የምግብ ዋስትና የኢትዮጵያዊያን መብት ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

በክፍል፡ አምስት፡ ህወሓት፡ ሙሉ፡ በሙሉ፡ የሚቆጣጠረው፡ መንግስት፡ እንዴት፡ አድርጎ፡ ተቋሞችን፡ ወገናዊ፡ እንዳደረገ፤ ሃቭትና፡ ጥሪት፡ ለእራሱና፡ ለደጋፊወቹ፡ እንደሚያካብት፤ የመከላከያ፤ የህግ፤ የውጭ፡ ግንኙነት፤ የጉምሩክ፤ የባንክ፤ የማዘጋጃ፡ ቤት፤ የአስተዳደር፤ የተፈጥሮ፡ ጥሪት፡ አጠቃቀም፤ የስራ፡ ፈቃድ፤ የትምህርት፡ ድርጅቶችን፡ በሙሉ፡ ፖለቲካዊ፤ ዘራዊ፤ እንዳደረገ፡ በማስረጃ፡ አሳይቻለሁ። እድገት፡ አለ፡ ቢባልም፤ የዚህ፡ አይነት፡ አድሏዊ፡ አገዛዝ፡ በምንም፡ መለኪያ፡ ዘላቂነትና፡ ፍትሃዊነት፡ ሊኖረው፡ አይችልም። አሁን፡ ኢትዮጵያ፡ ያለችበት፡ ሁኔታ፡ በልዩ፡ ልዩ፡ ዘርፍ፡ የችግሩን፡ክብደት፤ ስፋት፤ ያሳያል። መንግስት፡ ብቻውን፡ ችግሩን፡ ሊፈታው፡ አይችልም። ህወሓት፡ ያልተገነዝቨውና፡ ሊገነዘቭው፡ የማይፈቅደው፡ አገራዊ፡ ችግሮች፡ ሊፈቱ፡ የሚችሉት፡ ሌሎችን፡ በማቀቭ፤ በማሳደድ፤ በማሰር፤ በመግደል፤ አያገቫችሁም፡ በማለት፡ አይደለም። ችግሮች፡ ሊፈቱ፡ የሚችሉት፡ በአገራዊ፡ አሰራር፡ ስርአት፤ በመላው፡ ህዝብ፡ ተሳትፎ፤ ድምጽ፤ መብት፤ እኩልነት፡ ነው። የስር አቱን፡ ፖሊሲ፡ በመለወጥ፡ ብቻ፡ ነው። የምግብ፡ ዋስትናን፡ ጥያቄ፡ ምሳሌ፡ አድርገን፡ እንይ።

የምግብ፡ ዋስትና፤ ያለ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ተሳትፎ፡ አይገኝም፤

በዋሽንግቶንና፡ በካምፕ፡ ዴቪድ፤ በዚህ፡ ሳምንት፡ ደግሞ፡ በሜክሲኯ፡ የተደረጉት፡ የG-8ና፡ የG-20 ስብስብ፡ ያልተገነዘበው፡ የህወሓትን፡ የመጥፎ፡ አገዛዝ፡ ሃቅ፡ ነው። የህዝብን፡ መብቶች፡ የገፈፈ፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስ፤ የመምረጥ/መመረጥ፤ ወዘተ፡ መብቶችን፡ ማቀብ፡ ስልቱ፡ የሆነ፡ መሪ፡ ለተራቨ፤ ስራ፡ ላጣ፤ ለሚሰደድ፤ ለሚዋረድ፤ ደንታ፡ የለውም። የዘር፡ ክፍፍልና፡ ጽዳት፤ መሳሪያ፡ የሆነውን፡ የክልል፡ ስር አት፡ ዘላቂነት፡ ለመስጠት፡ የሚሞክረው፡ ለቁጥጥር፡ እንዲያመች፡ነው። የገጠሩን፡ አምራች፡ የሚቆጣጠረው፡ ለማጎልመስ፡ ሳይሆን፤ ስልጣንን፡ ለማቆየት፡ ነው።

የመገናኛ፡ ብዙሃን፡ ቁልፍ፡ የሚሆነው፡ እዚህ፡ ላይ፡ ነው። ህዝብ፡ ለህዝብ፡ እንዲገናኝ፡ ከተፈለገ፡ መገናኛ፡ ብዙሃን፡ሚና፡መጫወት፡ አለበት። እውነቱን፤ በደሉን፤ ሙስናውን፤ አድሎውን፤ ያወቀ፡ ህዝብ፡ ለመብቱ፡ ይታገላል። ማን፡ እንደሚጎዳው፤ ማን፡ እንደሚረዳው፡ ያውቃል። በነጻነት፡ የሚያገለግል፡ የዜና፡ ስርጭት፡ ለመብት፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለእውቀት፤ ለመደጋገፍ፤ ለእድገት፤ ለህዝብ፡ አመጽ፤ ለገበያ፡ ስፋት፤ ለድፍረት፡ ቁልፍ፡ነው። በሰሜን፡ አፍሪካ፡ የተካሄደው፡ የህዝብ፡ አመጽና፡ ለውጥ፡ ያለዜና፡ ስርጭት፡ ግብ፡ አይደርስም፡ ነበር። የግብጽ፡ ህዝብ፡ ለመጀመሪያ፡ ጊዜ፡ መሪውን፡ ያለ፡ ተጽኖ፡ ለመምረጥ፡ የቻለው፡ የህዝብ፡ አመጽ፡ ውጤት፡ ነው። ውጤቱ፡ እውን፡ የሆነው፡ በመገናኛ፡ ብዙሃን፡ አጠቃቀም፤ በህዝ፡ ሰንሰለትና፡ አብሮ፡ መነሳት፡ ስልት፡ ጭምር፡ ነው። እኛ፡ ኢትይጵያዊያንም፡ ልምዱ፡ አለን። የጎደለን፡ ድፍረቱ፡ ይመስላል። ለዚህም፡ ነው፤ መለስና፡ ግብረአበሮቻቸው፡ መገናኛ፡ ብዙሃን፡ የሚፈሩት፤ በሙሉ፤ የዘጉት። እነ፡ እስክንድር፡ ነጋ፤ እነ፡ አንዱ አለም፡ አራጌና፡ ሌሎች፡ ነጻ፡ ጋዜጠኞችን፡ እስር፡ ቤት፡ የታጎሩት፤ ሌሎችም፡ ከሃገር፡ እዲወጡ፡ የተገደዱት፡ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለህዝብ፡ ድምጽ፤ ለእውነተኛ፡ ሰላም፡ ስለቆሙ፡ እንጂ፤ ወንጀለኛ፡ ስለሆኑ፡ አይደለም። ሀወሓት፤ ሌላው፡ ቀርቶ፡ በውጭ፡ የምንገኘውን፡ ሁሉ፡ ለማበርከክ፡ ይሞክራል። አንዳንዶቻችን፡ ለፍረሃት፡ ተገዥ፡ የሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። ፍርሃቱ፡ በምንም፡ አያዋጣም።

