አሁንም አልሸባብ! – ጌታቸው ሽፈራው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ምርጫ 97 ላይ ድምፅ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ የተያዘው፣ ከዛም የሌባ አይነ ደረቅ ሆኖ እኔ ነኝ አሸናፊ ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ የተቀየመውን ህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ አንዳች ዘመቻ ያስፈልገው ነበር፡፡ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ሶማሊያ ውስጥ ቡራከረዩ ሲል የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ለህወሓት/ኢህአዴግ ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት፡፡ ‹‹ድንበርክን ጠብቅ›› ተብሎ ቢመከር አልሰማም፡፡ አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግስታትና ሌሎችም ጥለውት የወጡት ሶማሊያ ውስጥ ዘሎ ገባ፡፡ ለጊዜው በምስኪን ኢትዮጵያውያን ደም የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት የተበታነ መሰለ፡፡ ግን ደግሞ የውጭ ወረራ ከምንም በላይ የሚያበረታቸው ሶማሊያዎች ‹‹ጠላት ኢትዮጵያ ወረረችን›› ብለው ወጣቱን አነቃነቁ፡፡ አልሸባብ ወይንም ‹‹ወጣቶቹ›› አዲስ ሀይል ሆነው መጡ፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ ዘሎ ገብነት ምክንያት በምስራቅ አፍሪካ አዲስ አሸባሪ ተፈጠረ፡፡

ከብአዴን፣ ኦህዴድ….እስከ ትግስቱ አወሉው አንድነት ኢህአዴግ ቡድኖችን ፈጥሯል፡፡ እነዚህ ሁሉ ታዛዦች ናቸው፡፡ አልሸባብ ግን ህወሓት/ኢህአዴግ ከፈጠራቸው ቡድኖች መካከል አደገኛው ነው፡፡ በእርግጥ ለእሱ የዶላር ምንጭ ነው፡፡ ከእነ ቴሌ ቀጥሎ ሌላ በኢትዮጵያውያን ደም ዶላር የሚታለብ ላም፡፡ ወደ ሶማሊያ ከገባበት 2006 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ዶላር ይዝቅባታል፡፡ በኢትዮጵያውያን ደም!

እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን አልቀዋል፡፡ ከሁለት አመት በኋላ ደግሞ ‹‹ተው!›› እየተባለ አልሰማ ብሎ የፈጠረውን አልሸባብን አልችል ብሎ በበቃኝ ከሶማሊያ ቅሌቱን ተከናንቦ፣ ኢትዮጵያውያንን አስፈጅቶ ወጣ፡፡ ዶላር ተፈለገና ከወጣ ከሁለት አመት በኋላ እንደገና ገባ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አልሸባብን ጠራርገን አስወጣን ሲሉን ቆይተዋል፡፡ አልሸባብ ግን አሁንም አለ፡፡ አሁን ኦባማ ሲመጣ እንኳን በጦር ጀት እያባረርነው ነው፣ በታንክ መግቢያ መውጪያ እየነሳነው ነው ይሉናል፡፡ ሰሞኑን ወሬያቸው አልሸባብ ላይ እየተወሰደ ያለው ‹‹መጠነ ሰፊ ጥቃት›› ሆኗል፡፡ ለኦባማ ገፀ በረከት መሆኑ ነው፡፡ (ለጠቅላላ እውቀት ያህል ግን ኦባማ ኢቲቪን አያይም)

ሀገር ውስጥም የፈጠሩት አልሸባብ ጥቃት ይፈፅማል ብለው ሰራዊት አፍሰዋል፡፡ አልሸባብ ነህ ብለው ዲያቆን ሳይቀር አስረዋል፡፡ አልሸባብ ግብሩን ከማን ወሰደ ቢባል መልሱ ቀላል ነው፡፡ ከፈጣሪው!

Al shebab