“በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ አልተደሰትኩም ቅሬታ አለኝ” – ወ/ሮ ሙሉ ገ/ እግዚአብሄር የፓርላማ አባል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው እስረኞች በይቅርታ መፈታታቸውን ከሕግ አግባብ ጋር አያይዘው ጥያቄ ያቀረቡት የምክር ቤቱ አባል ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ናቸው፡፡ ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ አልተደሰትኩም ቅሬታ አለኝ፤›› ብለዋል፡፡ ለቅሬታቸው እንደ ምክንያት የሚያነሱት ላቀረቡት ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ከመስጠት ይልቅ፣ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተጠምደው ነበር የሚል ነው፡፡ ‹‹እኔ የፓርቲ አባል ብሆንም ያቀረቡኩት ጥያቄ […]