ከሳሽ ሲከሰስ : የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ቢኖር ነበር
እኛም እንዲህ ብለን እንከስ ንበር!
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ የቀ/ቁ/ 001/2006 የወ/መ/ቁ. 01/0001/06 ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በመላው ዓለም ከሳሽ ….. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ)
ተከሳሾች… 1/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሽብር ቡድኑ አጠቃላይ አስፈጻሚ 2/ የህውኃት/ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሽብር ቡድኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 3/ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት) የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር 4/ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ የሽብር ቡድኑ አመራር 5/ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ 6/ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል 7/ የኢ.ፌዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚነስቴር የሽብር ቡድኑ የስልጠናና ምልመላ ክንፍ 8/የኢ.ፌዲሪ. የፍትህ ሚኒስቴር የሽብር ቡድኑ የህግ ሽፋን ሰጭ ክፍል 9/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የሽብር ቡድኑ ተባባሪ 10/ የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስ የሽብር ቡድኑ ተቀዳሚ ተባባሪና ኃይማኖታዊ ሽፋን ሰጭ ተቋም 11/የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) የሽብር ቡድኑ ቶርቸርና ማወጣጫ (inquisition) ክፍል 12/ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል ሃላፊና አመራር 13/ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የሽብር ቡድኑ የስልጠናና ምልመላ ክፍል ሃላፊና አመራር 14/ አቶ ጸጋዬ በርሄ የሽብር ቡድኑ የፀጥታ ክፍል ሃላፊና አመራር 15/ አቶ ሬድዋን ሁሴን የሽብር ቡድኑ ቃል-አቀባይ 16/ አቶ አህመዲን አብዱላሂ ጨሎ የሽብር ቡድኑ ተቀዳሚ ተባባሪና የኃይማኖታዊ ሽፋን ሰጭ ተቋሙ አመራር 17/ ፕሮፌሰር ሃጋይ ኤርሊኽ (በሌሉበት) የሽብር ቡድኑ ዋና አማካሪ 18/ ዶ/ር ሰሚር አል-ሪፋዒ (በሌሉበት) የሽብር ቡድኑ አማካሪና የአይዲዮሎጂ ክፍል ተጠሪ 19/ ፔትራም ኃ/የተወ/የግል ማህበር የሽብር ቡድኑ የፋይናንስ ድጋፍ ሰጭ ክንፍ 20/ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (አዲስ ዘመን ጋዜጣ) 21/ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት (ኢ.ቲ.ቪ) የሽብር ቡድኑ የድምጽ-ከምስል ስርጭት ክፍል ክፍል ሁለት 1ኛ ክስ (ከ1ኛ እስከ 21ኛ ተከሳሾችን ይመለከታል ወንጀሉ በ1996 የወጣውን የኢ/ፊ/ዲ/ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/(1)(ሀ)(ለ)፣ 38(1) እነ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3፣4፣5፣6፣7፣8፣10፣እና 11 የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ተከሰዋል፡፡
የወንጀሉ ዝርዝር
(ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ቢኖር ነበር እኛም እንዲህ ብለን እንከስ እንበር!)
