ህወሓት መራሹ መንግስት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ወደ ዝዋይና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች ሊያዛውራቸው ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ህወሓት መራሹ መንግስት የሚሊዬኖች ወኪሎች የሆኑት ውድ የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ወደ ዝዋይና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች ሊያዛውራቸው ነው::


በአሁኑ ሰዓት ለመንግስት መዋቅር ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለ BBN RADIO በላኩት መግለጫ እንዳስታወቁት ህወሓት መራሹ መንግስት ውድ የህዝበ ሙስሊሙን ወኪሎች ያስተላለፈባቸው የተገመደለ ፍርድ አልበቃው ብሎት ተጨማሪ በደል ለመፈፀም ሆን ብሎ በማቀድ ንፁሃኖቹን ከቤተሰብና፣ ከልጆቻቸው በማራቅ ስነ ልቦናዊ ጉዳት በእነሱም ሆነ በቤተሰቦቻቸው ላይ ይደርስባቸው ዘንድ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙት የዝዋይና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች ለማዛወር ተዘጋጅቷል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ከወኪሎቻችን የተዛባ ፍርድ ቡሃላም በህዋት ደህንነቶችና ባለ ስልጣናት እንዲሁም ሌሎች የክልል ፕሬዝዳንት ተብየ የሥርዓቱ አገልጋይ ባለስልጣናት መካከል የእርስ በእርስ ትርምስ እና ከፍተኛ አለመግባባት እንደተፈጠረ የታወቀ ሲሆን ህወሃቶች በቀጣዬቹ ግዜያቶች የሥርዓቱ ታማኝና ታዋቂ ግለሰቦች ላይ በተደራጀና በረቀቀ ስልት ግድያ በመፈፀም ” አሸባሪዎች” ፈፀሙት በማለት በህዝብ ሙስሊሙ ላይ ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመፈፀም እቅድ መያዙን ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው የ BBN RADIO ምንጮች አሁን ባደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።
አድማጮቻችን ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከታማኝ ምንጮቻችን የሚደርሱንን መረጃዎች እየተከታተልን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ መሆናችንን ለመግለፅ እንወዳለን ።


BBN RADIO