ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ October 3, 2016 በአለም ላይ በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት በአለም ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ – ጀርመን
—————————————————————————————–
ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ October 3, 2016 በአለም ላይ በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት በአለም ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የጀርመን መራህቲ መንግስት ወይዘሮ አንጀላ መርክል የኢትዮጵያ ጉዞ በማስመልከት ሰኞ በኦክቶበር ሦስት ጀርመን የተዋሃደችበት ቀን ነው ትልቅ በአል ነው። ሰብአዊ መብት ለአርባ አመት ሲረግጥ የኖረው ምስራቅ ጀርመን ዲክታተር ስርዓት ተገርስሶ ሁለቱ ጀርመኖች የተዋሃዱበት ቀን ነው ።
የወቅቱ የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ እንዲሁም የወቅቱ መራህቲ መንግስት ወይዘሮ አንጀላ መርክል የምስራቅ ጀርመን ዲክታተር ስርዓት ተገርስሶ ነው ነጻነታቸውን ያገኙት። እ.አ.አ October 3, 2016 መራህት መንግስት ወይዘሮ አንጀላ መርክል በጀርመን የዲሞክራሲ እና የነጻነት የአንድነት በአል በሚከበርበት ቀን በኢዮጵያ ጉብኝት ላይ ይገኛሉ። የጀርመን መንግስት በህገመንግስቱ የተደነገገውን በአለም አቀፍ ህግ የተደነገገውን በመጣስ (ክራይም አጌይንስት ህዩማኒቲ) ዘር ማጥፋት ማፈናቀል በኢትዮጵያ ውስጥ ይተባበራል።
በዚህ አጋጣሚ በአለም ያሉ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰኞ በኦክቶበር ሦስት October 3, 2016 ጀርመን የተዋሃደችበት የጀርመን መንግስት በጀርመን የምስራቁን ከዲክታተር ወደ ነጻነት ዲሞክራሲ በሚያከብርበት ቀን በኢትዮጵያ የጀርመን መንግስት እየደገፈው ያለውን የሰብአዊ መብት ረጋጭ ስርዓት በአለም ለማጋለጥ የፈሰሰውን እና የሚፈሰውን የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም በማስታወስ በአለም ላይ በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ እንድታደርጉ በማክበር እንጠይቃለን። በኢትዮጵያ በንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየትካሄደ ያለው አፈና እና ጭፍጨፋ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የለጋሽ አገር መሪ ጉዞ የመጀመሪያ ነው።
ለታፈኑት ለሚታፈኑት ለተገደሉት ለሚገደሉት ለታሰሩት ለሚታሰሩት ለተፈናቀሉት ለሚፈናቀሉት ለተጨፈጨፉት ለሚጨፈጨፉት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ድምጻችንን እናሰማ። የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል። ለመረጃ ያህል የጀርመን መንግስት እና ህዝብ እ.ኤ.አ ኦክቶበር ሦስት የምስራቁም ጀርመን ክፍል ከዲክታተር ተላቆ የህግ የባላይነት ዲሞክራሲ እንዲሁም ሰብአዊ መብቶች በማረጋገጥ ጀርመን የተዋሃደችበት ቀን ሆኖ በዲክታተር የተሰቃዩት እሚታወሱበት ዲክታተር የሚወገዝበት ቀን ነው።
በተለይ የጀርመኑ ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ እንዲሁም መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ሁለቱ ጀርመኖች እስከ ተዋሃዱበት ድረስ በዲክታተር አገዛዝ ስር በምስራቅ ጀርመን ዜጋ እና ነዋሪ ነበሩ ሁለቱም ነጻነት ያገኙት ሁለቱ ጀርመኞች ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው ሁለቱም በዲክታተር ስርታአት የማይቻለውን በዴሞክራሲ ሁለቱም የተዋሃደው ጀርመን የአገር መሪ ለመሆን በቅተዋል።
ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል። ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ በ march 17 – 20, 2013 የኢትዮጵያ ጉዞዋቸው ከፖለቲከኞች እና የታወቁ ሰዎች ተገናኝተው ይህ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ የድሮ አገሬን ምስራቅ ጀርመንን ያስታውሰኛል ብለው ነበር። በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን ጥያቄ በእዚሁ በጀርመን ኤምባሲ በተካሄደው (ሪሴፕሽን) አቀባበል ላይ ተጋብዘው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሰብማአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን በጹሁፍ የገለጡት ነው ። ዶር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል የጹሁፍን ኮፒ ልከውለታል ደርሶታል።
ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል። ጊዝ ወይም በቀድሞ ስሙ ጂ ቲ ዜድ በተባለው የጀርመን የርዳታ ሚኒስትር ስር የሚተዳደር ድርጅትም ባለፈው አመት 2015 የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ላይ ሦስት ሺ ወጣቶች የጀርመንን ሰንደቅአላማ ቀለም በማስለበስ የጀርመንን ውህደት ምስራቅ ጀርመን ከዲክታተር ሥርዐት ተላቅቃ ወደ ሰብሳአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲሁም የህግ የበላይነት ከተረጋገጠበት ምዕራብ ጀርመን ጋር የ ሃያ አምስተኛ አመት መዋሃድ በአዲስ አበባ አስከብሯል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን