ሴቶች ደፈሩ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Meron Getinet
Aster Bedane
ሸክሙ አስቸገራቸው፣ መተንፈስ ጀመሩ፣
ወንዶቹ ሲፈሩ፣ ሴቶች ተዳፈሩ፣
የሕሌናቸውን፣ ደፍረው ተናገሩ።
ባለፈው ለት ሜሮን በግጥም ተነፈሰች፣
የውዳሴ ከንቱ፣ መመሪያውን ጣሰች፣
ሥሙኝ ብላ ጮኸች፣
ውርድ ከእራሴ እያለች፣
ለሁሉ አዳረሰች፣ ለሁሉም አሰማች፣
ያለውን አንድ በአንድ፣ እየዘረዘረች፣
ወቼ ጉድ አሰኘች፣ ሕዝብን አሥደመመች
ወዳጅ ካድሬዎችን፣ በጣም አሳዘነች፣
ማወደሱን ትታ፣ ሃቅ በተናገረች፣
ጥርሥ ተነከሰባት፣ አንች ክሃዲ ተባለች፣
ሃቅ በመሰከረች፣ ከሕዝብ በወገነች።
በሜሮን ተንጫጭተው፣ ነደው ሳያበቁ፣
በአስቴር በዳኔ፣ ደግሞው ተጠየቁ፣
ያው ቁሥላቸው ሳይሽር፣ ድጋሜ ተጠቁ፣
ሕሌና አልባዎቹ፣ አቃጣሪዎቹ፣ ምታለቀልቁ፣
ገና ሥንት ጉድ አለ፣ ይወጣል ጠብቁ።
አስቴር ከፊታቸው፣ ከመሃል ተነሥታ፣
መሥማት ማይሹትን፣ ጠየቀች አንሥታ፣
መመለስ አይችሉም፣ እሷም ታውቀዋለች፣
መጠየቋን እንጅ፣ መልስም አልጠበቀች።
የሁሉም ጥያቄ የሆነውን ነገር፣
ማን ደፍሮ ይጠይቅ፣ ማን ደፍሮ ይናገር።
ከመካከላቸው፣ ይሄው ሴቷ ደፍራ፣
ውርድ ከእራሴ አለች፣ እውነቱን ተናግራ፣
እሷ ምን ተዳዋ፣ ሰው የፈለገውን ያሻውን ቢያወራ፣
ሥለተናገረች ታፍኖ ያለውን፣ የብዙሃን ብሶት፣
አንዳንዱ ሲወቅሳት፣ ሌላው ሲያወድሳት፣
አንዱ ሄሮ ሲላት፣ ሌላው ሲያኮስሳት፣
በቀን አሥር ጊዜ፣ ሚዲያው ሲያነሳት፣
ሚነድ ዜና ሆነች፣ የማይጠፋ እንደሳት።

– Getachew Mulatu