ሰበር ዜና – ከቤተ ክርስቲያን የሰላምና የአንድነት ኮሚቴ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና የአንድነት ኮሚቴ በሜሪላን ከተማ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ አድርጎት በነበረው ስብሰባ ለመጪው የሰላምና የእርቅ ውይይት አስፈላጊ በሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች ላይ እንደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ተጠብቆ ነበር። በዚህም መሠረት የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው የእርቅ ውይይቱን ስፍራ እና ጊዜ በተመለከተ ኮሚቴው ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ ስብሰባው በአሜሪካን ሀገር ከዐብይ ጾም መግቢያ በፊት እንዲሆን ወስኗል።  ባለፈው ዓመት ተደርጎ በነበረው የእርቅ ስብሰባ ዙሪያ የታዩትን ችግሮችን ለማስወገድ ይቻል ዘንድ ኮሚቴው የስብሰባውን ከተማና ቦታ እንዲሁም የስበሰባውን ጊዜ በዝርዝር እንደማይገለጽ ለመረዳት ችለናል። በአባቶች ስብሰባ ጊዜ ግራ አጋቢና ሃሳብ ከፋፋይ ግለሰቦች ድርሻ እንዳይኖራቸው አስፈላጊው ሁሉ ጥረት እንደሚደረግም የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
ከዚህ ጋር አያይዞ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው የእርቁን ስበሰባ በሚገባ ለማካሄድ ያመች ዘንድ ወጪውን ለመሸፈኛ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በተለያዩ ከተማዎች ይደረጋሉ። ከዚህ ቀደም ተደርጎ ለነበረው ስብሰባ አስፈላጊው ወጪ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላትና በጥቂት የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች የተሸፈነ ቢሆንም ይህ ኃላፊነት የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ሰላም ለማየት የሚፈልጉ ሁሉ የጋራ ድርሻ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ከሥራቸው ፈቃድ በመውሰድ ለስብሰባ ዝግጅት አስፈላጊውን ጊዜ ከመሰዋት ባሻገር ብዙዎቹ የኮሚቴ አባላት የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለማገናኘት የሚያስፈልገውን ወጪ ከኪሳቸው አውጥተው ለመሸፈን እንደሚቸገሩ ለሁላችንም ግልጽ ነው ለመረዳት ችለናል። በመሆኑ እያንዳንዱ ምእመን ለዚህ ታሪካዊና መንፈሳዊ የእርቅና የሰላም እንቅስቃሰየ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚቴው ጥሪውን አስተላልፏል።  
ከዚህ በታች ያለው የኮሚቴው ደብዳቤ አስፈላጊውን መረጃ እንደሚሰጣችሁ እምነታችን ነው።