የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ (‹ፈላስፋው› ዘርዐ ያዕቆብ ማነው?)

የመጽሐፉ ታሪክከደብረ ታቦር ከተማ የተላኩ ሁለት መጻሕፍት በ1848 ዓ.ም. ፓሪስ ደረሱ፡፡ መጽሐፎቹ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ያልተለመደ ይዘት ያላቸው ናቸው፡፡ የተላኩለት ሰው አንቶኒዮ ዲ. አባዲ የተባለ ፈረንሳዊ የካቶሊክ ሚሲዮናዊ ነው፡፡ ዲ. አባዲ በዘመነ መሳፍንት እኤአ ከ1836 – 1848