ዲያስፓራው የትግሉ አጋር ሆኖ ይቀጥላል! – ድምፃችን ይሰማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ድምፃችን ይሰማ
#EthioMuslims #EthioMuslimDiaspora #EthioMuslimPeacefulStruggle
ዲያስፓራው የትግሉ አጋር ሆኖ ይቀጥላል!
ህብረተሰባችንን በትግላችን ዙሪያ በማሰባሰብ ትግላችንን እናጠናክራለን!
ረቡእ መስከረም 18/2009
ቀጣይ ትግላችን ሙሉ መብታችንን በዘላቂነት ማስከበርን ዓላማው ያደረገ
እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ማንሳታችን፣ ለትግላችንም መጠናከር እና ግቡን መምታት
ህብረተሰባችን በግል እና በቡድን ያለበትን ሃላፊነቶች የሚያመላክቱ የግንዛቤ
ማስጨበጫዎችን መልቀቃችን ይታወቃል፡፡ የትግሉ ጀማሪ ህብረተሰባችን
እንደመሆኑ መጠን መመለሻው እና መቋጫውም ህብረተሰባችን ነው።
የትግላችን መለያ ከሆኑት ባህሪዎቹ መካከል አንዱ ህዝባዊነቱ ሲሆን ሁሉን
አሳታፊ ሆኖ መቀጠል እና ለዚህም አመቺ የሆነን የትግል ማእቀፍ መዘርጋት
የዚህ ህዝባዊነቱ መገለጫ ነው። ሌላው የትግላችን ህዝባዊነት መገለጫ
ደግሞ ትግሉ በተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ወይም ቡድን የተወሰነ ሳይሆን
ሁሉንም አማክሎ እና የሁሉንም ጥረት በግብዓትነት ይዞ የሚጓዝ መሆኑ ነው።
በዲያስፓራ ያለውን መስሊም ማህበረሰብ በማሳተፍ ይህ የህብረተሰባችን ክፍል
ለወገኑ እና ለአገሩ ብልጽግና፣ ለሰላሟ፣ ለህዝቦቿ መብት መከበር እና
ለፍትሃዊነት የራሱን አሻራ እንዲጥል የሚያስችል መሆኑም በተጨማሪነት
ይጠቀሳል፡፡
ባለፉት 5 ዓመታት የዳያስፖራው ማህበረሰባችን ሁለገብ በሆነ መልኩ
ትግላችንን ለመደገፍ ሲያደርጋቸው የቆያቸው ጥረቶች ምትክ አልባ ነበሩ።
የተለያዩ ሰልፎችን በማዘጋጀት፣ ሲምፖዚየሞችን በማካሄድ፣ ዓለም አቀፉን
ማህበረሰብ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዙሪያ ሎቢ በማድረግ እና በትግሉ
ለተጎዱ አካላት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
እንደህዝብ አጋርነታቸውን በጠየቅንባቸው ወቅቶች ሁሉም አሳፍረውን
አያውቁም፡፡ ለዚህ ታላቅ አጋርነታቸው አላህ መልካም ምንዳቸውን ይሞላላቸው
ዘንድ ሁልጊዜም ምኞታችን ነው፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት ከላይ በተገለጸው መልኩ ለትግላችን ታላቅ የደጋፊነት ሚና
ሲጫወት የቆየው በዲያስፓራ የሚገኘው ህብረተሰባችን እያደረገ ያለው
አስተዋጽኦ የበለጠ ፍሬያማ እንዲሆን የሚያስችሉ መሰረታዊ ስራዎችን ስንሰራ
ቆይተናል። ከእነዚህ መካከል ህብረተሰባችን በመካከሉ ያሉ ጥቃቅን ልዩነቶችን
በማቻቻል ራሱን በሰፊው የትግል ማእቀፋችን ዙሪያ እንዲደራጅ ማስቻል
ቀዳሚው ስራችን በመሆኑ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና
ጥሪዎችን አድርገናል።
አንድ ትግል መስመር የሚይዘው እና ለዘላቂነቱም ዋስትና የሚኖረው የተደራጀ
ህብረተሰብ መፍጠር ከቻለ ብቻ ነው። በዲያስፓራ ያለው ህብረተሰባችንም
የትግላችን አጋር እንደመሆኑ ራሱን በትግሉ ዙሪያ ማደራጀት እና ጥረቶቹንም
በትግሉ ማዕቀፍ ውስጥ ማድረግ የግድ ይለዋል። እንቅስቃሴውም ለዚህ ሂደት
ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ይጠበቅበታል።
ህብረተሰባችንን በትግላችን ዙሪያ በማሰባሰብ ትግላችንን እናጠናክራለን!
