ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው:: – በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው::-በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)-የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማስታጠቅ እና በማደራጀት ዙሪያ በደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስባቸው መሆኑ ተሰምቷል::በመጭው ሳምንት የሚሰበሰቡ እና በስብሰባው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪው የቀረበላቸው የኤርትራ የፖለቲካ ድርጅቶች:-
1 Eritrean People Congress,
2 Democratic Front for Eritrea Unity,
3 Eritrea Liberation Front,
4 Eritrea Democratic Party,
5 Eritrean Democratic Movement ,
6 Eritrean Nahda Party,
7 Eritrean Islamic Party for Development & Justice,
8 Red Sea Afar Democratic Organization,
9 Eritrean Islamic Congress”……….ናቸው:: እነዚህ ድርጅቶችን ወያኔ በራሱ ሰው ሃይል አዋቅሮ በማስታጠቅ እና በማደራጀት ፊት ለፊት አስቀድሞ የሻእቢያን መንግስት የመገርሰስ ሕልሙን የሚያሳካበት ስብሰባ መሆኑ ተጠቁሟል::ሻእቢያ በኤርትራ ምድር ላይ የወያኔን መንግስት ልመጣል የሚታገሉ ድርጅቶችን በማደራጀት እና በማስታጠቅ እየረዳ እንደሚገኝ ይታወቃል::ወያኔ እንዲሁ በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ ቀደም ሲረዳቸው የነበሩ ድርጅቶችን አሁን በመሳሪያ ለማስታጠቅ እንዳሰብ ታውቋል::ባለፈው ወር በጎንደር ተሰብስበው የነበሩ ድርጅቶች እርስ በርስ አለመግባባት እንደታየባቸው ሲነገር ሰንብቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ኢትዮጵያ የኦባማ መምጣት ከተሰማ በኋላ በወያኔ እና አልሸባብ ሰራዊቶች መካከል ጦርነቱ ታጋግሎ መቀጠሉ የኦባማ እና የባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ እና ሽብርን እየተዋጋን ነው በሚል የማጭበርበሪያ ስልት መሆኑ ታውቋል::በወያኔ ትንኮሳ የተነሳው ጦርነት እስካሁን ያልበረደ ሲሆን የውስጥ ጉዳዮችን እና ውጥረቶችን በመሸፋፈን ሽብርን እየተዋጋሁ ነው በሚል ሰበብ ከአሜሪካ ከፍተኛ ድጋፍን እና የገንዘብ እርዳታን ለማግኘት የሚደረግ መራወጥ መሆኑ ተጠቁሟል::ይህ የኦባማን እና የባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ የተጀመረው ጦርነት ከኦባማ ጉብኝት በኋላ እንደሚቆም ምንጮቹ ገልጸዋል::ጦርነቱ ምንም የማይፈይድ እና ወታደሮችን ከመገበር ውጪ አዋጪ ያልሆነ የባለስልጣናት ኪስ በአሜሪካ ዶላሮች የሞሞላ መሆኑ ታዛቢዎች ይናገራሉ::#ምንሊክሳልሳዊ