናን አሁን የጀመሩት ጥናት ያንን ያካትት ወይም አያካትት የታወቀ ነገር የለም።
በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት በሊቢያ ሰማዕትነትን የተቀበሉትን ቤተሰቦችን ማግኘታቸውን በፎቶ FACEBOOK ላይ ተመልክተናል። ምናልባት የሊቢያ ሰማዕታትን በተመለከተ መምህር ዘበነ ለማ ብቻ የመናገር ባለቤትነት እንዳላቸው የሚያስመስል በሬድዮና በሌላም ሲያሰራጩ መቆየታቸውን የሚታወስ ነው። አግኝተን ያነጋገርናቸው የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ምእመናን የመምህር ዘበነ ለማ የአገር ቤት ጉዞ “ብዙ ፕሮጀክቶች አሉ ስለሚል ጉዞው ጥናት ለማድረግ በቂ ጊዜ አይመስልም “ብለዋል።
ቀጥለውም የመምህር ዘበነ ጉዞ ዲያስፖራውን ለመቆጣጠር በንቡረዕድ ኤልያስ የሊቢያ ሰማዕታትን በተመለከተ መምህር ዘበነ የሚመራው የዋሽንግተን አካባቢ የአንድነት ጉባኤ አስመዘገብኩ የሚለውን ዘገባ ለማቅረብ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ። በቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ሰላምን ለማውረድ ትልቅ ኃላፊነት የተቀበለ የሚያስመስል ጥቆማዎችን የተናገረው መምህር ዘበነ በጉዳዩ ሊገፋበት መመሪያ ተቀብሎ ይምጣ አይምጣ የተወቀ ነገር የለም።
መምህር ዘበነ ለማ የመሩትን በሊቢያ ሰማዕት ለሆኑትና በደቡብ አፍሪካ ለተገደሉት ኢትዮጵያዊያን በቨርጅንያ ግዛት ካና ማዕከል የተደረገው ‘ሙሉ’ ዘገባ በ EBS ሲተላለፍ አንዳንድ የወያኔን መንግስትን ያስከፋሉ የተባሉ ንግግሮችን ቆርጠው አስቀርተዋል የሚባል ሰምተናል። ሰሞኑን ማጣራት አድርገን ዘገባውን እናቀርባለን።