ከዚህ ፅኑ እምነት በመነሳት ዲያስፓራው የትግላችን ምሰሶ መሆኑን እውቅና
በመስጠት ይህን ኃላፊነቱን ይወጣ ዘንድ ጥሪ ከማቅረብ ጀምሮ በትግሉ ዙሪያ
እንዲሰባሰብ፣ እንዲደራጅ፣ እንዲሁም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለትግሉ
ቀጥተኛ ግብዓት እንዲሆኑ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። የትግላችንን
አራተኛ ዓመት በዘከርንበት ወቅትም ከነበሩን አራት መርሃ ግብሮች መካከል
አንዱ ሙሉ ትኩረቱን ያደረገው በዲያስፓራው ላይ ነበር። በዚሁ ወቅትም
በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ተደራሽ ያደረገ እና ከእንቅስቅሴው
ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው የዋትስአፕ ቁጥር መክፈታችን ይታወሳል። ይህ
በተቀሩት የዓለማችን ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመድረስ ለምናደርገው ሰፊ
እና ቀጣይነት ያለው ስራ መጀመሪያ እንዲሆን ታስቦ የተጀመረ እንደሆነ በወቅቱ
ገልጸናል።
በዲያስፓራ ከሚገኘው ህብረተሰባችን አብዛኛው የተሰባሰበው በመካከለኛው
ምስራቅ መሆኑ የሚካድ አይደለም። ከአገር ውጭ ሆኖም በስርዓቱ የብዝበዛ ስር
ያለው በዚሁ የአለማችን ክፍል የሚገኘው ህብረተሰባችን ነው። በአገር ሁስጥ
ከአምባገነኑ መንግስት ጋር ከምናደርገው ፍጥጫ ባላነሰ መልኩ በመካከለኛው
ምስራቅ ያለውን ህብረተሰባችንን በትግላችን ዙሪያ ማሰባሰብ መቻላችን
ለሂደታችን ይህ ነው የማይባል ጉልበት እንደሚሆነው የሚካድ አይደለም።
እንቅስቃሴያችን ለዲያስፓራው ጥሪ ካቀረብንበት ጊዜ ጀምሮ በመካከለኛው
ምስራቅ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ራሳቸውን በወጣው የትግል ማዕቀፍ ውስጥ
ለማስገባት እና ለትግሉ እስካሁን እያደረጉ ያለውን አስተዋጽኦ ይበልጥ
ለማጠናከር እና ለትግሉም ቀጥተኛ ግብዓት እንዲሆን ጥረቶችን እያደረጉ
ይገኛል። ዛሬ ላይም ስብስባቸውን አብዝተው፣ አሰራራቸውንም መልክ አስይዘው
ይገኛል። ይህ ሂደት በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኘው ህብረተሰባችን በቀጣይ
አንድነቱን አጠናክሮ በትግሉ ዙሪያ ለመሰባሰብ ለሚያደርገው ጥረት መሰረት
ጣይ እና ፈር ቀዳጅ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎች ላለው ህብረተሰባችንም
አርዓያ የሚሆን ጅምር ነው። በመሆኑም ጅምሩ ይበልጥ ተጠናክሮ እና ሰፍቶ
ይቀጥል ዘንድ ሁሉም የህብረተሰባችን ክፍል እገዛ ሊያደርግላቸው ይገባል።
በተለይም ሙስሊም የሃይማኖት ምሁራን እና የትግሉ አቀንቃኞች (አክቲቪስትስ)
ልዩ ኃላፊነት አለባቸው። የሙስሊሙ ሚዲያ አውታሮችም ጅምሩ አድማሱን
እንዲያሰፋ እና ተሞክሮውንም ለሌሎች አዳርሶ ሰፊው የመካከለኛው ምስራቅ
ህብረተሰባችንም አርዓያቸውን እንዲከተል እና ራሱን በትግሉ ዙሪያ ያሰባስብ
ዘንድ ስራዎቻቸውን በማሰራጨት በኩል ታላቅ ኃላፊነት አለባችሁና ይህንን
ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪያችንን አያይዘን እናቀርባለን።
በዲያስፓራ የመካከለኛው ምስራቅ ዲዋይ ጀመዓዎችን ለማግኘት በሚከተሉት
የዋትሳፕ ቁጥሮች አስተባባሪዎችን ማነጋገር የሚቻል መሆኑን እናታውቃለን፡-
1/ +1 267 818-8896
2/ +966 50 072 2040
3/ +971 50 188 7558
4/ +971 55 571 5476
5/ +32 465 92 03 40
ዲያስፓራው የትግሉ አጋር ሆኖ ይቀጥላል!
ህብረተሰባችንን በትግላችን ዙሪያ በማሰባሰብ ትግላችንን እናጠናክራለን!
ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን በአላህ ፍቃድ እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
Like Comment Share

Image may contain: text