በልቶ፤ ሰርቶ፡ ለማደር፡ ነጻነት፡ ወሳኝ፡ ነው፤

የህዝብ፡ ተሳትፎ፡ የሌለበት፡ እድገት፡ በምንም፡ ፍትሃዊ፡ ሊሆን፡ አይችልም። የ G-8፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ስብሰባ፡ የተካሄደው፡ እንደዚህ፡ ባለ፡ ሁኔታ፡ ነው። በአሜሪካ፡ የሚገኙ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ይህን፡ አጋጣሚ፡ በመጠቀም፡ እ.አ፡ አ፡ በተከታታይ፡ May 14, 2012 ሁዋይት፡ ሃውስ፡ ሕንጻ፡ ፊት፡ ለፊት፤ ከዚያም፡ በህንድ፡ ኤምባሲ፡ ፊት፡ ለፊት ፤ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ የሚያኮራ፤ ሁሉም፡ ለመብቱ፤ ለነጻነቱ፤ ለአንድ፡ አገር፤ በአንድ፡ ድምጽ፡ የሚነሳበትን፡ መፈክሮች፡ አንግቮ፡ አጋርና፡ ጠቨቃ፡ ለሌለው፡ ህዝብ፡ ሲሟገት፡ ዉሏል። በ May 18, 2012, ከጥዋቱ፡ ሰቫት፡ ሰአት፡ ተኩል፡ ጀምሮ፡ በሬገን፡ ህንጻ፡ የተካሂደው፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ የኢትዮጵያን፡ ስብጥር፡ ህዝብ፡ ያንጸባረቀ፤ በወጣቶች፡ የተመራ፤ የተቀነባበረ፡ መልእክት፡ ያስተላለፈ፡ ነበር፡ ለማለት፡ እችላለሁ። ከውጭ፡ ያለው፡ ድምጹን፡ ለፕሬዝደንት፡ ኦባማ፤ ለአሜሪካ፡ ህዝብ፤ ለተጠሩ፡ እንግዶች፡አሰማ። አዳራሹ፡ ውስጥ፡ ደግሞ፤ የታወቀው፡ ጋዜጠኛ፤ አቶ፡ አበበ፡ ገላው፡ ታሪክ፡ የመዘገበው፤ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያከበረው፤ የአሁንና፡ የወደፊት፡ ትውልድ፡ ምሳሌ፡ የሚያደርገው፤ ለፍትህ-ርትእ፡ የቆሙ፡ ሁሉ፡ “አገራችን፡ ሰው፡ አላት” ብለው፡ ሊነሳሱብት፡የሚያስችል፡ መልእክት፡ አስተላለፈ። ቀረብ፡ ብሎ፡ ለሰማው፡ በአዳራሹ፡ ያለው፡ ሁሉ፡ አይኑና፡ ሃሳቡ፡ በሙሉ፤ ከተናጋሪው፡ ላይ፡ ነበር። “መለስ፡ ዜናዊ፡ አምባገነን፡ ነው። እስክንድር፡ ነጋ፡ ይፈታ። የፖለቲካ፡ እስረኞች፡ ይፈቱ። ምግቭ፡ ያለ፡ ነጻነት፡ ዋጋ፡ የለውም። መለስ፡ ሰላማዊ፡ ህዝብ፡ በመግደል፡ ወንጀል፡ ፈጽሟል፡ (ወንጀለኛ፡ ነው)። እኛ፡ የምንፈልገው፡ ነጻነት፤ ነው። ነጻነት፤ ነጻነት፤ ነጻነት.” ጸጥ፡ ብሎ፡ ያዳመጠው፡ ሁሉ፡ በአድናቆት፡ ተቀብሎታል፡ ለማለት፡ እደፍራለሁ። ፕረዝደንት፡ ኦባማ፡ “አመስግናለሁ” ብለው፡ ሲሸኙት፡ ምን፡ ያስቡ፡ እንደነበር፡ ከስራቸው፡ ሲወጡ፡ መግለጻቸው፡ አይቀርም። ለህሊናቸው፡ ምግብ፡ አግኝተዋል።