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001
የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ
የቀ/ቁ/ 001/2006
የወ/መ/ቁ. 01/0001/06
ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ
በመላው ዓለም
ከሳሽ ….. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ)
እዝህ ይጫኑ (https://www.facebook.com/profile.php?id=100000794889003#)
1ኛ ክስ
(ከ1ኛ እስከ 21ኛ ተከሳሾችን ይመለከታል
ወንጀሉ
በ1996 የወጣውን የኢ/ፊ/ዲ/ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/(1)(ሀ)(ለ)፣ 38(1) እነ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3፣4፣5፣6፣7፣8፣10፣እና 11 የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ተከሰዋል፡፡
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋ በመሆን እና የወንጀል አድማ ስምምነት በማድረግ በመላ ሃሳባቸው እና አድራጎታቸው የወንጀል ድርጊቱን እና ወንጀሉ የሚሰጠውን ውጤት ሙሉ በሙሉ በመቀበል እነ የራሳቸው በማድረግ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ——— ከተረጋገጠው የእመነት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸው “አህባሽ” የተሰኘ አክራሪ አስተሳሰብና አስተምህሮት ውጭ በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ የእስልምና አስተሳሰብና አስተምህሮት መኖር የለበትም የሚል ፖለቲካዊ ዓላማ በማንገብ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጉባዔን (መጅሊስን ) ፖለቲካዊ ዓላማን ለማስፈፀም የተቋቋመ ኃይማኖታዊ ተቋም እንዲሆን እቅድና ግብ በማስቀመጥ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 11ን በመቃረን ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ 1987 ጀምሮ ህውኃት /ኢህአዴግ በተሰኘው የሽብር ቡድን በመሠባሰብ የረጅም፣ የመካከለኛ እና የአጭር ጊዜ እቅድ በማውጣት እና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ተከሳሾች “አህባሽ” የተሰኘው አንጃ በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰዋ ሊባኖስ ውስ የሚንቀሳቀስ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው የኃይማኖት ሴክት መሆኑን እያወቁ፣ እንዲሁም የቀድሞውን የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ረፊቀስ ሀሪሪን ግድያ የሚያጣራው የተባበሩት መንግስት የወንጀል አጣሪ ቡድን “አህባሽ” የተሰኘው አንጃ ግድያውን እንደፈፀመ ሪፖርት ያወጣ መሆኑን እያወቁ፤ የአህባሽ አንጃ መስራች የሆኑት ሽህ ዐብደላህ አልሃረሪ ሀረር የሶማሊ አካል ነች የሚል ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው መሆኑን እያወቁና ይህንን አቋም የሚገልፀውን መጽሀፍ በመጅሊስ በኩል እያሰራጩ፤ ይህንን በሀገር ሰላም ላ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችልን አንጃ ህዝብ የሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ አስመጥተዋል፣ በዚህም ከህዝብና ከሀገር ደህንነት ይልቅ ጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅምን በመምረጥ ስልጣናቸውን ለሽብር ዕቅዳቸው ማስፈፃሚያነት ተጠቅመዋል፡፡
ይህን አክራሪ አስተሳሰብ የተጠናወተው “አህባሽ” የተሰኘውን አንጃ ከ1996 ጀምሮ በጦር-ኃይሎች ሦስት ቁጥር ማዞሪያ በሚገኘው ተቋሙ አክራሪ አስተሳሰቡን እንዲያስፋፋ በህቡዕ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም አልፎ ዕለቱና ወሩ ባልታወቀ 2003 ላይ በቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፊርማ በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ አንድ መቶ ሺህ (100000) ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጣቸውና ለአንጃው ማሰልጠኛ ተቋ ግንባታ ይሆን ዘንድ የፔትራም ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ ዐብዱልከሪም በድሪ እንዲከታተለው ትዕዛዝ ሰጥተዋልል፡ በዚህም ተግባራቸው ህዝብ የሰጣቸው ስልጣን ለሽብር ዕቅዳቸው ማስፈፀሚያ ተጠቅመዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ከሐምሌ ወር 2003 ጀምሮ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይህንኑ “አህባሽ” የተሰኘ አክራሪ አስተሳሰብ እንዲቀበሉ በማስገደድ፣ ማንኛውም ሙስሊም እነርሱ ከሊባኖስ ካስመጡት የአስተሳሰብ መስመር ውጭ መከተል የማይቻል መሆኑን በአደባባይ በመግለፅ እና የእምነት ነፃነታቸውን ለማስከበር የተንቀሳቀሱ የኃይማኖት መምህራን፣ ዑለማዎችና ምሁራንን ለሥነ-ልቦና እነ ለአካል ጉዳት በመዳረግ እስር ውስጥ በማዋል፣ የህገ-መንግስት ጥሰታቸውን በተቃወመው ህዝበ-ሙስሊም ላይ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት አድርሰዋል፡፡
ቀደም ሲል ባቀዱት መሰረትም መጅሊስ (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጉባኤ) ውስጥ ከእነርሱ አክራሪ አስተሳሰብ
ውጭ የሆነ ወይም የሽብር ቡድኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ ግለሰብ በየትኛውም የመጅሊሱ አስተዳደራዊ እርከን እንዳይሳተፍ አግደዋል፡፡ ህዝብ የማያውቃቸውና የኃይማኖትም ይሁን የአካዳ ዕውቀት የሌላቸው ግለሰቦችን የመጅሊሱ አመራር አድርጎ በመሾም ተቋሙ ህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ለሚፈፀመው የሽብር ድርጊት ኃይማኖታዊ ሽፋን እንዲሆን ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህንንም ለማሳካት የመንግስት መዋቅርን በመጠቀም በትጋት ሰርተዋል፡፡ በተለይም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮው ሙሉ ኃይሉን ለዚህ እኩይ ጉዳይ በማዋል በንፁሃን ዜጎች ላይ የእስር፣ የእገታ፣ የድብደባና የግድ ወንጀል ፈፅሟል፡፡ መጅሊሱን ለሽብር ዓላማቸው ማስፈፀሚያነት ለማመቻቸት ይችሉ ዘንድ ህዝበ-ሙስሊሙ ባልተሳተፈበትና የህዝበ-ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በፌ/ወ/ምርመራ (ማዕከላዊ) ኢ-ሰብዓዊ ግፍ እየተፈፀመባቸው (እፈፀሙባቸው) ባሉበት ሁኔት ህገ-ወጥ ምርጫ- የመንግስት ተቋም በሆነው ቀበሌ ውስጥ-አካሂደዋል፡፡ በሂደቱም ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮችን በሌላ ህገ-ወጥ አመራሮች ተክተዋል፡፡ በዚህም የሽብር ቡድኑ ተሳታፊዎች በኃይማኖት ጉዳይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነታቸውን አሳይተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ የሀገሪቱን መንግስታዊ ተቋማት በመጠቀምና የሀገሪቱን የፀጥታ ኃይል ሙሉ በሙሉ ለህገ- ወጥ ዓላማቸው በማዋል በ “ህገ-መንግስት ማስተማር” ስም አዲሱን አክራሪ አስተሳሰብ በኃይል ጭነዋልል፡ የግዳጅ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ስልጠናቸውን ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑና የፀጥታ ኃይላት ማስፈራሪያና ዛቻ ያልበገራቸው የመስጅድ ኢማሞች ከኢማምነታቸው (ከስግደት መሪነታቸው አባርረዋል፡፡ በኃይማኖት ጉዳይ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት የመስጅድ ኢማሞችን ሾመዋል፤ እነርሱ የሾመዋቸውን ኢማሞች “ተከትለን አንሰግድም” ያሉ በርካታ ሙስሊሞችን ዘብጥያ ወርውረዋል፣ ለህገ-ወጥ ድርጊታቸው ማስፈፀሚያ ያቋቋሟቸውን ፍ/ቤቶች በመጠቀም በ “ዋስትና” ስም በርካታ ሚሊዬን ብር ከህዝበ-ሙስሊሙ መዝብረዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀገራቸው ሙስሊም ሆነው የመኖር ነፃነታቸውን ነፍገዋል፡፡
