ለቂሊንጦ ማ/ቤት እሳት ቃጠሎ ንፁሃን ሙስሊም እስረኞችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ባስቸኳይ ይቁም
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ለቂሊንጦ ማ/ቤት እሳት ቃጠሎ ንፁሃን ሙስሊም እስረኞችን ተጠያቂ
ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ባስቸኳይ ይቁም ——- ፍትህ ራዲዬ
ይህ ወንድማችን ኡመር ሁሴን ይባላል፡፡ በሼኽ ኑሩ ግድያ በሃሰት
ተወንጅሎ ከደሴ ከተማ ተይዞ በማዕከላዊ አሰቃቂ እና ከባድ
የተባለውን የስቃይ እና የግፍ ቅጣት በምርመራ ወቅት አሳልፏል፡፡
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆን ተብሎ በመንግስት በተለኮሰ እሳት
ማረሚያ ቤቱ ከተቃጠለ ቡኋላ በዚህ ወንድማችን ላይ አካሉ
እስኪዝል ድረስ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውበታል፡፡ ወደሸዋሮቢት
ማረሚያ ቤት ከተወሰደም በኋላ እጁ የታሰረበት ካቴናው
እንዳይፈታለት በማድረግ እጁ እስኪቆስል ድረስ እያሰቃዩት ይገኛሉ፡፡
የቂሊንጦ ማ/ቤት እሳት ቃጠሎንም ሆን ብላችሁ ያደረጋችሁት እናንተ
ናችሁ ከተባሉት መካከል እሱም አንደኛው ነው፡፡ የማዕከላዊ
መርማሪዎች ወደ ሸዋሮቢት በመሄድ በግዳጅ ማረሚያ ቤቱን እኛ ነው
ያቃጠልነው ብላችሁ እመኑ በሚል ከማዕከላዊ የባሰ ዘግናኝ ግፍ
እየፈፀሙባቸው ይገኛል፡፡
በማረሚያ ቤቱ በፂሙ የተነሳ ከፍተኛ በደል እየተፈፀበት ሲሆን
መርማሪዎች ማን ፈቅዶልህ ነው ፂምህን እንዲህ ያሳደከው በማለት
እያሰቃዩት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ወንድም ኡመር ፂሜን እንዳሳድግ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶልኛል ቢላቸውም
ፍርድ ቤት ምን አገባው እና ነው ላንተ ፂም ማሳደግ የሚፈቀድልህ
በማለት እጁን በካቴና በማሰር ከፍተኛ ስቃይ እና ግፍ እየፈፀሙበት
እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
እስረኞቹ እየደረሰባቸው ባለው ስቃይ የበፊት ጥንካሬያቸው ከድቷቸው
ቤተሰብ ሲመለከታቸው ከአይናቸው እንባቸውን በማፍሰስ በደከመ፣
በተጎሳቆለ እና አቅም ባጣ አካላቸው እባካችሁ በቀየኑ መጥታችሁ
እይኙን ከዚህ በኋላ ምን እንደሚያደርጉን አናውቅም፡፡ እዚህ ማረሚያ
ቤት የሉም እስክትባሉ ድረስ መጥታችሁ እዩን ሲሉ ለቤተሰቦቻቸው
እንባቸውን እያፈሰሱ እየተማፀኑዋቸው ይገኛሉ
ይህ ሁሉ ግፍ እና ስቃይ እየተፈፀመባቸው የሚገኘው በቂሊንጦ
ማረሚያ ቤት የተከሰተውን እሳት ቃጠሎ እና ግድያ በእስረኞቹ ላይ
ለማላከክ በማቀድ ነው፡፡
ከእሳት ቃጠሎ እና ከጥይት የተረፉትን እስረኞች እየተፈጸማባቸው
ያለውን ግፍ በጋራ እንቃወም።
ስቃያቸውን እና ለቅሷቸውን በዱዓ እንጋራቸው
