በዳባት ሕወሓት ጸረ ሕዝብ ዶክመንተሪ ፊልም ሊሰራ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጀግናውን የዳባትን ሕዝብ በተልካሻ ምክኒያት በመሸወድ ከዘረኛው እና ሰው በላው ሕወሓት መንግሥት ጎን የቆመ በማስመሰል ታላቅ ሰልፍ በማስወጣት በEBC ሰፊ ሺፋን ተሰጥቶት ዶክመንታሪ ፊልም ሊሠራ መሆኑ ታውቋል።

ባንዳው የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ አገናኘው አስማማው ከዳባት አጅሬ የሚሰራውን መንገድ ምክኒያት በማድረግ የሁሉንም
ቀበሌ ነዋሪዎች ከመስከረም 25 -27 2009ድረስ የሚቆይ ሰልፍና ስብሰባ በማስወጣት በአሁኑ ሰዐት በአማራና
በኦሮሚያ የሚካሄደውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት የሚያወግዙ ጽሑፎችን ከሕዝቡ ማሀል አድርገው በካሜራቸው ፊልም ለመሥራት መዘጋጀታቸው ታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ትግሬዎች በገንዘብም በሀሳብም ከጎናቸው ነን ያፈናቀሏቸው ትምክህተኞችና የነፍጠኛውን ሥርአት የሚናፍቁ ናቸው የሚሉሀሳቦች በስፋት ሊሰራባቸው የታሰቡ ተግባራት ናቸው።
ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነው እንዲሉ አበው የዳባት ሕዝብ ይህን ስብሰባ ይሁን የማጭበርበሪያ ሰልፍ ለአማራው ተጋድሎ በሚመጥን መልኩ ትጠቀምበት ዘንድ ከወገኖችህ (የዳባት ነዋሪዎች) ተጠይቀሃል። የባንዳው የአቶ አገናኘው አስማመው ዘመዶችና ወዳጆች የባንዳነት ሥራውን እንዲያቆም ትመክሩት ዘንድ ትጠየቃላችሁ።