የስርአቱ ታማኝ ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ተባረሩ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Journalists

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኦባማን ከናይሮቢ መንቀሳቀስ ተከትሎ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ተኮልኩለው የነበር የስርአቱ ታማኝ ጋዜጠኞች እቃችሁን ልንፈትሽ ነው ከተባሉ በኋላ ደጅ ራቅ ብለው እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ መግባት እንደተከለከሉ ተናግረዋል::

እናንተ በሌላቹበት እቃችሁን መፈተሽ እንፈልጋለን ከተባሉ በኋላ የወያኔ ደህንነቶች ፈትሸው ቢጨርሱም ጋዜጠኞቹን መግባት አትችሉም እቃችሁንም ማንሳት አትችሉም አስፈላጊዉም መረጃ ፎቶ እና ቭድዮ ከመንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ ታገኛላቹ በማለት ንብረቶቻችንን በዝናብ እያስመቱብን ይገኛሉ በማለት አማረዋል::ጋዜጠኞቹ ወደ ባላስልጣኖች እየደወሉ በመማጸን ላይ ናቸው::

ጋዜጠኞቹ ከቦታው እንዲለቁ ያደረጉት የአሜሪካ የጸጥታ እና የደህንነት ሃይሎች ሲሆኑ የወያኔ ባለስልጣናት ጉዳዩን በማስረዳት ጋዜጠኞቹን ወደ ቦታቸው እንዲመልሱ ያደረጉት ሙከራ ባይሳካም እስካሁን ሂደት ላይ ነው::የአሜሪካ የጸጥታ ሃይሎች ሙሉ ኤርፖርቱን ተቆጣጥረውታል::

AA airport  for Obama