ፌስቡክ ላይ ያሉ ቫይረሶች እና መፍትሄያቸው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ፌስቡክ ላይ ያሉ ቫይረሶች እና መፍትሄያቸው ፡-
1- በጣም አደገኛው ቫይረስ በአፕ መልክ የቀረበ ሲሆን ሙሉ መረጃችሁን ለመስረቅ በመጀመሪያ እናንተን ሸውደው ፈቃድ ያገኛሉ። ይሄን ይመስላሉ ፣
— Who among your FB friend is secretly in love with you?
— who viewed my profile
— Who visited your profile most?
— Who will you marry?
— Which friend likes you the most?
እና የመሳሰሉ በርካታ አማላይ የሚመስሉ ነገሮችን ያያሉ። እነዚህን ከፍተን መልሱን ለማግኘት ስንሞክር መረጃችንን በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዲያውሉት እየፈቀድን ስለሆነ መጠንቀቅ አለብን።
★ ፌስቡክ በይፋ እንዳሳወቀው የትኛውም አፕ (App) ወይም ገፅ ይሄን ማድረግ እንደማይችል ገልጿል፣ በዚህ መልኩ የሚያገኙት መልስም ትክክል አይደለም።
2- ሌላው የቫይረስ አይነት የፌስቡክን ቀለም መቀየር ይፈልጋሉ? የፅሁፎቹን አይነት እና አቀማመጥ መቀየር ይፈልጋሉ? Dislike እንዲመጣሎ ይፈልጋሉ? በመሳሰሉ የማይሆኑ ማሳሳቻ ጥያቄዎች አድራሻውን እንድትከፍቱት በማድረግ የመረጃ መስረቂያ አፕልኬሽናቸውን የናንተ ፌስቡክ ላይ ይጭናሉ።
★ እውነታው ግን ከፌስቡክ ውጭ ድህረገፁን ሊቀያይር የሚችል ምንም መተግበሪያ አለመኖሩ ነው።
3- ይሄኛው መንገድ ደግሞ ቫይረሳቸውን ለመጫን የሚጠቀሙት የነፃ ስጦታ ስላለ እንዲመዘገቡ በማማለል ነው። ተሸውዳችሁ ወደ ወጥመዱ ትገቡና ቫይረሱን ሌሎች አይተው እንዲከፍቱት በናንተ ስም ገፃችሁ ላይ ፖስት ያደርጋል።
በቅርቡ በጣም በዝቶ የነበረው Iphone 6 ተሸለሙ የሚል ቫይረስ ነበር። ሽልማቱ የሚሰጣችሁ መሰሏችሁ የግል መረጃችሁን ትሰጣላችሁ።
★ እውነታው ግን በፌስቡክ የትኛውም ድርጅት በነፃ ምንም እንደማይሰጣችሁ ነው።
4- በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበዛው ቫይረስን በቪድዮ መልክ ማቅረብ ነው። ይህም ትኩረት የሚስብ ምስል እና ርእስ ጋር መልቀቅ እና ስትከፍቱት ቫይረሱ ወዲያውኑ ጥቃቱን ይጀምራል።
አብዛኛውን ጊዜ ቪድዮዎቹ የሚሰጣቸው ርእስ ፣
የአሸባሪዎች ግርፋት እና ግፍ፣
የታዋቂ ሰዎች ሚስጥር፣
ታይቶ የማይታወቅ አይነት ፍጡር (8 ጭንቅላት ያለው እባብ፣ ከወገብ በታች እባብ የሆነ ሰው …) ፣
የወሲብ ቪድዮ ።
★ በዚህ ቫይረስ ላለመጠቃት ተመሳሳይ ቪድዮችን መክፈት አይኖርብንም።
>> እንደ መፍትሄ –
ከ 1-3 በተጠቀሱት የቫይረስ አይነቶች ፌስቡክዎን ማጥቃታቸውን ለማወቅ እና ለማስወገድ የሚከተለውን እናድርግ።
—> Settings & Privacy —> Apps —> Logged in with Facebook
– ይሄን ስንከፍት ፌስቡካችን ጋ የተገናኙ አፕሊኬሽኖችን ያገኛሉ።
– ከታዋቂዎቹ skype, viber ከመሳሰሉት ውጭ የምታገኟቸውን በየተራ በመክፈት ከስር Remove App የሚለውን በመምረጥ ማጥፋት።