ሰብእነትን፡ ሲገፉ፤ የእራሳቸውን፡ ብሄረሰቭ፡ “እንቁ፤” አማራውን፡ “ጭራቅ”፡ ብለው፡ የሚሳደቩት፤ ተቃዋሚወቻቸውን፡ ሁሉ፡ የሚያዋርዱት፤ ግለሰቦችን፡ ባልሰሩት፡ ወንጀል፡ ይቅርታ፡ ጠይቁ፡ ብለው፡ እንዲምበረክኩ፡ የሚያስገድዱት፤ ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ ካሉበት፡ መቀመጫ፡ ሰምጠው፤ ራሳቸውን፤ ወደታች፡ ሲቀረቅሩ፡ የተቀረጸው፡ ሰእል፡ የውርደቱን፡ ክብደትና፡ ቆይነት፡ አሳይቷል። መልክቱ፤ አንድ፡ ግለሰብን፡ በመጥላት፤ በይፋ፡ ማዋረዱ፡ አይመስለኝም። መልክቱ፡ “ነጻነት፤ መብት፤ ፍትህ፤ የህግ፡ የበላይነት፤ እኩልነት፤ የመላው፡ ህዝብ፡ ድምጽና፤ተሳትፎ፡ ይከበር” የሚል፡ ነው። መልክቱ፤ “የአንድ፡ ጠባብ፡ ብሄርተኛ፡ ጠቅላይ፡ ሚኒስትር፡ መሆነወን፡ ያቁሙ፤ መላውን፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያለ፡ አድሎ፡ ያገልግሉ፤ አድሎወትን፡ ያቁሙ፤ አገራችን፤ “ዘርፎ፡ ለዘራፊ፡ አይዳርጓት” ወዘተ፡ የሚል፡ ነው። ማንም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ቢሆን፡ ለኣገሩ፤ ለመላው፡ ህብረተሰብ፤ የቆመን፡ መሪ፡ አያዋርድም። ይህ፡ ቢሆን፡ ውርደቱ፡ ለሁሉም፡ ይሆን፡ ነበር። ጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፡ ህወሓትና፡ መንግስቱ፡ “የእነሱ፡ ፓርቲ፤ የእነሱ፡ መንግስት” ተብሎ፡ እንደሜጠራ፡ ያውቃሉ። አብዛኛው፡ ህዝብ፡ ህወሓትንና፡ የሚመራውን፡ መንግስት፡ “የእኔ፡ ፓርቲ፤ የእኔ፡ መንግስት” ናቸው፡ ብሎ፡ አለመቀበሉን፡ ጋሎፕ፡ፓል፡ በማስረጃ፡ አቅርቦታል።

የጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፡ በመሪወች፡ ፊት፡ እነደዚህ፡ መጋለጥ፤ መዋረድ (humiliation): የህይወት፡ ሙሉ፡ ለምጽ፡ መሆኑ፡አያጠራጥርም። ይህን፡ ሁኔታ፡ የፈጠሩት፡ እራሳቸው፤ ፓርቲያቸው፤ ደጋፊወቻቸው፤ እንጂ፤ ሌላ፡ ሰው፡ አይደለም። የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ “ጉድ”፡ አልፎም፡ “እሰይ” ማለቱ፡ አልቀረም። በሰአት፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡የተላለፈው፡ ቪዲዮ፡ ብዙ፡መቶ፡ ሽህ፡ ህዝብ፡ በሞባይል፡ እየተቀባበለ፡ አሰራጭቶቷል። አሁንም፡ እያነጋገረበት፡ ነው። ሲጠቀስ፡ ይኖራል።

ከዚያ፡ ባሻገር፤ ቁም፡ ነገሩ፤ አበበ፡ ገላው፤ እንደ፡ አብዛኞቻችን፡ “ምሁራን”፡ በፍርሃት፡ አልተጠመደም። ለግል፡ ጥቅም፡ አልተገዛም። ታሪካችንና፡ ባህላችን፡ የሚያስተምረን፡ ፍርሃትን፡ ሳይሆን፡ ድፍረትን፤ መከፋፈልን፡ ሳይሆን፡ አብሮ፡ መኖርን፤ እ ራስ፡ ወዳድነትን፡ ሳይሆን፡ አገርን፡ ማስቀደም፤ ነው። ደፍረን፡ መነሳት፡ የነጻነት፡ መለኪያችን፡ ነው። አብዣⶉቻቺን፡ ከእነዚህ፤ መለስ፡ ዜናዊና፡ ታማኝ፡ ቡድናቸው፡ ካዘጋጁልን፡ የፍርሃት፡ ወጥመድ፡ ነጥቀን፡ ብንወጣ፡ ኢያትዮጵያ፡ እንደ፡ ግብጽ፤ እንደ፡ ሊቢያ፤ እነደ፡ ቱኒሲያ፡ ተሳትፏዊ፡ ለውጥን፡ ትቀዳጃለች። ጋዜጠኛው፡ ለአንድ፡ ብሄረሰብ፤ ለአንድ፡ ቡደን፤ ለአንድ፡ ሃይማኖት፡ አልተናገረም። የተናገረው፡ ለኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ በሙሉ፡ ነው። ያሳየን፤ የነጻነት፤ የፍትህ፤ ጥቅም፡ በሳንቲም፡ የሚታሰብ፡ አለመሆኑን፡ ጭምር፡ ነው። ነጻነት፤ በቤት፤ በመሬት፤ በገንዘብ፡ ድጎማ፤ የማይለወጥ፡ መሆኑን፡ ነው። ነጻነት፡ የሌለው፡ ሰው፡ በ እራሱ፡ አይተማመንም። ይፈራል።ይገረፋል፤ ይሰደዳል። በሆዱ፤ ለሆዱ፡ ይገዛል። ለሰብ አዊ፡ መብት፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለሰው፡ ክብር፡ መታገል፡ በዶላር፡ ሊተመን፡ አይችልም። ነጻነት፡ ካለ፡ ያለ፡ አድሎ፡ ለመስራት፤ ለመፍጠር፤ ለመንቀሳቅስ፤ ሃብት፡ ለማግኘት፤ ለመምረጥ፤ ባለ፡ ስልጣኖችን፡ “ሃላፊ፡ ናችሁ፤ አገልጋይ፡ ናችሁ፡” ለማለት፡ ይቻላል። ጠባብ፡ ብሄርተኞችን፤ ሌቦችን፤ ሙስኞችን፤ የንጹህ፡ ደም፡ አፍሳሾችን፤ ለም፡ መሬት፤ ሴቶች፤ ህጻናት፡ እንደ፡ ተራ፡ ሸቀጥ፡ ቸርቻሪወችን፡ በህግ፡ ለመሟገት፤ ደፍሮ፡ ለማጋለጥ፤ ይቻላል።

