ትግላችን ተቀናጅቶና ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! (አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር) – October 9, 2013
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ላለፉት ሶስት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ሕዝባችን በአራቱም ማእዘናት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ያለዉን ጥማት ለመግለጽና በሚታዩት የዜጎች የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ለማስተጋባት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ስር ሲንቀሳቀስ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ/ሶዶ፣ በባሌ/ሮቢ፣ …