እውነታዎች ስለ አሜሪካው ፕሬዚደንታዊ አውሮፕላን ‘ኤር ፎርስ ዋን’
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
1. ‘ኤር ፎርስ ዋን’ የአውሮፕላን ስም አይደለም #Ethiopia
ኤር ፎርስ ዋን የአንድ አውሮፕላን ብቻ መጠሪያ አይደለም። ማንኛውም ፕሬዚደንቱን እያጓጓዘ ያለ አውሮፕላን ይህ መጠሪያ ስም ይሰጠዋል። ይህ መጠሪያ የሬዲዮ ሞገድ ወይም ጥሪ መለያ ኮድ ሲሆን በዚህ መሰየም ያስፈልገውም በአንድ ቦታ እየበረሩ ካሉ ሌሎች በረራዎች ጋር ሊፈጠር የሚችልን መቀላቀል ለማስወገድ ነው። በዚሁ መሰረት ፕሬዚደንቱን የጫነ ማንኛውም ወታደራዊ አውሮፕላን አርሚ ዋን እንዲሁም የፕሬዚደንቱ ሄሊኮፕተር ማሪን ዋን ይባላሉ።
2. ኤር ፎርስ ዋን መንታ አውሮፕላን ናቸው
ፕሬዚደንቱ በመደበኛነት ለእሱ ለግሉ እንዲሆን ተደርጎ ከተሰሩት ከሁለት አንዱ ይጠቀማል። ሁለቱም እጅግ አንድ አይነት እና የ 6 ፎቅ ያክል ቁመት አላቸው።
3. ቋሚ እና ኦፊሴላዊ የሐገሪቱ እና የፕሪዚደንቷ መለያ ነው
አውሮፕላኑ የፕሬዚደንቱ ዋነኛ እንዲሆን ተብሎ ዲዛይን የተደረገ ነው። በሄደበት ሁሉ መኖሩ እንዲያስታውቅ እና ተፅዕኖ እርግጥ እንዲሆን ይፈለጋል። ምልክቶቹም ‘United States of America’ የሚሉት ቃላት፣ የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ እና የፕሬዚደንቱ ማህተም ናቸው።
4. ያለጊዜ ገደብ ላይ ያለእረፍት መብረር ይችላል
ያለምንም ማቆም ፕሬዚደንቱን ይዞ በአየር ላይ ላልተወሰነ ጊዜ መብረር ይችላል። ጥያቄው “ነዳጅ አይጨርስም ወይ?” ነው ሌሎች ነዳጅ የተሸከሙ አውሮፕላኖች ባለበት ደርሰው ነዳጅ ሞልተውለት ይመለሳሉ። በአንድ ጊዜ 203,000 ሊትር ነዳጅ ጭኖ በሙሉ አቅሙ ሲጓዝ 377,000 ኪ.ግ ይመዝናል። በዚህም የዓለምን ዙሪያ ገማሽ ያህል መብረር ይችላል።
5. በራሪው ኋይት ሃውስ ይባላል
በአውሮፕላኑ ውስጥ ያሉ ኤሌክትሮኒክ እቃዎች በሙሉ ኤሌክትሮማግኔቲክ ምቶችን ይቋቋማሉ፤ የጠላት ራዳርን ጃም ለማድረግ ኤሌክትሮኒካዊ አጸፋ መመለሻ ስለተገጠመለት ማንም አካል የበረራ መስመሩ ማወቅ አይችልም፤ 85 ስልኮች፣ ባለሁለት ወገን የራዲዮ ስብስቦች አሉት፤ የጠላትን የሚሳኤል ጥቃት አሳሳች የእሳት ወይም የሙቀት አቅጣጫ በማሳየት እና በማምከን መከላከል ይችላል፤ ፕሬዚደንቱ በረራ ላይ እያለ ዩናይትድ ስቴስ ላይ ጥቃት ቢፈጸም፣ እዛው በረራ ላይ እያለ ወታደራዊ ትእዛዝ መስጠት የሚያስችል የተሟላ እና የረቀቀ የትዕዛዝ ማዕከል አለው። በነዚህ በተጠቀሱት ምክንያቶች በራሪው ኋይት ሃውስ አሰኝተውታል።
6. ተንቀሳቃሹ ባንከር እና እጅግ ደኀንነቱ የተጠበቀ መጓጓዣ
በ ሴፕቴምበር 11 2001 የሽብር ጥቃት ወቅት በመሬት ላይ የመቆየት ደኅነት ባለመረጋገጡ ፕሬዚደንት ይዞ ለረዥም ሰዓታት አየር ላይ እየተንሳፈፈ በመቆየት ተንቀሳቃሽ ማቆያ መሆኑን አስመስክሮ ነበር። በዚህ የሽብር ወቅት ሁሉም በረራዎች እንዲቆሙ በመደረጉ ይህ አውሮፕላን ፕሬዚደንቱን በአሜሪካ የአየር ክልል ላይ ሲንሳፈፍ የነበረ ብቸኛው በራሪ ግዙፍ አካል ነበር።
7. እጅግ ፈጣን እና በከፍታ በራሪ ወፍ
1,126 ኪ.ሜ በሰዓት እና 45,100 ጫማ ከፍታ ላይ መብረር ይችላል። ይህም በ30,000 ጫማ ከሚበሩ ከሌሎች የንግድ አውሮፕላኖች የተለየ ያደርገዋል።