ለህግ፡ የበላይነት፤ ለፍትህ፤ ለሃገር፤ ለድሃው፡ ህዝብ፤ የቆመ፡ አገር፡ ወዳድ፡ መሪ፡ እንደ፡ ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ “የመንግስት፡ ሌቦች፡ አሉ። በውጭ፡ ሁለት፡ ቢሊየን፡ ዶላር፡ ያስቀመጡ፡ መኖራቸውን፡ እናውቃለን።” ብዙ፡ ሽህ፡ ቶን፡ ቡና፡ ሲሰረቅ፡ “ማን፡ አንደሰረቀ፤ እናውቃለን። የእኛው፡ እጂ፡ ስላለበት፡ አንከታተለውም” ለማለት፡ አይችልም፤ ህሊናው፡ አይፈቅድም። ከህግ፡ በላይ፡ ነኝ፡ የሚል፡ መሪ፡ ብቻ፡ ነው፡ አይቶ፡ አላየሁም፡ የሚል። ስለሆነም፤ ችግሩን፡ የፈጠረው፡ የህወሓት፡ አገዛዝ፡ ነው። ተጠቃሚው፡ እራሱና፡ ታማኞቹ፡ ናቸው። ሙስናን፡ ስናይ፡ የቻይና፡ ጠበብት፡ አንዳሉት፡ “አሳ፡ የሚገማው፡ ከእራሱ፡ ነው.” የሚለው፡ ለህወሓት፡ አዛዦች፡ አግባብ፡፡አለው። የህወሓት፡ ስር አት፡ የገማው፡ ከቁንጮው፡ ነው።” ጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፡ ይህን፡ አያውቁም፡ ብሎ፡ መናገር፡ ቂልነት፡ ነው። የመለስ፡ መንግስት፡ ለፍርድ፡ የሚያቀርበው፡ ዝቅተኛ፡ በሙሰኝነት፡ ተከሳቾን፡ እንጂ፡ “ለገማው፡ ስርአት፡ ተጠያቂ፡ መሆን፡ የሚገባቸውን፡ የመንግስት፤ የፓርቲ፤ ሌቦች፤ የበላይ፡ ባለስልጣኖች፡ አይደለም። ወደ፡ ቤተሰብ፡ ስለሚመራ።

አበበ፡ ገላው፡ ታሪክ፡ በሰራበት፡ ሳምንት፤ May 19, 2012፤ በካምፕ፡ ዴቪድ፤ ከምርጫ፡ ዘጠና፡ ሰባት፡ ወዲህ፡ አስደናቂ፡ የሆነ፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ ተካሂዷል። የሚዲያ፡ ሽፋኑ፡ ከዚህ፡ በፊት፡ ታይቶ፡ የማያውቅ፡ መሆኑን፡ አይቻለሁ። የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ ሰቆቃ፡ ፈረንጆች፡ እንደመዘገቡት፤ “በብዙ፡ መቶ”፤ እኔ፡ እንዳየሁት፤ ከሽህ፡ በላይ፤ የልዩ፡ ልዩ፡ ሃይማኖት፤ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ፡ ስብሰብ፤ የወጣትና፡ የሴቶች፡ ተወካዮች፡ ድምቅት፡ ባለው፡ ሑኔታ፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ አካሂደዋል። የሰበሰባቸው፡ አበይት፡ጉዳይ፡ የመለስ፡ ዜናዊ፡ ህወሓት፡ አሰቃቂ፡ ስርአት፡ ነው። ያያዛቸው፡ አበይት፡ ጉዳይ፡ ነጻነት፤ ፍትህ፤ የህግ፡ የበላይነት፤ ሰብአዊ፡ መብት፤ የሰው፡ ክብር፡ ወዘተ፡ መናድ፡ ናቸው። ኢትዮጵያዊያንና፡ ደጋፊወች፡ በደመቀ፡ ሁኔታ፡ ለፍትህ፤ ለነጻነት፡ ሲታገሉ፤ የአሜሪካ፡ ፕሬዝደንት፤ ኦባማ፤ ለ G-8፤ ስለ፡ ምግብ፡ ዋስትና፡ ያቀረቡትን፡ ሃሳብና፡ እቅድ፡ ማጤን፡ አስፈላጊ፡ ነው። በ May 18, 21012: ስብሰባ፡ ላይ፡ እንዲህ፡ አሉ። “ተከታታይ፡ እርሃብ፡ ኢ-ፍትሃዊ፡ ነው። መንግስታት፡ ሁሉ፤ እርሃብን፡ ማጥፋት፡ ተቀዳሚ፡ ተግባራቸው፡ መሆን፡ አለበት። የምግብ፡ ዋስትናን፡ ጭብጥ፡ ማድረግ፡ የጥበባዊ፡ እድገት፡ አመራር፡ መለኪያ፡ ነው። ሰው፡ ክብሩን፡ የሚጎናጸፈው፡ በእርዳታ፡ ሲኖር፡ አይደልም። እራሱን፡ ሲችል፡ ብቻ፡ ነው። ሰውን፡ በምግብ፡ ለመደጎም፡ የምናደርገው፡ እርዳታ፡ ዘላቂ፡ መልስ፡ ሊሆን፡ አይችልም።” ፕሬዝደንቱ፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፤ ምሁራን፤ የእድገት፡ ባለሙያወች፤ ተቋሞች፡ ሲሉት፡ የቆየውን፡ በመቀበላቸው፤ የአሜሪካ፡ የእርዳታ፡ አመራር፡ የተለወጠ፡ ይመስላል። ድጋፉ፡ ትንንሽ፡ ገበሬወችን፤ ድሃውን፤ የአገር፡ ከበርቴውን፡ ለማጎልመስ፡ ይመስላል። እኔ፡ ግን፡ በጀርባ፡ ያለውን፡ አላማና፡ እቅድ፡ እጠራጠራለሁ። የምጠራጠረው፡ የኢትዮጵያን፡ ታናናሽ፡ ገበሬወች፤ የአገራችን፡ ከበርቴወች፡ በዘመናዊ፡ እርሻ፡ ተሳትፎ፡ ለማጠናከር፡ አመራሩ፤ መንግስቱ፡ ከአድሏዊነት፤ ወደ፡ ኢትዮጵያዊነት፡ መለወጥ፡ ይኖርበታል። ኢትዮጵያዊያን፡ የአገራቸው፡ የተፈጥሮ፡ ሃቨት፡ አዛዦች፡ መሆን፡ አለባቸው። መብት፤ ነጻነት፤ ተሳትፎ፡ ከታገደ፡ ኢትዮጵያዊ፡ ተሳትፎ፤ ዘላቂነትና፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ ሊኖር፡ አይችልም።