የሽብር ቡድኑን ህገ-ወጥ ድርጊት በመቃወም ህገ-መንግስት ይከበር! የሚል ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን “ጥቂቶች” ሲሉ አሸማቀዋል፤ የነፃነት ጩኸታቸውን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ያደረሱላቸውና ለመብት ጥያቄያቸው መፍትሄ ያፈላልጉላቸው ዘንድ በፊርማቸው አረጋግጠው ውክልናቸውን የቸሯቸውን የህዝብ ልጆች የሽብር ቡድኑ ራሱ በሚፈፅመውና ግዙፍ የወንጀል ድርጊት በሆነው በሽብር በመወንጀል አሰቃቂ ግፍ ፈፅመዋል፡፡ ይህንኑ የሽብር ዕቅዳቸው አካል የሆነውን ህገ-ወጥ ተግባር የህግ ሽፋን ለመስጠት የኢ/ፌ/ዲ/ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የተሰኘ ክፍላቸውን በመጠቀም የህዝብ ወኪሎችን ከሃያ ወራት ያላነሰ በእስር ቤት አጉረዋል፡፡ በተጨማሪም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን “በሁከትና በብጥበጥ” በመወንጀል ተመሳሳይ ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ መረጃ ለህዝብ እንዳይደርስ ለማገድ በማሰብ በሙስሊሙ ህ/ሰብ ጉዳይ ላይ በማጠንጠን የሚዘግቡ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን አግደዋል፤ አዝዘግተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ አባስት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን በተለያ ስያሚዎች በመከፋፈል፣ አክራሪ አስተሳሰባቸውን በኃይል በመጫን፣ ይህንን ህገ-ወጥ ተግባራቸውን በተቃውሙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፤ በርካታ የኃይማኖት መምህራንና ምሁራን ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርገዋል፡፡ ህዝብ የሰጣቸውን ስልጣን ህዝብን ለማሸበር ተጠቅመዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በኮፈሌ፣ በአሳሳ፣ በሀረር፣ በሀርጉ፣ በደጋን፣ በአዲስ አበባ አወሊያ መስጂድ፣ በአንዋር መስጅድና በአዲስ አበባ ስቴድዮም በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡ጰ፡
ተከሳሾች የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በማሰብ አክራሪ አስተሳሰባቸውን የማቃባሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን በኢኮኖሚ ለማዳከም የተለያዩ እቅዶችን ነድፈው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ብልጽግና የሚጨበጥ ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችላቸውን ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋም እንዳይችሉ ከልክለዋል፡፡ ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋም የሚፈቅድ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ አመራሮች በሰጡት ቀጭን ትዕዛዝ ከ6800 (ስድስት ሺህ ስምንት መቶ) አባላት በላይ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ያቀፈውን ዘምዘም ባንክ በብሔራዊ ባንክ ፕሬዝዳንት ፊርማ አዋጁን በመጣስ በኃይል በትነዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያላቸውን የትምህርት ተሳትፎ ለማቀጨጭ በማቀድ ሆን ብለው ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚቃረንና የእምነት ነፃነትን የሚጋፋ አግላይ ደንብ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በማውጣት ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል፡፡ ይህንኑ ህገ-ወጥ ደንብ የተቃወሙ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አንድም ለእስራት አሊያም ከትምህርት ገበታ ለመገለል እንዲደረጉ አድርገዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ዓላማውን ለማስፈፀም ባቋቋማቸው የመገና ብዙሃን የሽብር ቅስቀሳ አድርጓል፡፡ አባላቱ መረጃን አዛብቶ በማቅረብ የጠወሰነን የህበረተሰብ ክፍል በተወሰነው ላይ የማነሳሳት ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ ህዝበ-ሙስሊሙ ያነሳቸውን የእምነት ነፃነት ጥያቄዎች በመቀልበስ ሙስም ላልሆኑ ወገኖቹ ስጋት እንደሆነ አድርገው በመሳል ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህም ድርጊታቸው ለዘመናት ተከባብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ለማስገባት በማስብ ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ቀስቃሽ የመገናኛ ብዙሃናቸውን በመጠቀም በእስር ላይ ያሉ ንፁሃን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና የኃይማኖት መምህራንን በ “ሽብር” በመፈረጅ “ጅሃዳዊ ሀረካት” የተሰኘ ከእውነት የራቀና የተቀነባበረ ዘጋቢ ፊልም በማሰራቸት ህዝብን በህዝብ ላይ አነሳስተዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ አባላት በደሴ ከተማ በሸህ ኑሩ ኢማም ላይ ግድያ በመፈፀም የመገናኛ ብዙሃናቸውን በመጠቀም የህዝበ-ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ ለማጠልሸት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የተዛባ መረጃ በመስጠትና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ያደራጇቸውን ዜጎች በጥቅም በመደለል አሊያም በማስፈራራት በመላ ሀገሪቱ የሀሰት የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረግ ህዝብን ለማታለል ሞክረዋል፡፡ በግድያው ማግስትም በርካታ ንፁሃን ሙስሊሞችን ለእስር በመዳረግ በሽብር ወንጅለዋል፡፡
በአጠቃላይ ተከሳሾች የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በማቀድ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እነርሱ ከመረጡት አክራሪ አስተሳሰብና አይዲዮሎጂ ውች ያለን ለማጥፋት በመንቀሳቀሳቸው፣ የተወሰነን የህብረተሰብ ክፍል በማስፈራራታቸው በህይወት፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው፣ እገታ በመፈጸማቸው፣ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም በማቀዳቸው፣ በመዘጋጀታቸው፣ በማሴራቸው፣ በማነሳሳታቸው እና በመፈፀማቸው በግዙፍ የወንጀል ድርጊት ተከሰዋል፡፡
ከሳሽ ሲከሰስ
የሽብር ቡድኑ አባላት የወንጀል ተሳትፎ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡-
1ኛ. ተከሳሽ – የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት
የሽብር ቡድኑን እቅድና ዓላማ ለማስፈፀም በመዋቅሩ ተዋረድ ያሉ መስሪያ ቤቶች እንዲንቀሳቀሱ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ የሚፈፅማቸውን የሽብር ድርጊቶች ህጋዊና ትክክለኛ ለማስመሰል የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት እንደ ሽፋን ተጠቅሟል፡፡ ለዚህም ከ8ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ንፁሃንን ለእስርና ለኢ-ሰብዓዊ ግፍ ከመዳረጉም በተጨማሪ በሺዎች ከሚቆጠሩ ሙስሊሞች በዋስትና ማስጠበቂያ ስም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር መዝብሯል፡፡ ለሽብር ዓላማው መደለያ ይሆን ዘንድ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ለ2005 የበጀት ዓት ብቻ 350,000,000.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር) በመመደብ ተንቀሳቅሷል፡፡ ለሽብር ዓላማው የሚገለገልባቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት (ኢቲቪ) እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን (አዲስ ዘመን ጋዜጣን) በመጠቀም የሀሰት መረጃ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ህዝበ-ሙስሊሙን ሙስሊም ካልሆነው ወገኑ ጋር ለማጋጨት ተንቀሳቅሷል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን የሽብር ድርጊት በፊታውራሪነት የመራና ያስፈፀመ በመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት በፈፀመው የሽብር ድርጊትን ማቀድ፣ ማሴርና መፈፀም ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3 እና 4 የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡
2ኛ. ተከሳሽ የህውኃት/ ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ
የሽብር ቡድኑ ስራ-አስፈፃሚ በመሆን ሰርቷል፡፡ የሽብር ድርጊቱን በማቀድ፣ በማሴር እና አመራር በመስጠት ተሳትፏል፡፡ ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ 1996 ዓ.ል ጀምሮ በሽብር ድርጊቱ ዙሪያ በህቡዕ በመወያትና የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ በማውጣት የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን መሪ ድርጅት የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስን) የፖለቲካዊ ግባቸው ማስፈፀሚያ ኃይማኖታዊ ተቋም እንዲሆን ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በህገ-መንግስት አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 የተደነገገውን የእምነት ነፃነት በመቃረን በእምነት ተቋና በኃይማኖት ጉዳይ በቀጥታ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት በተቃወሙ ንፁሃን ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ የሽብር ድርጊት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ስለሆነም ለሽብር ድርጊት በማሴር፣ በማቀድና አመራር በመስጠት ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 እና አንቀጽ 7(2) የተመለከተውን በመተላለፋቸው ተከሰዋል፡፡
3ኛ. ተከሳሽ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት)
የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር በመሆን ሰርተዋል፡፡ የሽብር ድርጊቱን በማሴር፣ በማቀድና አመራር በመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ከ17ኛ ተከሳሽ ሃጋይ ኤርሊኽ የተሰጣቸውን ምክር ከልብ በመቀበል ያላቸውን የግል ክህሎት በማከል የሽብር ቡድኑን ዓላማ በመቅረፅ የቡድኑን ጥንስስ ጥለዋል፡፡ በሚያዚያ 9/2004 ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ለመከፋፈል ሞክረዋል፡፡ የሽብር ዘመቻው ለመጀመር የነበራቸውን እቅድ የመብት ጥያቄ ያነሳውን ህዝበ-ሙስሊም “ጥቂቶች” በማለት ከማሸማቀቅ አልፈው “በእንጩጩ ማስቀረት” ሲሉ ዝተዋል፤ አስፈራርተዋል፡፡ ይህንኑ የፓርላማ ንግግራቸውን ተከትሎ 5ኛ ተከሳሽ የፌ/ፖሊስ ኮሚሽን በሚያዚያ 2004 በአሳሳ ከተማ በንፁሃን ሙስሊሞች ላይ የህይወትና የአካል ጉዳት አድርሷል፡፡ ምንም እንኳን የሽብር ድርጊቱን ከመፈፀማቸው በፊት እርሳቸው ራሳቸው በእንጩጩ የቀሩ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ በእርሳቸው የተዘረጋለትን የአፈፃፀም እቅድ በመከተል ከፍተኛ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት አድርሷል፡፡ ግለሰቡ በአዋጅ የፀደቀውን የወለድ ነፃ ባንክ የመመስረት መብትን በመንጠቅ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችና በክርስቲያን ወንድሞቻቸውም ተሳትፎ የተቋቋመውን “ዘምዘም ባንክ” እንዲበተን ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመስጠት በትነዋል፡፡ በዚህም የሽብር ቡድኑ ዓላማ አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማኮሰስን ለማሳካት በማሰብ አዋጅን በመመሪያ ጥሰዋል፡፡ ግለሰቡ በ2004 ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በተፃፈ ደብዳቤ ለአህባሽ ማሰልጠኛ ተቋም ግንባታ የሚውል በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ 100ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጥ በፊርማቸው አዘዋል፡፡ በዚህም የህዝብ ስልጣንን ለራሳቸው የሽብር ዓላማ ማሳኪያ ተጠቅመዋል፡፡ ስለሆነም ግለሰቡ የሽብር ድርጊትን በማቀድ፣ በማሴር፣ በማነሳሳትና በመፈፀም ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 እና 7(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል በሌሉበት ተከሰዋል፡፡
4ኛ ተከሳሽ -ጠ/ሚኒስቴር ኃ/ማርያም ደሳለኝ
ተከሳሽ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን (3ኛ ተከሳሽን) የእግር ኮቴ ያለምንም መጨመርና መቀነስ በመከተል የሽብር ቡድኑን መርተዋል፡፡ የሽብር ድርጊቱን የተቃውሙ ሙስሊሞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ- 21ኛ ተከሳሽ እና በአልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ህዝበ-ሙስሊሙን “ጥቂቶች” ሲሉ አሸማቀዋል፡፡ ለሚፈፀሙ የሽብር ድርጊቶች ሁሉ አመራር ሰጥተዋል ባባልም የሀገሪቱ የበላይ አመራር ከመሆናቸው አንፃር በይሁንታ በማለፍ በቀጥታ አመራር የመስጠት ያህል ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ስለሆነም ሀገሪቱ ውስጥ የተፈፀሙ የሽብር ድርጊቶችን በሙሉ በማቀድ፣ በመፈፀምና አመራር በመስጠት ወንጀል የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 2 እና 7(2)ን በመተላለፍ ወንጀል ተከሰዋል፡፡
