ከሰባት ዓመት በላይ የተፈረደባቸው የህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ቃሊቲ ማረሚያ መዘዋወራቸው ታወቀ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሐምሌ 27/2007 በዋለው ኢ ፍትሀዊው ችሎት ከሰባት ዓመት በላይ የተፈርዶባቸውና በቂሊንጦ ማረሚያ ይገኙ የነበሩት ወኪሎቻችን በትላንትናው ዕለት ወደቃሊቲ ማረሚያ እንደተዘዋወሩ ታወቀ።

በትላንትናው ዕለት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተዘዋወሩት ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን፣ ወንድም ሙባሪክ አደም፣ ገጣሚ ሙኒር ሁሴን፣ ተርጓሚ አቡበከር አለሙ፣ ሸህ መከተ ሙሄና ወንድም ካሊድ ኢብራሂም ሲሆኑ የሰባት ዓመት ቅጣት የተላለፈባቸው ኡስታዝ ባህሩ ዑመር፣ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪና ወንድም ሙራድ ሽኩር አሁንም በቂሊንጦ ማረሚያ እንደሚገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በሐምሌ 27 ኢ ፍትሀዊ የቅጣት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ወኪሎቻችን መሀከል ወንድም አብድረዛቅን ጨምሮ 15ቱ በቃሊቲ ማረሚያ የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት ሶስቱ በቂሊንጦ ማረሚያ ይገኛሉ።