ምክንያቱም፤ ከአጼ፡ ሓይለ፡ ስላሴ፡ መንግስት፡ ጀምሮ፤ በተለይ፡ በመለስ፡ መንግስት፤ የአሜሪካ፡ ሰብአዊ፡ ርዳታ፡ ከአስር፡ እስከ፡ አስራ፡ ሶስት፡ ሚሊዮን፡ የሚሆኑ፡ ኢትዮጵያዊያንን፡ በምግብ፡ ድጎማ፡ እንዳይሞቱ፡ ማድረግ፡ ነው። ይህ፡ የጥገኝነት፡ መለኪያ፡ ነው። ታዲያ፤ እስካሁን፡ አመራሩ፡ (Policy) ለምን፡ አልተለወጠም፡ ብሎ፡ መጠየቅ፡ ተገቢ፡ የሚሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። ኢትዮጵያ፡ በምግብ፡ እራሷን፡ ከመቻል፡ አልፋ፡ ወደ፡ ውጭ፡ ለመላክ፡ እንደምትችል፡ ማሰረጃወች፡ አሉ። የመሬት፡ ነጠቃንና፡ ቅርሚትን፡ ማየት፡ ብቻ፡ ይበቃል። ድሃው፡ ህዝብ፡ የእድገቱ፡ አጋር፡ ካልሆነ፤ በአመራርና፡ በተግባር፡ ተሳታፌ፡ ካልሆነ፤ ድምጹ፡ ካልተሰማ፤ ነጻነቱና፡ መብቱ፡ ካልተከበረ፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ሊኖረው፡ አይችልም። የአሜሪካው፡ መሪ፡ ይህን፡ ያውቁታል። ተሳትፎ፡ ከሌለ፡ ፍትህ፡ ሊኖር፡ አይችልም። ዘላቂነት፡ ያለው፡ እድገት፡ ሊኖር፡ አይችልም። ፍትሃዊ፡ እድገት፡ (equitable development)፤ ከአምባ፡ ገነን፡ ስርአት፡ ጋር፡ አብሮ፡ አይሄድም። መለስ፡ ዜናዊ፡ አምባ፡ ገነን፤ በህግ፡ የበላይነት፡ የማያምኑ፡ ከሆኑ፡ (መሆናቸው፡ አያጠራጥርም)፡ መጀመሪያ፤ የፖለቲካው፡ ስርአት፡ መፈታት፡ አለበት፡ ማለት፡ ነው። ፖሊሲና፡ መዋቅሩ፡ ከስር አቱ፡ ጋር፡ የተያያዙ፡ ስለሆነ፡ የመንግስት፡ አመራር፡ ችግር፡ ካልተፈታ፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ሊገኝ፡ አይችልም። ይህን፤ ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ አልነኩትም፤ ሊነኩትም፡ አይችሉም። መለስ፡ ዜናዊ፡ የአሜሪካን፡ ጥቅም፡እስክ፡ ጠበቁ፡ ድረስ፡ የክብር፡ እንግዳ፡ መሆናቸው፡ይቀጥላል። ሜክሲኮ፡ የተገኙት፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ ነው።

