ሰሞነኛ ወጋ-ወግ!-ቁጥር-2


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወይ ቻይና አሉ አንድ አባት በመገረም የሰላማዊ ሰልፈኞቹን የዋሽንግቶን ሰላማዊ ሰልፍ ዜና ካዳመጡ በኋላ በቅርቡ ልጃቸው ጋብዛቸው ወዲህ ወዳመሪካ ብቅ ያሉ አባት:: የኛን አገር ለምን ፈረንጁ ሁላ እንደሚወደው አሁን ነው የገባኝ: ምክኛቱም ይሔው ከመጣሁ ጀምሮ ከቤት አልወጣ ሙቀቱ አያድርስ ነው ልጆቼ; ምድሩ እሳት ሰማዩ እሳት እንዲያው ይሔ ማቀዝቀዣችሁማ ባይኖር የሚኖርበት አገር አይደለም:: ታዲያ ድሮ ጣሊያን ሊወስዳት አስቦ ያው ሳይሳካለት ቀረ: ከጣሊያን በኋላ እንግሊዞችም አስበዋት ነበር አሉ በንጉሱ ደሞ አማሪካኖቹ ወዲያ ወዲህ ማለት ጀምረው ነበረ: ቀጥሎ ደሞ ራሻዎቹና ኩባዎቹ መጡ ሁሉም ሄዱ ያሁኖቹ እኒህ ቻይናዎቹ ብዛታቸውን ጉድ እኮ ነው የምትሉት፤ በማለት አግራሞታቸውን ከገለጹ በኋላ የነሱም አገር እንዲሁ እንዳማሪካ እየሞቃቸው ይሆን የኛን አገር የሚወዱት? ሲሉ ግንዛቤአቸውን አስቀመጡ::ሞቀም አልሞቀ እሳቶቹ (ኢሳቶቹ) ቻይና ኤምባሲ ሰልፉን ሲያሟሙቁ፤ የወያነ ደጋፊዎች ደሞ ከላፋየት ፓርክ እስከ ስቴት ዲፓርትመንት ድረስ አሟሙቀዋል:: ዋሽንግቶንም ላለፉት 18 አመታት ሱስ የሆነባትና ለጥቂት ወራት የጠፋባት የእኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ ከስታርባክስ የአኢትዮጵያ ቡና ጋር ተቀላቅሎ ውልታዋን አርክቶላት ሰንብቷል።