የኦነግ አባላትን ለማደን ጋራሙለታ የዘለቀው የሕወሓት የደሕንነት ሃይል የኦሕዴድ ካድሬዎችን ፈጃቸው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኦነግ አባላትን ለማደን ጋራሙለታ የዘለቀው የሕወሓት የደሕንነት ሃይል የኦሕዴድ ካድሬዎችን ፈጃቸው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከባሌ ክፍለሃገር ተነስተው አዳዲስ ተዋጊ አባላትን ለመመልመል ወደ ሃረርጌ ጋላሙለታ ዘልቀዋል የተባሉትን የኦነግ አባላት በደረሰው መረጃ መሰረት አድኖ ለመያዝ አሊያም የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ በሚል የዘመተው የሕወሓት የደህንነት ሃይል በአከባቢው ላይ ከነበሩ የኦሕዴድ ካድሬዎች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሶስት የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ካድሬዎችን እንደገደለ ተሰምቷል::

የደህንነት ቡድኑን ይሚመራው በጸረ ሽብር ግብረሃይል ስም የተሸፈነው የደህንነት ሰው የአከባቢው የኦሕዴድ ካድሬዎች ተሰብስበው ከጸረ ሽብር ግብረ ሃይል ለመምጣታቹ ደብዳቤ አምጡ በማለቱ እንዲሁም በአከባቢያችን የገቡ የኦነግ አባላት የሉም በቂ ቁጥጥር አድርገናል ጸጉረ ልውጦች እስካሁን የመጡ የሉም በአከባቢያችን ማንም ማዘዝ አይችልም የሚል መከራከሪያ በማቅረባቸው እና የደህንነት ሃይሉ የሚመልሰውን መልስ ለመቀበል እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው በተፈጠረው የቃላት ልውውጥ አለመግባባት የሕወሓት ደህንነቶች በያዙት ኡዚ መሳሪያ የኦሕዴድ ካድሬዎችን እንደፈጇቸው ታውቋል::

ከገደሏቸው በኋላ ሬሳውን ጭነው ደህንነቶቹ ወደ መሃል ሃገር እንደተመለሱ የገለጹት ምንጮች ሬሳውን መንገድ ላይ ይጣሉት አሊያም ይዘውት አዲስ አበባ ይግቡ አለመረጋገጡ ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