ሰውን እንደ እባብ መቀጥቀጥ በህግ የተፈቀደ እስኪ መስል ድረስ የአራተኛ ክፍለጦር ወታደሮችም መፈጠሬን እስክጠላ ገረፋኝ ። አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሰውን እንደ እባብ መቀጥቀጥ በህግ የተፈቀደ እስኪ መስል ድረስ የአራተኛ ክፍለጦር ወታደሮችም መፈጠሬን እስክጠላ ገረፋኝ ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ

(በፎቶው ላይ የምንመለከተው ጥላሁን በ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ሲውል ነው )

(በፎቶው ላይ የምንመለከተው ጥላሁን በ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ሲውል ነው )

//ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ እና የ 1953ቱ መፈንቅለመንግስት //

/በኢዮብ ዘለቀ/

“የመፈንቀለ መንግስት ሙከራው በተካሄደ በአራተኛው ቀን መሰለኝ ጃንሆይ ጉብኝታቸውን አቋርጠው አዲስ አበባ ገቡ ።አሁን አገር ሰላም ነው አልሁና እኖርበት ወይም በጭንቅ ሆኜ ሁኔታውን እከታተልበት ከነበረው ፊት በር እየተባለ ከሚጠራው ሰፈር ወጣሁና አራት ኪሎ አቶ ሻወል ቤት ገባሁ ።ለካ ጦር ሰራዊት ይከታተለኛል ።ድንገት ጀርባዬን በሰደፍ ደቃና ቀጥል አለኝ ።
ከዛ ሌሎችም በጥፊ በርግጫ እያዳፋ እንዲያውም የሌለኝን መአረግ ሁሉ እየስጡኝ ”የኛ መቶ አለቃ! የሾሙህ የሸለሙህ ጃንሆይ መጥተዋል ምን ይዋጥህ? አንተ ከሀዲ! ለሰንደቅ አላማህና ለንጉስህ የገባህውን ቃል በልተህ መንግስት ልትገለብጥ ሞከርህ አይደል.. ..”አሳሬን ያሳዩኝ ጀመር። መልስ ለመስጠትና ”መቶ አለቃ ቀርቶ ወታደር አይደለሁም ፤ሲቪል ነኝ ” ብዬ ለመናገር እንኳ ፋታ አልሰጡኝም ።ቁም ስቅሌን አሳዩኝ ።በዚህ አይነት ሁኔታ መከራዬን እያሳዩ ወስደው አሁን ሸራተን አዲስ ወደ ተሰራበት አካባቢ ከነበረ ሽንት ቤት ውስጥ አስገቡኝ ።እውነት ለመናገር ያን ሁሉ መከራ ከማየት ያን እለት ብሞት እመርጥ ነበር ።

አንዴ በርግጫ ፣ሊያውም በወታደር ጫማ ፣እንደገና በጥፊ ፣እንደገና በቆመጥ.. ….እረ ስንቱ ይነገራል? እና እንዲህ እንደ አውድማ ላይ ገብስ ሲወቁኝ ውለው ሽንት ቤት ከዘጉብኝ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ”አራተኛ ክፍለጦር ”ወሰዱኝ ።
እዚያ ስደርስ የያዙኝ ወታደሮች በኩርንችት ጫማ እስከሚበቃቸው ከወቀሩኝ በሁዋላ ለዘቦች አስረከቡኝ ። ሰውን እንደ እባብ መቀጥቀጥ በህግ የተፈቀደ እስኪ መስል ድረስ የአራተኛ ክፍለጦር ወታደሮችም መፈጠሬን እስክጠላ ገረፋኝ ።እረ ”ገረፋኝ” የሚለው ቃል አይገልጸውም ።ሕሊና ያለው ሰው በመሰሉ ላይ ይፈጽመዋል ተብሎ የማይታሰበውን የጭካኔ እርምጃ ወሰዱብኝ ።”
(ክቡር ዶ/ር አርስቲት ጥላሁን ገሠሠ እንደተናገረው )

መስከረም 17 የሀገር ልጅ ጥላሁን ገሠሠ ልደት