አራት ልጆቻቸው በእስራኤል ጦር ውስጥ አገልግሎት የሰጡት ኢትዮጵያዊ አባት በሀገሬው ባለስልጣናት የመኖሪያ ፈቃድ መከልከላቸው ተዘገበ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ኢትዮጵያዊው የ 55 አመት አባት የቀድሞ ሚስታቸውና አራት ልጆቻቸው በ 1980 ዎቹ እንደፈረንጆቹ ወደእስራኤል ከተሰደዱ አይሁድ ኢትዮጵያዊያን ውስጥ ይገኙበታል፡፡ ቤተሰቡ ወደእስራኤል ከገባ በኋላ ሙሉ የእስራኤል ዜግነት ከማግኘቱ በተጨማሪም አራቱ ልጆች አድገው በእስራኤል ጦር ሀይል ውስጥ ብሄራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በቅተዋል፡፡
ይሁን እንጂ እኒህን አራት ልጆች አፍርተው ለእስራኤል የሰጡት አባት ለረጅም ጊዜ በሀገራቸው ኢትዮጵያ ከቆዩ በኋላ በ2013 እአአ ላይ ወደቤተሰቦቻቸው ጋር መሄዳቸውና በዛው በእስራኤል ኑሮን መጀመራቸው ነው የተነገረው፡፡ ዘግይቶም ቢሆን ግለሰቡ የጊዜያዊ ቪዛቸው ቀነ ገደብ በማለቁ በእስራኤል ከቤተሰባቸው ጋር ለመኖር የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለማግኘት ጥረት መጀመራቸው ቢነገርም የእስራኤል ባለስልጣናት ግን ለግለሰቡ መኖሪያ ፈቃድ እንደከለከሏቸው ይባስ ብሎም በህገወጥ መንገድ ያለፈቃድ በእስራኤል ለመኖር ሞክረዋል በሚል መታሰራቸው ነው የተዘገበው፡፡
መላ ቤተሰባቸው እሰራኤላዊ ሆኖ ሳለ በእስራኤል ለመኖር የሚያስችል ፈቃድ የተነፈጉት የእኚህ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በርካታ የዘር መድሎ በኢትዮ-አይሁዳዊያን ላይ ያደርሳል ተብሎ የሚታማውን የእስራኤል መንግስትን በእጅጉ እያሳማው የሚገኝ ቢሆንም እንኳን ግለሰቡ በፍርድ ቤት ሙግትም ቢሆን ፈቃዱን ያገኛሉ የሚል ተስፋ መኖሩን አንዳንድ የወሬ ምንጮች ዘግበዋል፡፡