ይህን፡ መግቢያ፡ ከሰጡ፡ በኋላ፤ ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ አዲስ፡ እቅድ፡ አለ፡ ያሉት፤ ኢትዮጵያን፤ ጋናን፤ ታንዛንያን፤ ያቀፈ፡ “A New Agriculture Alliance)፡ የእነዚህን፡ አገሮች፡ ጦም፡ አደር፡ አምሳ፡ ሚሊዮን፡ ህዝብ፡ እራሱን፡ ማስቻል፡ የሚል፡ ነው። ለዚህ፡ አላማ፡ ሃብታም፡ አገሮች፡ ሶስት፡ ቢሊዮን፡ ዶላር፡ ወጭ፡ ያደርጋሉ። “ዘላቂነት፡ እንዲኖረው፡ መንግስታት፤ ለጋሽ፡ ድርጅቶች፤ አርባ-አምስት፡ የሚሆኑ፡ የግል፡ ባለ፡ ሃቭቶች፤ ተቋሞች፤ የአካባቪ፡ ስብስቦች፤ ይሳተፉበታል። ከአላማው፡ ላይ፡ ብንስማማም፡ በቤን፡ ሻንጉል፡ ጉሙዝ፤ በደቡብ፤ በአማራ፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በአፋር፤ በኦሮሚያ፡ በኦሞ፡ ሸለቆ፤ ያሉ፡ የህብረተሰብ፡ ክፍሎች፡ ለጥቅማቸው፡ የቆመ፡ አጋር፡ መንግስት፡ ያስፈልጋቸዋል፡ ማለት፡ ነው። አሁን፤ የላቸውም። አቅማቸው፡ ካልተገነባ፡ (empowerment and engagement): ለጥቅማቸው፡ መቆም፡ ያስቸግራቸዋል። የመንግስት፤ የክልል፤ የአካባቢ፡ ተቋሞች፡ ለቁጥጥር፡ የተሰሩ፡ እንጂ፡ ለአቅም፡ ግንባታ፡ የተመሰረቱ፡ አይደሉም። እውቀቱ፤ መሳሪያው፤ ገንዘቡ፡ ያለው፡ ከግል፡ ባለ፡ ሃብቶች፤ ከውጭ፡ መንግስታት፤ ከአበዳሪወች፡ ጋር፡ እንጂ፡ ከህዝቡ፡ ጋር፡ አይደለም። አቅም፡ ካልተገነባ፤ ዘላቅነትና፡ ፍትሃዊ፡ የሆነ፡ እድገት፡ አሁንም፡ እውን፡ አይሆንም። ለም፡ መሬቱ፤ ለሃብታሞች፤ የምግብ፡ ዋስትናው፤ ለእነሱ፤ የውጭ፡ ምንዛሬው፡ ለህወሓት፡ ይሆናል፡ ማለት፡ ነው። ዋጋ፡ ከፋዩ፡ የአካባቢው፡ ህዝብ፤ የኢትዮጵያ፡ ሸማች፤ ኢትዮጵያ፡ ይሆናሉ፡ ማለት፡ ነው። አዲሱ፡ ውል፡ ከጥቅሙ፡ ጉዳቱ፡ ሊያመዝን፡ ይችላል፡ ለማለት፡ የምደፍረው፡ ውሎች፡ ለገበሬወች፤ ለኢትዮጵያ፡ ሸማቾች፤ ለአገር፡ ከበርቴወች፡ አያመዝኑም፡ በሚል፡ ነው። ነዋሪው፡ ህዝብ፡ በእራሱ፡ ለም፡ መሬትና፡ ወንዝ፡ አዛዥ፡ አይደለም፤ አይሆንም። ጠበቃ፡ የሚሆኑት፤ ማህበራዊ፡ ድርጅቶች፤ ከመንግስት፡ ቁጥጥር፡ ነጻ፡ የሆኑ፡ መገናኛ፡ ብዙሃን፡ ስለሌሉ፡ ለድሃው፡ ህዝብ፡ ጠበቃ፡ አይኖረውም። ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ ባንግላደሽ፤ ሃይቲ፡ የዝቅተኛ፡ አምራቾች፡ ውጤት፡ እጥፍ፡ አድጓል፡ ያሉት፡ ትክክል፡ ነው። በቬትናምም፡ እንደዚሁ። ነገር፡ ግን፡ እነዚህ፡ አገሮች፡ በን ኡስ፡ ብሄርተኛ፡ ቡድን፡ አይመሩም። በባንግላደሽ፡ ዘመናዊ፡ የመገናኛ፡ ስርጭት፡ አለም፡ ያደነቀው፡ ነው። በኢትዮጵያ፤ ህወሓት፡ መገናኛ፡ ብዙሃንን፡ ለመቆጣጠሪያ፤ ለማጥፋት፡ እንጂ፡ ለማጎልመሻ፡ አይፈቅድም። ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ የኢትዮጵያን፡ ድሃ፤ ዝቅተኛ፡ አምራች (smallholder): ለማጎልመስ፡ ከፈለጉ፡ መለስ፡ ዜናዊ፡ መገናኛ፡ ብዙሃንን፡ ነጻ፡ እንዲያደርጉ፡ መማጸን፤ የመሬት፡ ይዞታ፡ እንዲሻሻል፡መምከር፤ እርዳታ፡ ሁሉ፡ ለአቅም፡ ግንባታ፡ እንዲውል፡ ማድረግ፡ አለባቸው። ካልሆነ፤ ከስባዊ፡ አገልግሎት፡ ውጭ፡ እርዳታ፡ እንዳይስጥ፤ መሞከር፡ ወቅታዊ፡ ነው። እርድታ፡ ጎጂ፡ መሆን፡ የለበትም።

አለበለዚያ፤ ኢትዮጵያ፡ ያለ ውጭ፡ ድጋፍ፡ ሕዝቧን፡ ልትመግብ፡ አትችልም። መጋቪ፡ ግን፡ ለመሆን፡ ትችላለች። እንደ፡ ገና፡ ለማሣሰብ፡ የምፈለገው፤ በቅርቡ፡ ጠቅላይ፡ ሚንስተር፡ መለስ፡ ከታወቁት፡ ሃብታምና፡ ለጋስ፡ ቢል፡ ጌትስ፡ ጋር፡ ስለ፡ ዝቅተኛ፡ 15 ሚሊዮን፡ የኢትዮጵያ፡ አምራቾች፡ አቅም፡ የማጎልመስ፡ ጉዳይ፡ የተነጋገሩትና፡ የእርሻ፡ ምርትን፡ ለማሳደግ፡ የተዋዋሉት፤ ሃያ፡ አንድ፡ አመት፡ ሙሉ፡ ሊፈቱት፡ ያልቻሉትን፤ አሁን፡ ደግሞ፤ ካሩቱሪና፡ ሳውዲ፡ ስታር፡ ሊያሟሉት፡ የማይችሉትን፤ በእርሻ፡ ልማት፡ ላይ፡ የተመሰረተ፡ ልማት፡ ውጤት፡ አለማስገኘቱ፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ በውጭ፡ ኢንቬሰተሮች፡ ይገኛል፡ ብሎ፡ አዲስ፡ መንገድ፡ የመሻት፡ዘዴ፡ ብቻ፡ ነው። ቢል፡ ጌትስ፡ በቀጥታ፡ አምራቹን፡ ካጎለመሱ፡ ውጤት፡ ይገኛል። በሰፋፊ፡ የንግድ፡ እርሻ፡ ላይ፡ የተሰማሩት፡ የውጭና፡ የውስጥ፡ ተጠቃሚወች፤ የገዡ፡ ቡድን፤ ምርጥ፡ የትግራይ፡ አዲስ፡ ሃብታሞች፤ በግብዣ፡ የመጡ፡ ትርፍ፡ ፈላጊ፡ የውጭ፡ አገሮች፡ የፓርቲው፡ አባል፡ግለሰቦችና፡ መንግስታት፡ ርሃብን፡ ሊያስወግዱ፡ የማይችሉ፡ መሆናቸውን፡ አንጠራጠር። የሚሰሩት፡ ለትርፍ፡ የሚያመርቱት፡ ለውጭ፡ ገቨያ፡ ነው። Guardian, Human Rights Watch, Suvival International, Friends of the Earth, Oakland Institute የደረሱበት፡ ዘገቫ፤ ድምዳሜ፡ ይህ፡ ነው።