5ኛ. ተከሳሽ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ በመሆን በዜጎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሷል፡፡ በሚያዚያ 2004 በአሳሳ፣ በሀምሌ 2005 በኮፈሌ፣ ቀኑና ወሩ ባልታወቀ በ2005 በሀርቡ፣ በ2004 በሀረር፣ በሀምሌ 06/2004 በአወሊያ መስጅድ፣ በሐምሌ 14/2004 በአንዋር መስጅድ እና በሐምሌ 2005 በአዲስ አበባ ስቴዲዮም ዙሪያ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ የህይወት፣ የአካልና የንብረት አሰቃቂ ጉዳት አድርሷል፡፡ በሐምሌ 06/2004 በሌሊት አወሊያ መስጅድ ውስጥ ለምፅዋት የሚሆን ምግብ ሲያዘጋጁ የነበሩ ሙስሊሞች ላ እገታ በማድረግ፣ በተዘጋ መስጅድ ውስጥ ባሉ ሙስሊሞች ላይ አስለቃሽ ጥይት ወደ ውስጥ በመተኮስ በህዝብ ጤና ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ በሐምሌ 2005 የዒድ አልፊጥር ባዕልን ለማክበር በአዲስ አበባ ስቴዲዮም በመገኘት የ1ኛ ተከሳሽን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስትን በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብነት በመቃወማቸው በሺህዎች በሚቆጠሩ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ድብደባ እና እስር ፈፅሟል፡፡ በዕለቱ ከአስር ሺህ በላይ ሙስሊሞችን ለእስርና እንግልት ዳርጓል፡፡ በመሆኑም ከ2ኛ ተከሳሽ ህውኃት/ኢህአዴግ በተሰጠው አመራር የሽብር ድርጊቱን በቀጥታ የፈፀመ በመሆኑ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(4) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡
6ኛ. ተከሳሽ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ
የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል በመሆን ለቡድኑ አመራሮች ሀሰተኛ መረጃን በመስጠት የሽብር ድርጊቱን አቀጣጥሏል፡፡ የሽብር ቡድኑ አመራሮችን ከጀርባ ሆኖ በመምራት ሆን ብሎ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ሽብር እንዲፈፀም አበረታቷል፡፡ የተለያዩ በህቡዕ የተፈፀሙ ግድያዎችን አሲሯል፣ አቀነባብሯል፣ ፈፅሟ፡፡ በ2005 በደሴው ሸህ ኑሩ ኢማም ላይ የተቀነባበረ ግድያ ፈፅሟል፡፡ ይህን በማድረግም የህዝበ-ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ ለማኮላሸት ንፁሃንን አስሯል፤ በሀሰት የከሰሳቸውን ዜጎች ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች “ህገ-መንግስት ይከበር” እንቅስቃሴ ጋር ለማዛመድ ጥረት አድርጓል፡፡ ቢሮው ከ5ኛ ተከሳሽ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ዜጎችን የማገት፣ የማሰር፣ ቶርች የማድረግና የመግደል ወንጀል ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም ቢሮው በሐምሌ 08/2004 በተወሰኑ የህዝበ-ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የመኪና እገታና ጠለፋ ሙከራ አድርገዋል፡፡ በሀሰት በተወነጀሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴና በተለያዩ ምድብ ችሎት በቀረቡ ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ ከ11ኛ ተከሳሽ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ጋር በመሆን ለሽብር ድርጊታቸው የሚሆኑ የሀሰት ምስክሮችን በማባበል አሊያም በማስፈራራት አዘጋጅተዋል፡፡ ስለሆነም የሽብር ድርጊት ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን እና ምስክር በማባባል ወይም በማስፈራራት ወይም ማስረጃ በማጥፋት ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(3)(4) እና 10(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡
…ይቀጥላል…