8. በልዩነት ለፕሬዚደንቱ
አውሮፕላኑ በልዩነት ለፕሬዚደንቱ በቦይንግ፣ በኋይት ሃውስ እና በፕሬዚደንቱ ጠባቂዎች ‘ሲክረት ሰርቪስ’ የጋር ትብብር ዲዛይን የተደረገ ነው። በውስጡ ያሉት 3 ፎቆች 4000 ስኩዌር ፊት ቦታ እንዲኖረው አስችለውታል። ይህም ግዙፍ እና በቴክኖሎጂ የረቀቀ ቢሮውን፣ የኮንፍረንስ ክፍሉን፣ የፕሬዚደንቱን መኖሪያ፣ መኝታ ክፍል፣ መታጠቢያ፣ ጂም መስሪያ፣ አነስተኛ ሆስፒታል እና ዶክተሩን፣ የኦፕሬሽን ወይም ሰርጀሪ ክፍል፣ በአንድ ጊዜ መቶ ሰው መመገብ የሚችል የምግብ ማብሰያ ያካትታል። በተጨማሪም ወቅት ከፕሬዚደንቱ ጋር የሚጓዙ የኋይት ሃውስ ሰራተኞች፣ ከፍተኛ አማካሪዎች፣ የሲክረት ሰርቪስ ተጓዥ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እንግዶችን በበቂ ሁኔታ መያዝ እና ማስተናገድ ይችላል።
9. ምንጊዜም በፕሬዚደንታዊው ሊሞዚን አቀባበል ይደረግለታል
ፕሬዚደንቱ ወደ ሩቅ ቦታዎች ሲጓዝ ይህን ተከትሎ የሚያስፈልጉ ነገሮችን የሚያሟሉ የካርጎ አውሮፕላሮች አሉ። በብዛትም እኚህ አውሮፕላኖች ቀድመው መገልገያ እቃዎችን የሚያደርሱ እና በጉዞ ወቅት ኤር ፎርስ ዋንን የሚያጅቡ ናቸው። ኤር ፎርስ ዋን ከበረራው እንዳረፈ አስቀድሞ በካርጎ የተላከው ሊሞዚን ፕሬዚደንቱን ይቀበለዋል።
10. እጅግ ሚስጥራዊ ነው
ማንም ሰው ቢሆን፣ ከፍተኛ የፖለቲካው ሰዎችን ጨምሮ አውሮፕላኑን እንዲጎበኝ እንኳ አይፈቀድም። አነስተኛ የሚባለውም የአውሮፕላኑ ጉዳይም ቢሆን በከፍተኛ ሚስጥር የተጠበቀ ነው።
11. የኒኩሌር ፍንዳታ ሞገድ የማያቆመው የግንኙነት መስመር
ፕሬዚደንቱ እና ሰራተኞቹ በአስር ሺህ ጫማዎች ከፍታ ላይ እየተጓዙ ካሻቸው ሰው ጋር መገናኘት የሚችሉበት የመገናኛ ቴክኖሎጂ በአውሮፕላኑ ውስጥ ይገኛል። የገመዶቹም ርዝመት እስከ 238 ማይል የሚደርስ እና ሽፋናቸውም በኒኩሌር ፍንዳታ እንኳ ሊደርስ ከሚችል የኤሌክትሮማግኔቲክ ምትን የሚቋቋሙ ናቸው።
12. አንደኛ ደረጃ አገልግሎት
ኤር ፎርስ ዋን በምቾት 70 መንገደኞችን 26 የበረራ ስራ አባላትን ማስተናገድ ይችላል። እነዚሁ አባላት በጥንቃቄ የተመረጡ የጦር አባላት ወይም ወታደሮች ሲሆኑ በቂ አገልግሎት ያበረከቱ መሆን ይኖርባቸዋል። የፕሬዚደንቱን ምግብ የሚያዘጋጁት በከፍተኛ ጥበቃ እና ደህንነት ነው። ለምሳሌ ምግብ የሚገዙት በድንገት፣ ከበረራው ጥቂት ጊዜ በፊት፣ እንዲሁ ካልታወቀ ከማንኛውም ገበያ ቦታ፣ ለማን እንደሆነ ሳይነገር ነው። ይህም ፕሬዚደንቱን ሆነ ተብሎ ሊፈጸም ከሚችል የመመረዝ አደጋ ለመከላከል ነው።
13. ማንኛውም የፕሬዚደንቱ በረራ የሚታየው እንደወታደርዊ ተልዕኮ ነው
የኤር ፎርስ ዋን የፕሬዚደንቱ በረራ የሚታየው እንደወታደርዊ ተልዕኮ ነው። የኤር ፎርስ አባላት አስፈላጊውን ቅድመ በረራ ጥንቃቄ እና ዝግጅት ያደርጋሉ። ለበረራ ዝግጁ ሲሆን ማሪን ዋን ሄሊ ኮፕተር ፕሬዚደንቱን ከኋይት ሃውስ መግቢያ በር ላይ አሳፍሮ አንድሪውስ ኤር ፎርስ ቤዝ ያደርሰዋል። በአውሮፕላን ጣቢያው አካባቢም አባላቱ ማንኛውም ያልተፈቀደለት በራሪ አውሮፕላን በአየር ላይ አለመኖሩን በንቃት ይከታተላሉ። ከተገኘም ተመትቶ እንዲወርድ ወይም እንዲወገድ የማድረግ ፍቃድ አላቸው።
ምንጭ: www.southreport.com