እነዚሃና፡ ሌሎች፡ እንዳሳዩት፤ ሁሉም፡ የተሰማሩት፡ ለትርፍ፡ እንጂ፡ ድህነትና፡ ርሃብን፡ ለማስወገድ፡ አይደለም። የመሬት፡ ነጠቃና፡ ቅርሚት፡ ጉዳት፡ በሁሉም፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ላይ፡ እነደሚሆን፡ ብዙ፡ ምርምሮች፡ ያሳያሉ። የመንግስትና፡ የግል፡ ትብብር፡ ችግሩን፡ ሊያስወግደው፡ አይችልም። መንግስት፡ የችግሩ፡ አካል፡ ስለሆነ። የውጭ፡ ሃብታሞች፡ ሚና፡ የፖሊሲና፡ መዋቅራዊ፡ ማነቆወችን፤ መለወጥ፡ አይችልም። ለአለም፡ ገቨያ፡ የምግቭ፡ ዋስትና፡ ማግኘት፤ ትርፍ፡ ማካቨት፡ ነው። ለዚህ፡ ነው፡ ፖሊሲው፡ መለወጥ፡ ያለበት። ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ ይህን፡ ዋጋ፡ አልሰጡትም። በአጭሩ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ በራሳቸው፡ አገርና፡ በራሳቸው፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፡ ላይ፡ አዛዥነታቸው፡ ማክተሙ፡ ለአገራችን፡ ነጻነት፤ አንድነት፤ ለሕቧ፡ ሉአላዊነት፡ አደገኛ፡ ነው። ይህን፡ አንቆ፡ የያዘ፡ የአገዛዝ፡ ስር አት፤ ለመለወጥ፡ የሚችለው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ እንጂ፡ የሃያል፡ መንግስታት፡ ከመለስ፡ ጋር፡ ድርድር፡ አይደለም። እኛ፡ ለማድረግ፡ የምንችለው፡ ድምጽ፡ ማሰማት፤ የመለስ፡ መንግስት፡ ፖሊሲውን፡ እዲለወጥ፡ ማጋለጥ። ካልለወጠ፡ ለአለም፡ፍርድ፡ ማቅረብ። ችግሩ፡ የገባቸውን፡ የአሜሪካ፡ ምክር፡ ቤት፡ አባላት፡ ጠበቃ፡ እንዲሆኑ፡ ቀርቦ፡ ማነጋገር፤ አብሮ፡ መስራት፡ ወዘተ፤ ናቸው።

ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ በቅርብ፡ አንድ፡ አለም፡ አቀፍ፡ ተቋም፡ ሰለ፡ ኢትዮጵያ፤ የተፈጥሮ፡ ሃቭት፡ አጠቃቅም፡ ያቀረበውን፡ ዘገባ፡ ያዩት፡ አይመስልም። “በአሁኑ፡ ወቅት፡ ከኢትዮጵያውያን፡ ይልቅ፡ የውጭ፡ ባለሃብቶች፡ እና ባለስልጣኖች፡ የበለጠ ሃይልና፡ ስልጣን፡ አላችው፡” የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ በሃገሩ፡ ምንም፡ ሃይልና፡ ዽምጽ፡ የለውም። ተሳትፎ፡ የለውም። ይህ፡ ስርአቱ፡ ያመጣው፡ ማነቆ፡ ነው። የውጭ፡ አገር፡ ባለሃብቶችና፡ ጥቂት፡ የህወሓት፡ ታማኞች፡ የኢትይጵያን፡ የእድገት፡ መሰረቶች፡ ቢይዙ፤ ስርአቱን ስለሚረዳው፡ የገዡ፡ ፓርቲ፡ አለቆች፡ ኢትዮጵያዊያን፡ በራሳችው፡ አገር፡ ቢናቁ፤ ቢያፍሩ፤ ቢሳደዱ፤ ታዛዥና፡ አጎብዳጂ፡ ቢሆኑ፤ እህቶቻችን፡ በአረብ፡ አገሮች፡ ቢዋረዱ፤ ቢራቡ፤ ምንም አይሰማቸውም። ስር አቱን፡ ስለሚጠቅም። ለዚህ፡ ነው፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ከድህነት፤ ከርሃብ፤ ከጥገኝነት፡ ሊያወጣት፡ የሚችል፡ ስር አት፡ አይደለም፡ ለማለት፡ የሚቻለው። የለም፡ የእርሻ፡ ሃብት፡ እና ወንዝ፣ ማእድን፡ እና የኢኮኖሚ አውታሮች፡ ቀስ በቀስ፡ ከአገርና፡ ከኢትዮጵያዊያን፡ እጂ፡ ወደ ፈረንጆች፡ እና፡ ጥቂት፡ የትግራይ ምርጥ፡ ተወላጆች፡ ሲተላለፉ፡ ዝም፡ ብለን፡ ማየት፡ በታሪክ፡ ያስጠይቃል፡ ለማለት፡ የምደፍረው። ሃብት፤ ጥሪት፤ ተሳትፎ፤ የመወስን፡ እድል፡ የሌለው፡ ሕዝብ፤ ድሃ ነው። በሃገሩ፡ ሊኮራ፡ አይችልም። ስለማያዝብት። ከገንዘብ፡ ድህነት፡ የባሰ፡ የመንፈስ፡ ድህነቱ፡ ያጠቃዋል። 76 በመቶ፡ የሆነው፡ የተማረ፡ ክፍል፤ ልሰደድ፤ ይሻለኛል፡ የሚለው፡ አገሩን፡ ጠልቶ፡ ሳይሆን፡ በሃገሩ፡ ሰርቶ፤ ኮርቶ፤ ተከብሮ፡ ለመኖር፡ ስለማይችል፡ ብቻ፡ ነው።

ስደት፡ እጣችን፡ ሆኗል። የአብዛኛው፡ ወጣት፡ ትውልድ፡ ድህ፡ ሁኖ፡ የመቆየት፡ እድሉ፡ ከፍ፡ እያለ፡ እንጂ፡ እየቀነሰ፡ የሚሂየድ፡ አይመስልም። ድህ፡ ሕዝብ፡ መከታ፡ የለውም፡፡ በሰላም፡ ተኝቶ፡ አያድርም። ሆዱ፡ ሞልቶ፡ አያድርም። መብቱን፡ ለማስከበር፡ አቅም፡ አይኖረውም። ህወሃት፡ ለም፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፤ ዉሃ፤ ማእድን፡ ፋብሪካ፡ ከኢትዮጵያዊያን፡ እና፡ ከአገር፡ ወደ፡ እራሱ፡ ተቋሞችና፡ ወደ፡ ደጋፊዎች፤ ወደ፡ ውጭ፡ ባለ፡ ሃብቶች፡ ሲያዘዘዋውር፡ የሚስራውን፡ ያውቃል። ይህ የሃብት፡ ዝውውር፡ ድጋፍን፡ ከኢንቭስተሮች፡ ያመጣለታል። ገንዝቭ፡ እንደልብ፡ ለማሸሽ፡ ያመቻል። ይህን፡ እንደ፡ ድል፡ ይቆጥረዋል። ቁጥጥርና፡ ዝውውር፡ ጣምራዊ፡ ናቸው፤ ይደጋገፋሉ። ከገንዘብ ጥቅሙ፡ ያላነሰ፡ የዲፕሎማሲ፡ ጥቅሙ፡ ከፍ፡ ያለ፡ ነው።

