‹‹እኛ በራችንን ዘግተን ስንቀመጥ በዓለም ላይ ግን መሄጃ ያጣ የገንዘብ ውቅያኖስ አለ›› አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያ

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ አክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያን በማቋቋምና በቦርድ አመራር ሥራ አስፈጻሚነት  በመምራት እስከ ቅርብ ጊዜ ድርስ መርተውታል፡፡ በርካቶች አዳዲስ የኢንቨስትመንት ሐሳቦችን በኢትዮጵያ የተገበሩ፣ የፋይናንስ ኢንዲስትሪው ውስጥ ባለአንድ ቅርንጫፍ ባንክ የሚል መነሻም ዘመን ባንክን ያደራጁ እየተባሉም ይጠቀሳሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት አቶ ኤርሚያስ ያደጉትና አፋቸውን የፈቱት ግብፅ ውስጥ በዓረብኛ ቋንቋ ነው፡፡ ከግብፅ ወደ ኬንያናይሮቢ በማቅናትም የእንግሊዝኛና የስዋህሊ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ለመናገር ያስቻሏቸውን ጊዜያት በኬንያ አሳልፈዋል፡፡ በታዳጊነታቸው ወቅትም ወደኢትዮጵያ በመመለስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሜሪካ ኢንተርናሽናል ኮሙዩኒቲ ስኩል በማጠናቀቅ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለአንድዓመት ከተማሩ በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው መሥርተው ቆይተዋል፡፡ ከ22 ዓመታት በፊት ዳግመኛ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ፣ በአሜሪካ ዎልስትሪት የካፒታል ገበያ ውስጥ በመሥራት […]