ልጅ በአባቱ ለመጨከን ተፈጥሮው አልፈቀደለትም! – ክርስቲያን ታደለ

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ ባካሄደው አንደኛ ልዩ ስብሰባ ሕወኃት በ61 ተቃውሞ፤በ5 ተዓቅቦ፤ በአብላጫ ድምጽ የአሸባሪነት ስያሜው ተነስቶለታል።
① በመከላከያ ሰራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ወንጀል የፈፀመና የአገር ክህደት ወንጀል የፈፀመ፤
② በአማራና አፋር ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል እንዲሁም የጦር ወንጀል የፈፀመ፤
③ አሁንም የጦር ነጋሪት እየጎሰመ ያለ፤
④ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ሆኖ ባወጣቸው ሪፖርቶች መሰረት ይቅርታና ምሕረት የማያሰጡ ዓለምአቀፍ ወንጀሎችን መፈፀሙ የተረጋገጠበት፤
ድርጅት ሆኖ ሳለ፤ «ከጋራ የጦርና በሰብአዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት በጋራ ስምምነት እናምልጥ» በሚል የጋራ ስምምነት በሚመስል መልኩ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ቀርቦ ውይይት ሳይደረግና ስምምነቶቹ ስለመፈፀማቸውም ማረጋገጫ ሳይገኝበት፤ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን ታሪክ መዝግቦታል። ውሳኔውን ተከትሎ በድብብቆሽ ሲከወኑ የነበሩ «ጉንጭ መሳሳሞች» ወደ አደባባይ መተቃቀፎች እንደሚያድጉ ይገመታል።
ልጅ በአባቱ እንደማይጨክን ተናግረን ነበር!