ወደ፡ ውስጥም፡ ብናይ፡ ይህ፡ ስርአትት፡ በራሱ ብቻ፡ የሚሺከረከር፡ አይደለም። ብዙ፡ ደጋፊወችን፡ በጥቅም፤ በጉቦ፤ በማስፈራራት፡ ያቀፈ፡ ነው። ስለዚህ፡ ስርአቱን፤ ከግለሰብ፡ ባሻገር፤ በሙሉ፡ ማየት፡ ይገባል። ተጠቃሚወችን፡ ባይሰበስብ፡ ኖሮ፡ እስክ፡ አሁን፡ ባልቆየም ነበር፡፡ በየቦታው፤ በየሕብረተሰቡ፡ ለእርሱ፡ አገልጋይና፡ አጎብዳጅ፡ የሆኑ፡ ደጋፊወችንና፡ እዝ፡ አስፈጻሚወችን፡ በጥቅም በመሳብ፤ በመደለል፤ በማስፈራራት፡ ወዘተ፤ ሰፋ፡ ያለ፡ ድርጂታዊ፡ አቅም፡ አለው። ሖኖም፤ በግብጽ፤ በሊብያ፤ በቱኒሲያ፤ በየመን፤ አሁን፡ በሶሪያ፡ እንደምናየው፡ በጥቅምና፡ በማስፈራራት፡ የተደራጀ፤ በጎሳ፤ በጠባብ፡ ቡድን፡ የተበከለ፡ ድርጂት፡ “የእምቧይ፡ ካብ፡” ነው። ሕዝብ፡ ከተነሳ፡ በቀላሉ፡ ይናዳል። ይህን፡ በመከፋፈል፡ የተዘረጋ፡ ስልት፡ እራሱ፡ የፈጠረው፡ ነው፡ ለማለት፡ አይቻልም። ከበፊቶቹ፡ የቀዳው፡ መጥፎ፡ ልምድ፡ አለ። በንጉሱ፡ ሆነ፡ በደርግ፡ ዘመናት፡ ከሁሉም፡ የህብረተስብ፡ ክፍሎች፡ የተመለመሉ፡ የስርአት፡ አገልጋዮች ነበሩ። በእነዚህ፡ ስራቶች፡ በደል፡ እና፡ አድሎ፡ አልነበረም ፡ ማለት፡ አይቻልም።

የአሁኑን፡ስርአት፡ የሚለየው፡ ዋናው፡ መለኪያ፡ መነሻው፤ ሂደቱ፡ እና፡ አሰራሩ፡ ሁሉ በዘር፤ ለዘር መሆኑ፤ ለጥቂት፡ ቡደን፡ መሆኑ፡ ነው። የዘር፡ ስርአት፡ አደጋ፡ ሁለ፡ ዘርፍ፤ ሁለ፡ ገብ፡ መሆኑን፡ እናያለን። ይህን፡ ለማድረግ፡ እየመረጠ፡ አለሁልህ፤ ይላል። ‘ድጋፍ፡ ከሰጠህ፡ ትበላለህ፤ ትኖራለህ፤ ትሰራልህ፤ ትማራለህ፤ መሬት፡ ትመራለህ፤ አላስርህም፤ አልገድልህም፤ ካልሰጠህ፡ ወዮልህ’፡ የሚል፡ ነው።የሰውን፡ ስነልቦና፡ ገምቶ፡ “ለከፋፍለህ ግዛው፤ ለፍርሃት፡ ዳርጎናል።

መገንዘቭ፡ የሚገባን፤ ተባባሪነት፤ አብሮ፡ ለአንድ፡ አገራዊ፤ በህዝብ፡ የበላይነት፡ ሊመሰረት፡ የሚገባ፡ ዲሞክራሳዊ፡ አላማ፡ መቆምን፤ ሃይማኖት፤ ጾታ፤ እድሜ፤ ጥቃቅን፤ የዱሮ፡ ታሪክ፡ ልዩነት፡ ሊገታው፡ አይችልም። ለነጻነት፤ ለእኩለነት፤ ለህግ፡ የበላይነት፤ ለፍትህ፡ ለኢትዮጵያ፡ አንድነት፤ ለመላው፡ ህዝቧ፡ ሉአላዊይነት፡ ከቆምን፤ ከህዝብ፡ ጎን፡ ከተሰለፍን፡ ምንም፡ የሚያግደን፡ ሃይል፡ አይኖርም። የሚያግደን፡ ህወሓት፡ ላጠመደልን፡ ማነቆ፤ በተለይ፤ ለፍርሃት፡ አጎብዳጅና፡ ተገዥ፡ መሆናችን፡ ነው። የሚያግደን፡ ለመሰብሰብ፤ ለመደጋገፍ፤ አብሮ፡ ለመስራት፤ ሃይላችን፤ ገንዘባችን፤ እውቀታችን፤ ወዘተ፡ ለአንድ፡ አገራዊ፤ አላማ፡ ለማዋል፡ ፈቃደኛነት፡ ማጣት፤ አገር፡ ሳይኖር፤ ለስልጣን፤ ለግል፡ ዝና፤ ለቡደን፡ መገዛት፡ ጭምር፡ ናቸው። ይህ፡ ባህል፤ አስተሳሰብ፡ መለወጥ፡ አለበት።